Get Mystery Box with random crypto!

ባል እና ሚስት..! 1. ሮናልዶ በሚስቱ ጭቅጭቅ የተነሳ ወደ ድሮው መልኩ ተመልሷል። ሰሞኑን ጨዋ | ውብ ታሪኮች ®

ባል እና ሚስት..!

1. ሮናልዶ በሚስቱ ጭቅጭቅ የተነሳ ወደ ድሮው መልኩ ተመልሷል። ሰሞኑን ጨዋታው ሳያልቅ ወደ ቤቱ መመለሱ የገረመው ጋዜጠኛ ጠየቀው፣
" ሮናልዶ! ጨዋታው ሳይጠናቀቅ ቀድመህ ወደ ቤትህ ለምን ሄድክ?"

"ሚስቴ ጆርጂና ደውላ 'ካልተጫወትክ ወንበር ላይ ተቀምጠህ ምን ትሠራለህ? በ10 ደቂቃ ውስጥ ካልመጣህ ቤቱን እቆልፈዋለሁ' ስላለችኝ ነው''

2. ባል ከሚስቱ ኋላ እየተራመደ ሲሄዱ የሚስቱን መቀመጫ አየና "አንቺ! ቂጥሽ አድጎ አድጎ አሮጌ የልብስ ማጠቢያ ማሽን መስሎ የለም እንዴ?" ሲላት በጣም ተናዳ መልስ ሳትሰጠው ዝም አለችው።

ማታ ወደ ቤት ሲመለሱ አማረውና ጠጋ ብሎ ሊያሻሻት ሲሞክር እንዲህ አለችው "ትንሽ ልብስ ለማጠብ ብዬ አሮጌውን የልብስ ማጠቢያ ማሽን አላስነሳውም። በእጅህ ለማጠብ ሞክር"

3. የ70 ዓመት ሃብታም ሽማግሌ ሚስቱን እንዲህ አላት "እኔ የምልሽ? ወጣት ሴቶችን ሳሳድድ የማትናደጂው ለምንድነው?" ሚስት መለሰችለት ".. ለምን እናደዳለሁ? ውሾች እንኳን የማይነዱትን መኪና እየሮጡ ያሳድዱ የለ!" ባሻዬ! ሴቶችን ሥርዓት የሚያሲዝልን የአገር መሪ ጠፋ ማለት ነው?

Tesfaye H.mariam | @WubTarikoch