Get Mystery Box with random crypto!

የሴት እንባ..! አንዲት ቆንጆ ልጅ ለቅሶ ላይ ስታለቅስ አየኋት፡፡ እንባዋ ሲወርድ በያዘችው ሶፍ | ውብ ታሪኮች ®

የሴት እንባ..!

አንዲት ቆንጆ ልጅ ለቅሶ ላይ ስታለቅስ አየኋት፡፡ እንባዋ ሲወርድ በያዘችው ሶፍት ስትጠርገው ሶፍቱ ቡና ዓይነት ቀለም ያዘ፡፡ ለካስ የተቀባቸው ሜካፕ እየለቀቀ ነበር።

ባሻዬ! ከዚህ በፊት የነገርኩህን ዛሬም እደግመዋለሁ፡፡ ወንድ ልጅ ሴትን ማስለቀስ የለበትም ። እንደ ሴት ልጅ እንባ ውድ ነገር የለም፡፡ ሴትን ካስለቀስካት ብዙ ወጪ ታስወጣሃለች፡፡ ይኸውልህ አንዲት ዘለላ እንባ ከሴቷ ዓይን ስትወርድ በመጀመሪያ ሎሪያል ከተባለው የዓይን ኩል ጋር ይቀላቀላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ Loreal Eye Liner ዋጋው 2100 ብር ነው፡፡ ከዚያም ዓይኗ ላይ ያለውን ሬቭሎን ማስካራ ያበላሸዋል። የአንድ ሬቭሎን ማስካራ ዋጋ 2300 ብር ነው፡፡

እንባዋ ከዓይኗ ወርዶ ጉንጫ ላይ ሲደርስ ፋውንዴሽኗን ያገኘዋል፡፡ የአንድ Lauder Foundation ዋጋ 2400 ብር ይገመታል። ከዚያም የተቀባችውን Zaron Blush ያበላሸዋል። የዚህም ዋጋ 2700 ብር ይሆናል። ከዚያም እንደ ፊቷ ከለር የምትቀባው ማክ ፓውደር በእንባዋ ምክንያት ቡኒ ቀለም I ሠርቶ በፊቷ ላይ ሲወርድ ይበላሻል። የአንዷ ብልቃጥ ማክ ዋጋ አሁን 5400 ብር ደርሷል።

በመጨረሻም እንባዋ ተንከባሎ ከንፈሮቿ ጋ ሲደርስ ከኤልዛ ሊፕስቲክና ከተደራቢው Avonlip Gloss ጋር ተቀላቅሎ ለሁለቱም የ 4400 ብር ኪሣራ ያስከትላል።

ባሻዬ! በድምሩ ተባበረኝ እባክህ፡፡ አንዷ ጠብታ የሴት እንባ በድምሩ 19300 ብር ያስወጣሃል።

ባሻዬ! እባክህ ሴትን ልጅ አታስለቅስ። እሷ ከምታለቅስ አንተ ብታለቅስ ይቀላል፡፡ ያንተ የቫዝሊን ዋጋ 13 ብር ከሃምሳ ሣንቲም ብቻ ነው።

ተስፋዬ ኃ.ማርያም | @WubTarikoch