Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ባል..!? ባለቤቴ ሴቶች ትምህርት ቤት ታስተምር ነበር። በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት አደር | ውብ ታሪኮች ®

ምርጥ ባል..!?

ባለቤቴ ሴቶች ትምህርት ቤት ታስተምር ነበር። በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት አደርሳት ነበር። ትምህርት ቤቱ በር ላይ ስደርስ ከመኪናው ወርጄ በሩን ከፍቼላት ትወርዳለች። ይህ ነገር ታዲያ ት/ቤቱ ውስጥ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።

የስራ ባልደረቦቿ ውይ ታድለሽ  ምን አይነት ፍቅር ነው፣ ምን አይነት እድለኛ ነሽ። ምነው እንዳንቺ ባል ባሎቻችን ቢሆኑ እያሉ ይቀኑባት ነበር። ተማሪዎቹ ሳይቀር ታድላ ይሏታል። ነገር ግን የመኪናው በር ተበላሽቶ ከውጭ እንጂ ከውስጥ እንደማይከፈት ከኔ ውጪ ሚያውቅ ሰው አልነበረም!

ባጭሩ አሁን እኔ ከአንድ ትምህርት ቤት የሶስት ሚስቶች ባል ነኝ። በሩን እስካሁን አላሰራሁትም። ይህ በር ለእኔ የእድል በር ሆኖልኛል።

achacher | @WubTarikoch