Get Mystery Box with random crypto!

አንብቧትማ..! ሁለት የሚዋደዱ ጓደሞች ቁጭ ብለው ሳሉ አንደኛው ያማረ ቪላ ቤቶችን ያይና ለጓደኛ | ውብ ታሪኮች ®

አንብቧትማ..!

ሁለት የሚዋደዱ ጓደሞች ቁጭ ብለው ሳሉ አንደኛው ያማረ ቪላ ቤቶችን ያይና ለጓደኛዉ ፈጣሪ ይህን ሁሉ ሀብት ለእነዚህ ሰዎች ሲያድል እኛ የት ነበርን አለው። ጓደኛውም አጠገቡ ነበረና ና ብሎ ወደ ሆስፒታል ይዞት ሔዶ እንዲህ አለው...

ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ ፈጣሪ በሽታን ሲያድል እኛ የት ነበርን ? ከዚያም የታመመ ሰው በሆስፒታል ውስጥ የሞተውን ሰው ሬሳ ተመለከተ ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ እንኳ አልሞትኩኝ ምክንያቱም የሞተ ሰው ፈጣሪን አያመሰግንምና አለ"።

ዛሬ ስለ ሁሉም የፈጣሪን በረከቶች እና ምሕረት ለምን አናመሰግንም? ሕይወት ምንድን ነው ? ህይወትን በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ:

*1. ሆስፒታል *2. እስር ቤት *3. መቃበር
በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ ትገነዘባለህ። በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ። በመቃብር ውስጥ ሕይወት ምንም ዋጋ እንደሌለው ትገነዘባለህ።

የዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው። ስለዚህ ትሁት እና አመስጋኝ ሁን። ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪያችን የተመሰገነ ይሁን አልሀምዱ ሊላህ!!

@WubTarikoch