Get Mystery Box with random crypto!

ባሻዬ! ለ5ኛ ጊዜ ከቸርች ከተባረርኩ በኋላ በነጻ ዝውውር እንኳን የሚቀበለኝ ቸርች አጥቼ ነበር። | ውብ ታሪኮች ®

ባሻዬ!

ለ5ኛ ጊዜ ከቸርች ከተባረርኩ በኋላ በነጻ ዝውውር እንኳን የሚቀበለኝ ቸርች አጥቼ ነበር። ሰሞኑን ግን አንዱ ፓስተር ሊወስደኝ እያሽኮረመመኝ ነው። እስከዚያው ግን ለሁለት ሰዎች ምክር ያስተላለፍኩበትን ይህንን ጽሁፌን ልጋብዝህ።

1. አንድ የምናውቃት ሴት ለረጅም ጊዜ ባል ሳታገባ ቆየች። ይቺ ሴት በአንዱ ነብይ የውሸት ትንቢት ተጭበርብራ ዕድሜዋን እየቆጠረች ትገኛለች። ነብይ ነኝ ባዩ ከብዙ ዓመታት በፊት "አንቺ የምታገቢው ፓስተር መርዕድን (የሙሉ ወንጌል ፓስተር የነበረው) ነው ብሏት አንድም ቀን አይቷት የማያውቀውን ፓስተር መርዕድን ቁጭ ብላ ስትጠብቅ ፓስተር መርዕድ ሚስት አገባ።
በጣም የሚያሳዝነው ነገር ልጅቷ ፓስተር መርዕድ ሌላ ሚስት አግብቶም መጥቶ ያገባኛል ብላ አሁንም እየጠበቀች ነው።

አንቺ ሴት! መርዕድ የሚባል በስም ሞክሼ የሆነ ሰው መጥቶ ካላገባሽ በስተቀር ያኛውን መርዕድ በመጠበቅ ሳታገኚው ትሞታለሽ። ምክሬን ስሚ!

2. ባሻዬ! አንተ ደሞ "ሌሊቱን በከባድ ቅዠት አሳለፍኩ ፣ ክፉ መንፈስ አግኝቶኛል፣ ፓስተሬ ጋ ሄጄ እጁን ጭኖ ይፀልይልኝ" አትበለኝ። ሁሉም ቅዠት ከክፉ መንፈስ አይመጣም። እስቲ ብርድ ልብስህን አጥበህ ሞክረው። ያደፈ ብርድ ልብስ ሽታ ከባድ ቅዘት ያመጣል።

Tesfaye H.Mariam | @WubTarikoch