Get Mystery Box with random crypto!

ልጅቷን ለምን ሳምካት..? በእድሜ የገፉ አባት ናቸዉ ከሁለት ወጣት ልጆቻቸዉ ጋር ሲኖሩችግር ይገ | ውብ ታሪኮች ®

ልጅቷን ለምን ሳምካት..?

በእድሜ የገፉ አባት ናቸዉ ከሁለት ወጣት ልጆቻቸዉ ጋር ሲኖሩችግር ይገጥማቸዋል :: ወንዱን ልጅ ስራ እንዲሰራ ይልኩታል ከመሔዱ በፊት ሊመክሩት ፈለጉና ''ልጄ ሆይ ስለ እህትህ ስትል አሏህን ፍራ አሉት:: አልገባዉም እህቱ አብራዉ አትሔድ ..ምን ለማለት ፈልገዉ እንደሆነ ሳይገባዉ ሳይጠይቅ ተሰናብቷቸዉ ሄደ:: ስራዉን ጨርሶ ሲመለስ አባት ልጄ ሆይ! ለምን ያቺን ልጅ ሳምካት አሉት ።

አባቴ አረ ማንንም አልሳምኩም አላቸዉ። ''በጭራሽ ስመሃታል!'' ብለዉ ሲያፋጥጡት አባቴ ማንም አላየንም ጨለማ ዉስጥ ነበርን ከአሏህ ዉጪ ማንም አልተመለከተንም ማን ነገረህ? ዋህይ(ራዕይ) ወረደልህ? እንዴት አወክ ብሎ ሲጠይቃቸዉ..

በሩን ከፍቼ ቤት ዉስጥ ቁጭ ብዬ ነበር ዉሀ ቅጂዉ ዉሀ ይዞ መጣ እህትህ ከፈተችለት ዉሃዉን ከገለበጠ በኃላ ሊወጣ ሲል እህትህን ግጥም አድርጎ ሳማት ያኔ አንተም የሰዉ እህት እንደሳምክ አወኩ ወደ ሌላ እንቅስቃሴ ብትገባ ዉሀ ቅጂዉም ወደሌላ እንቅስቃሴ ይገባ ነበር፡፡

በሰዉ እህት ሚቀልድ በእህቱ ይቀለዳል
• በሰዉ ልጅ ሚቀልድ በራሱ በልጁ ይቀለዳል
.በሰዉ ሚስት ሚቀልድ በራሱ ሚስቱ ይቀለዳል
« በሰዉ ልጅ በሰዉ ሚስት በሰዉ እህት ዝሙት የሚፈጽም እዳዉን በቤተሰቡ ይቀበላል፡፡ ዝሙት እዳ ነዉ ካበደርከዉ በቤተሠብህ ብድሩን ትቀበላለህ።

*ሁሉም ሰው የዘራውን ያጭዳል በራስህ ላይ (በቤተሰብህ) ላይ ሊደረግ የማትፈልገውን ነገር በሌሎች ላይ አታድርግ። በሌላ ሴት ላይ የምሰራዉ ስራ አንተ ሳታቅ በእህትህ ላይ እንደሚሰራ እወቅ የሌሎችን ሴቶች መብት ስትጠብቅ የአንተም እህት መብት ይጠበቃል፡፡

@WubTarikoch