Get Mystery Box with random crypto!

አንዱ ወጣት ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ሥራ አጥቶ ቤት ተቀምጧል። እናቱ ደሞ ልጃቸው ተምሮ ሥራ አለማግኘ | ውብ ታሪኮች ®

አንዱ ወጣት ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ሥራ አጥቶ ቤት ተቀምጧል። እናቱ ደሞ ልጃቸው ተምሮ ሥራ አለማግኘቱ አሳዝኗቸዋል። አንድ ቀን እናት ምሥር እየለቀሙ ልጁ ምሳ ሊበላ ወደ ቤት ሲመጣ፣

"ልጄ ዛሬስ ሥራ አላገኘህም?"

"በእኔ ሞያ ሥራ አይገኝም"

"ለመሆኑ የተመረቅኸው በምን ሙያ ነበር?"

"ጂኦሎጂ ነው እማዬ"

"ምን ማለት ነው እሱ?"

"የአፈር ምርምር፣ ጠቃሚውን ማዕድን ከማይጠቅመው አፈርና ድንጋይ መለየት ማለት ነው"

"ጎሽ! ታዲያ እዚህ ምሥር ውስጥ ያለውን አፈርና ድንጋይ ልቀምልኛ! እኔም አይኔ እየደከመ መጥቷል"

Tesfaye H.mariam | @WubTarikoch