Get Mystery Box with random crypto!

ያንተ ጓደኛ ይሄ ነው..? ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ አንድ ወታደር በውጊያ ሜዳ የወደቀውን ጓደኛውን | ውብ ታሪኮች ®

ያንተ ጓደኛ ይሄ ነው..?

ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ አንድ ወታደር በውጊያ ሜዳ የወደቀውን ጓደኛውን ለመፈለግ አለቃውን ያስፈቅዳል። አለቃውም 'መሞቱ ለማያጠራጥር ሰው ብለህ ህይወትህን አደጋ ላይ እንድትጥል አልፈቅድልህምበማለት ፍቃድ ይነፍገዋል፡፡

ወታደሩ ግን አሻፈረኝ ብሎ ፍለጋውን ይቀጥላል፡፡ከፍለጋ በኋላ እሱም ሞት አፋፍ ላይ ባደረሰው ሁኔታ ቆስሎ የሞተ ጓደኛውን አስክሬን ተሸክሞ ይመጣል፤አለቃውም 'ይሞታል ብዬህ አልነበረም? ለሚሞት ሠው ብለህ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል ነበረብህ፤' በማለት ይወቅሰዋል፡፡

ወታደሩ ግን በስራው ደስተኛ ነበር ። አለቃዬ ይህኮ ምንም ማለት አይደለም ጓደኛዬ በሞት አፋፍ ላይ ደርሸበት ያለኝን ብነግርህ ትረዳኝ ነበር ፣ አለቃውም 'ምን አለህ?' ሲለው ወታደሩም እንደምትመጣ እርግጠኛ ነበርኩ'፡፡ * እውነተኛ ጓደኛ ማለት ሁሉም ሠው ሲሸሽህ እሱ ግን የሚፈልግህ ነው!

Jabir  |  @WubTarikoch