Get Mystery Box with random crypto!

የሆኑ ባልና ሚስት ወደ አንድ እንስሳት ማቆያ ፓርክ በአጋጣሚ ይሄዳሉ እንዳጋጣሚ አንድ ዝንጀሮ አብ | ውብ ታሪኮች ®

የሆኑ ባልና ሚስት ወደ አንድ እንስሳት ማቆያ ፓርክ በአጋጣሚ ይሄዳሉ እንዳጋጣሚ አንድ ዝንጀሮ አብራው ካለች ጓደኛው ጋር እየተጫወተ የነበረ ዝንጀሮ አገኙ ።

የሰውየው ሚስት እንዲህ አለች  “ምን አይነት ፍቅር  ነው ! እንዲህም አይነት አለ እንዴ ? አለች በመገረም! "

ከዚያም ወዲያው ዞዞር ማለት እንደጀመሩ  ሌላ አንድ ወንድና ሴት አንበሳ ጎን ለጎን ተለያይተው ተቀምጠው  አዩና........ ሚስትየዋ  “ፍቅር የሌለበት ምን አሳዛኝ ትዕይንት ነው አለች በማዘን "

ይህን የሰማው ባልተቤቷ እንዲህ አላት
“ያን ድንጋይ ወደ አንበሳይው ወርውሪና ተመልከቺ አላት ” እሷም ድንጋዩን አንበሳው ላይ ስትወረውር አንበሳው አንበሳይቱን ለመከላከል ሲጮኽ  አየች

ባልየውም ከዝንጀሮዋ ጋርም ድገሚው አላት እሷም ለአንበሳው እንዳደረገችው ድንጋዩን ወደ ዝንጀሮው ስትጥል ወንዱ ዝንጀሮ ዘሎ  ዛፍ ላይ  ወጣና ራሱን  ለማዳን ሴቷን ጥሎ ሄደ ።

ባሏም እንዲህ አላት “በምታይው ነገር አትታለይ ያየሺው ሁሉ ፍቅር አይምሰልሽ ፡፡ ብዙ ጊዜ ባዶ ልብን ለመደበቅ ሲባል የሚያታልል ገጽታ ወይም አስመሳይነት ይኖራል ፡፡
@WubTarikoch