Get Mystery Box with random crypto!

አሁን ላይ ስለ ሁለት ትልቅና የተለያየ ገፅታ ያላቸው ሰዎች አንድ ነገር ልበላችሁ 1ኛዉ  ወጣቱ(F | ውብ ታሪኮች ®

አሁን ላይ ስለ ሁለት ትልቅና የተለያየ ገፅታ ያላቸው ሰዎች አንድ ነገር ልበላችሁ
1ኛዉ  ወጣቱ(Fire age)
2ኛዉ  አባቶቻችን(Old Guys)

ወዳጆቼ ምን አስተዋልኩኝ መሰላቹ እኛ ወጣቶች እኛ አዋቂ ነን፣እኛ ያልነዉ ልክ ነዉ፣ዘመናዊነት ዉስጥ ነን ብለን ዘራፍ እንላለን። አባቶቻችን ደሞ እኔ የህይወት ልምድ አለኝ ብዙ አስተምራኛለች አሳይታኛለች፣ ብዙ ወድቀን ተነስተናል ይላሉ።

አዉ ልክ ናቸዉ ባይ ነኝ ብዙ ነገሮችን ከነሱ እንማራለን። ወጣት ሆኜ የሰራሁትን ስህተት አንተ አንተ ደግመህ እንድትሰራ አልፈልግም ይሉናል...!!
አኔ እንዲህ ብናደርግ እላለዉ እኛ ወጣቶች የአባቶቻችንን ምክር ተቀብለን በስነ ምግባር አድምጠናቸዉ፣ እኛም ደሞ በኛ ጊዜ ስለተቀየረዉ ነገር ያልነበረዉ አሁን ላይ እንደተሻሻለ በእርጋታ ብናስረዳቸዉ ይቀበሉናል ብዬ አስባለሁ!!

እና ደሞ እኛም እድሜያቸዉ ገፍቷል ብለን አንናቃቸዉ። እነሱም ወጣት ነዉ ገና ነዉ ብለዉ አያታልሉን... ሁለቱም ፍፁም የተለያዩ የዕድሜ ክልል ባሉ ሰዎች መካከል ትልቅ መከባበርን፣ ፍቅርን እና ሰላምን ማስፈን ይቻላል።
 
ሙራድ ሙሀመድ | @WubTarikoch