Get Mystery Box with random crypto!

አብሮ አደግ ጓደኛዬ ከአንድ ወር በፊት ሊያገባ እንደሆነ እና እንዳጅበው ደውሎ ነገረኝ። በስራ ምክ | ውብ ታሪኮች ®

አብሮ አደግ ጓደኛዬ ከአንድ ወር በፊት ሊያገባ እንደሆነ እና እንዳጅበው ደውሎ ነገረኝ። በስራ ምክንያት የሰርጉ ቀን ወደሌላ ቦታ ተንቀሳቅሼ ሳልሄድ ቀረሁ፡፡ ከተመለስኩ በኋላ መንገድ ላይ ሳየው ሀፍረት እየተሰማኝ ባላየ ማለፍ ጀመርኩ።
በጣም ሲደጋገም የሆነ ስጦታ ገዝቼ ቤቱ መሄድ አንዳለብኝ ወሰንኩ።

ከመሄዴ በፊት ቤት መሆኑን ማረጋገጥ ስለነበረብኝ ደወልኩለት!

" ቤት ነህ እንዴ ሀቢቢ?" "አዎ ቤት ነኝ!" አለኝ
"ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ቤት እመጣለሁ ጠብቀኝ" አልኩት
"እሺ ግን በሰላም ነው?" አለኝ
"አዎ በሰላም ነው ለሰርግህ ስላልመጣሁ ዛሬ ካንተ ጋር ላሳልፍ ብዬ ነው"
"አሽሙር መሆኑ ነው? አለኝ
"ማለት አልገባኝም!" አልኩት
"ካንተ ግን ይሄን አልጠብቅም" ብሎ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ዘጋው!

ቆይቼ ከጓደኞቹ ሳጣራ ጀለስ ከሚስቱ ጋር ተፋቷል ;) Ebad


@WubTarikoch