Get Mystery Box with random crypto!

#የሕይወትህን_መሪ_አሳልፈህ_አትስጥ! አንድ አሜሪካዊ ሰው ለንደን ውስጥ ወደሚገኝ ሬስቶራንት ገባ | ውብ ታሪኮች ®

#የሕይወትህን_መሪ_አሳልፈህ_አትስጥ!

አንድ አሜሪካዊ ሰው ለንደን ውስጥ ወደሚገኝ ሬስቶራንት ገባ፤ እንደገባም ጥግ ላይ አንድ ህንዳዊ ተቀምጦ አየ።

እናም ወደ ባልኮኒው አመራና የኪስ ቦርሳውን በእጁ እንደ ያዘ፣ እንዲህ ብሎ ጮኸ
"አስተናጋጅ! እዚህ ሬስቶራንት ውስጥ ላሉ ተመጋቢዎች በሙሉ ምግብ ጋብዤያቸዋለሁ፤ እዛ ጥግ ካለው ጠቋራ ህንድ በስተቀር!"

ሆኖም ከመናደድ ይልቅ ህንዳዊው ድምጹን ከፍ አድርጎ፣ አሜሪካዊውን እየተመለከተ"አመሰግናለሁ" አለው።
ይህም ሰውዬውን አስቆጣው።

እናም በድጋሜ አሜሪካዊው የኪስ ቦርሳውን አወጣና ጮኸ "አስተናጋጅ፤ አሁን ለሁሉም ጠርሙስ ወይን እና ተጨማሪ ምግብ ጋብዣለሁ፤ እዛ ጥግ ካለው ጠቋራ ህንድ በስተቀር!"

እናም አስተናጋጁ ከሰውዬው ገንዘቡን ተቀብሎ ምግብ እና ወይኑን ለተስተናጋጆቹ ማቅረብ ጀመረ። አሁንም ህንዳዊው አልተናደደም፤ በድጋሜ በፈገግታ ተሞልቶ "አመሰግናለሁ" አለ፡፡

ይህም ይበልጥ አሜሪካዊውን አበሳጨው፤ እናም ባልኮኒው ላይ እንደተደገፈ ወደፊት አዘንብሎ አስተናጋጁን ጠየቀው
"ያ ሕንዳዊ ሰው ምንድን ነው ችግሩ? ከእርሱ በቀር ለሁሉም ሰው ምግብ እና መጠጥ ገዛሁ፤ ነገር ግን ከመናደድ ይልቅ _ እየሳቀ 'አመሰግናለሁ' ይለኛል፤ እብድ ነው?"

አስተናጋጁም በአሜሪካዊው ንግግር እየሳቀ እንዲህ አለው "አይ እብድ አይደለም ፤ እሱ የዚህ ሬስቶራንት ባለቤት ነው"

@WubTarikoch