Get Mystery Box with random crypto!

እኚህ እናት ለባንክ ቤት ሰራተኛዋ ካርዳቸውን ሰጥተው 'አስር ዶላር ማውጣት እፈልጋለሁ' አሏት።ከመ | ውብ ታሪኮች ®

እኚህ እናት ለባንክ ቤት ሰራተኛዋ ካርዳቸውን ሰጥተው "አስር ዶላር ማውጣት እፈልጋለሁ" አሏት።ከመቶ ዶላር በታች የሚያወጡ ከሆነ እባክዎ ATM ይጠቀሙ አለቻቸው።ሴትየዋም "ለምን" ብለው ጠየቁ።የባንክ ሰራተኛዋም በስጨት ብላ ካርዱን እየመለሰች ይሄ የባንኩ ህግ ነው ይልቁን ቦታ ይልቀቁልኝ ከኋላ ያለውን ሰልፈኛ ላስተናግድበት አላቻቸው።

ሴትየዋም ለጥቂት ደቂቃ ዝም እንደማለት አሉና ካርዳቸውን ለባንኩ ሰራተኛ መለሰው "እንዲያውም የእናንተን ባንክ አልፈልገውም ገንዘቤን በሙሉ አውጣና ስጠኝ" አሏት።የባንኩ ሰራተኛም ሴትየዋ ባንክ ውስጥ ያላቸውን የገንዘብ ሙጠን ስታይ ደነገጠች።ጭንቅላቷን ነቅነቅ አድርጋ ከእክብሮት ጋር በአካውንትዎ $300,000 ዶላር ነው ያለው።ባንካችን ደግሞ በዚህ ሰአት ይሄን ያክል ገንዘብ የለውም ነገ ተመልሰው የሚመጡ ከሆነ ቀጠሮ ልያዝልዎት? አለቻቸው።

ሴትየዋም "እሺ አሁን ማውጣት የምችለው ከፍተኛው የገንዘብ መጠን ስንት ነው" ብለው ጠየቁ።የባንኩም ሰራተኛ እስከ $3,000 ዶላር ብላ መለሰች።"እሺ እንደዛ ከሆነ $3,000 ዶላር ስጪኝ"አሉ።የባንኩ ሰራተኛም ፈገግ ብላ ገንዘቡን ሰጠቻቸው።

ሴትየዋም $10 ዶላር አውጥተው ከቦርሳቸው ከተቱና የተቀረውን $2990 ገንዘብ መልሰው ለሰራተኛዋ ሰጥተው የባንኩን ሰራተኛ ይሄንን መልሰሽ ከአካውንቴ ክተችልኝ አሉዋት።

The moral of this story is....

ዘላለም | @WubTarikoch