Get Mystery Box with random crypto!

ጥቁሩ አንበሳ..! ሳዲዮ ማኔ፡ 'ለሚትዝ ጋር ለመፈራረም እና ፈተናን ለመጋፈጥ ፈረንሳይ የደረስኩ | ውብ ታሪኮች ®

ጥቁሩ አንበሳ..!

ሳዲዮ ማኔ፡ "ለሚትዝ ጋር ለመፈራረም እና ፈተናን ለመጋፈጥ ፈረንሳይ የደረስኩባትን የመጀመሪያ ቀን አስታውሳለሁ። ከደረስኩበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ልምምድ ማድረግ ነበረብኝ ነገር ግን አሰልጣኙ እስኪደውልልኝ ድረስ ቤት ውስጥ እንድቆይ ነገረኝ።"

    "እኔም ፈረንሳይ መሄዴን ለእናቴ ደውዬ መንገር ብፈልግም ስልኬ ላይ ምንም ብር አልነበረኝም። ታዲያ በማግስቱ ሜትዝ ላይ ከነበሩ አንዳንድ ጓደኞቼ ጋር ካርድ ለመግዛት ሄድኩና ደወልኩላት። ሰላም እማ፣ ፈረንሳይ ነው ያለሁትም አልኳት።"

እሷም፦ “ምንድን የትኛው ፈረንሳይ ነው ምትለኝ” አለችኝ።

እኔም፦ "አላመንሽኝም እንዴ እማ? ፈረንሳይ አውሮፓ ነዋ" አልኳት።

"አውሮፓ? ምን ማለትህ ነው? ሴኔጋል አይደል እንዴ የምትኖረው፤ የአጎትህ ቤት መሆን አለብህ" አለችኝ።

እኔም፦ "አዎ። አሁን ግን አውሮፓ ውስጥ ነው ያለሁት አልኳት።… ይህ ለሷ እብደት ነበር። በጣም ተገርማ በየቀኑ እየደወለች እውነት እንደሆነ ትጠይቀኛለች። ስጫወት እንድታየኝ ብዬ ቲቪ እንድታይ እስከነገርኳት ቀን ድረስ አላመነችኝም ነበር። እኔም በመጨረሻም ህልሜ እውን መሆኑን ተረዳሁ።"

ከምንም ነገር የሚመጣ ምንም ነገር የለም። ለህልሞችህ መፋለም አለብህ።


Inah Abubeker | @WubTarikoch