Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi_merej
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.68K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-10-10 07:45:36
ለፈተና ሄደው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለወለዱ ተፈታኞች በቀጣይ እንደመደበኛ ተማሪ እንዲፈተኑ ዕድል ይሰጣቸዋል ተባለ

በእርግዝና ላይ ላሉ እና ወልደው ህጻንን ጡት እየመገቡ ላሉ ለተመዘገቡ ሴት የ 12ኛ ክፍል ተፈታኞች የእነርሱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የመፈተኛ ስርዓት በቀጣይ ተዘጋጅቷል ሲል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታዉቋል፡፡

በዚህም መሰረት አገልግሎቱ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሚሰጠው ፈተና ተፈጣኝ ወላዶች መፈተን አያስፈልጋቸውም ማለቱን ብስራት ራዲዮ ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ይህም ከወራት በፊት ከወረዳ ደረጃ አንስቶ ገለጻ ተሰጥቷል፤መመሪያም ሆኖ ወርዷል ብሏል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፡፡

ሆኖም ለመፈተን ወደዩኒቨርሲቲ ከመጡ ተፈታኞች መካከል ወደ ተቋማቱ እንደደረሱ የወለዱ እንዳሉ ሪፖርት ደርሶናል ያለ ሲሆን ስለሆነም እነዚህ ወላድ ተፈታኞች የቤተሰብ እንክብካቤና ፈተናውን ለመፈተንም አካላዊ ማገገሚያ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው እሙን ነው፡፡ በመሆኑም በቀጣይ እንደመደበኛ ተማሪ እንዲፈተኑ አገልግሎቱ ዕድል የሰጣቸው መሆኑ ታውቆ ቀድሞ በተላለፈው መመሪያ መሠረት በመጀመሪያው ዙር መፈተን የማይችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ሲል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታዉቋል፡፡
ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
2.8K views04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 20:23:31
ጁንታው በስምንት ወራቱ የትግራይ ህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት ደብቆት የነበረውና በድንቆቹ የኢትዮጵያ ጥምር ጦር መሃንዲሶች እንዳይጠቀምበት ተደርገው የነበሩት ሚሳኤሎች፣ ረዥም ርቀት ተወንጫፊ ሮኬቶች፣ የራዳር መቆጣጠሪያዎች፣ ከባባድ የጦር መኪኖች፣ ታንኮች፣ መድፎች፣ ለመቁጠር ሳይሆን ለማየት የሚታክቱ የልዩ ልዩ መሳሪያዎች ተተኳሾች ተይዘዋል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
3.2K views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 06:25:11
" ስልክ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት  የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባታቸውን ገልጿል።

የተከለከሉ ነገሮችን ማንም ተፈታኝ ይዞ እንዳይገባ ከወረዳ ጀምሮ ገለጻ ተደርጓል ያለው አገልግሎቱ ከዚህ በተጨማሪ አካላዊ ፍተሻ ተደረጓል ሲል አሳውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የተለያየ የማጭበርበሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም የተከለከሉ ነገሮችን በተለይም ተንቀሳቃሽ #ስልክን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ገልጿል።

ድርጊቱ #ከፍተኛ_የፈተና_ደንብ_ጥሰት በመሆኑ ውሳኔው ከሁሉም ፈተና የሚሰረዙ ይሆናል ሲል አሳውቋል።

በተመሳሳይ ከዚህ በኃላም የተከለከሉ ነገሮችን መፈተኛ ማዕከላት (የኒቨርሲቲ) ግቢ ውስጥ ማንኛውም ተፈታኝ ይዞ ቢገኝ ከሁሉም ፈተና የሚሰረዝ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ገለጻውን ባለመቀበልና አካላዊ ፍተሻዎችን በማጭበርበር ስለፈጸመው ጉዳይ ተጨማሪ ህጋዊ ምርመራ የሚካሄድ ሲሆን እንደግኝቱም ተመጣጣኝ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል ሲል አስጠንቅቋል።

ፈተና የሁሉም ማህበረሰብ ሀብት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለፈተና ደህንነትና ፍትኃዊነት የበኩሉን አዎንታዊ ድርሻ እንዲወጣ ሲልም አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
3.7K views03:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 18:50:04
#ጅቡቲ ጦሯን ወደ ኤርትራ ድንበር አስጠጋች
ዛሬ ማለዳው ጀምሮ የጅቡቲ መከላከያ ጦር ኃይሎች ወደ ኤርትራ አዋሳኝ ድንበር በታንክ የታጀበ ሰራዊቷን በማስጠጋት በኤርትራ ወታደሮች ተፈፅሞብኛል ያለችውን አፀፋ ለመመለስ ያቀደ እንቅስቃሴን መጀመሯን ምንጮች ገልፀዋል
ከዚህ በተጨማሪ ህወሃትም ወደ ኤርትራ ድንበር ሰሞኑን ሀይል ማስጠጋት ጀምሯል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
1.3K views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 18:35:05 ህወሃት ካሉት ግምባሮች ማለትም ከአፋር በርሀሌ፣ ከማይጠብሪ ከመቀሌ ደግሞ ከኩያ ከአድዋ ወደ ራያ ተጨማሪ ሀይል አስገብቷል።
በመተማ እና በበአከር በኩል ከሱዳን የተነሳ የሳምሪ ሀይል እየተጠጋ መሆኑ ታዉቋል።  ጥምር ጦሩ ተዘጋጅቶ እየጠበቀ ነው አላማዉ ወልቃይትን መያዝ ነው።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
1.4K views15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 18:17:35
#UNHRC

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ኮሚሽን የሥራ ጊዜ ለአንድ ዓመት ተራዝሟል ፤ የስራ ጊዜው የተራዘመው ትላንት አጄኔቫ ውስጥ የተመድ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ም/ቤት አባላት ውሳኔውን በተመለከተ በሰጡት ድምጽ ነው።

የውሳኔ ሀሳቡ ጠባብ በሆነ የድምፅ ልዩነት ነው ተቀባይነት ያገኘው።

47 አባላት ካሉት የምክር ቤቱ አባላት መካከል የመርማሪ ቡድኑን ሥራ መቀጠል 21 ሀገራት ሲደግፉት 19ኙ ተቃውመውታል።

ከማላዊ " ድምፀ ተአቅቦ  " በስተቀር የምክር ቤቱ አባል የሆኑ ሁሉም የአፍሪካ አገራት ውሳኔውን ተቃውመውታል።

የደገፉ ፦

- አርጀንቲና
- አርሜኒያ
- ብራዚል
- ቼክ ሪፐብሊክ
- ፊንላንድ
- ፈረንሳይ
- ጀርመን
- ሁንድራስ
- ጃፓን
- ሉቱንያ
- ሉክዘንበርግ
- ማርሻል አይላንድስ
- ሜክሲኮ
- ሞንቴኔግሮ
- ኔዘርላንድስ
- ፓራጓይ
- ፖላንድ
- ኮርያ ሪፐብሊክ
- ዩክሬን
- ዩናይትድ ኪንግደም
- አሜሪካ

የተቃወሙ ፦

- ቤኒን
- ቦሊቪያ
- ካሜሮን
- ቻይና
- ኮትዲቯር
- ኩባ
- ኤርትራ
- ጋቦን
- ጋምቢያ
- ህንድ
- ሊቢያ
- ሞሪታንያ
- ናሚቢያ
- ፓኪስታን
- ሴኔጋል
- ሶማሊያ
- ሱዳን
- ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ
- ቬንዙዌላ

ድምፀ ተአቅቦ ፦

- ኢንዶኔዥያ
- ካዛኪስታን
- ማላዊ
- ማሌዥያ
- ኔፓል
- ኳታር
- ሁዝቤክስታን

የውሳኔ ሀሳቡን መፅደቅ ተከትሎ በተ.መ.ድ. የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ፅ/ቤት (ጄኔቫ) ባወጣው መግለጫ ፤ የውሳኔ ሀሳቡን የተቃወሙ እና አጋርነትን ላሳዩ ፣ የድምፀ ተአቅቦ ላደረጉ የም/ቤት አባላት ምስጋና አቅርቦ ፤ በሰጡት ድምፅ ጣልቃ ገብነትን፣ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ማተራመስንና ማደፍረስን ነው የተቃወሙት ብሏል።

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
1.5K views15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 12:10:34
ቶማስ ሳንካራ እና ኢብራሂም ትራኦሬ

ቶማስ ሳንካራ በ34 አመቱ በመፈንቅለ መንግስት የቡርኪናፋሶን መንበረ ስልጣን ያዘ። ለውጥ አቀንቃኝ እና ፀረ ኮሎኒያሊስት ነበረ። ፈረንሳይ በሴራ አስገደለችው።

"ሻምፓኝን ለጥቂቶች፤ ወይም ንጹህ የመጠጥ ውሃ ለሁሉም፡፡' ከሁለት አንዱን መምረጥ አለብን"
በሚል ንግግሩ ይታወቃል።

በዚህ ሳምንት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ላይ የወጣው ኢብራሂም ትራኦሬ 34 አመቱ ነው። እንደ ቶማስ ሳንካራ ሁሉ ወታደር ነው፣ የፈረንሳይ በሀገሩ ጉዳይ ጣልቃ ገብነትን ይቃወማል። ለደሀው እቆማለሁ እያለ ነው። የወጣቱን ልብ እየገዛ ነው።

ጥያቄው እንደ ቶማስ ሳንካራ በሀገሩ ልጆች ተከድቶ ይገደላል ወይስ የቶማስ ሰንካራን ራዕይ ያስቀጥላል?
ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
2.3K views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 16:16:58
ተጀመረ

Safaricom ከች ብሏል

አማራጭ ተገኘ

እስቲ የዋጋ ሂደቱ ምነኛ ለተጠቃሚ
ቅናሽ ይሆን አስረዱን። ምነኛ ዝቅ ብላችሁ ይሆን አሳውቁን።

ተወዳዳሪ ሲኖር ሸጋ ነው
በመሀል ህዝቡ ተጠቃሚ ይሆናል።

ናይጄሪያ 6 አማራጭ አይችያለሁ
ሰዉ እንደአቅሚቲ በተመቸው ይጠቀማል።

ሳፋሪኮም የተባለው የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ዙሪያ በሚገኙ አስር
ከተሞች የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን ያካሄደው ሳፋሪኮም ዛሬ በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል።

የአዲስ አበባ 07 ኔትወርክ ደንበኞች የ4G ዳታ፣ የድምፅ ጥሪ እና የጽሁፍ መልዕክት አገልግሎቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ደንበኞች 700 ላይ በመደወል የሳፋሪኮም የጥሪ ማዕከልን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤ አገልግሎቶቹም በ5 ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሱማሊኛ፣ ትግሪኛ እና እንግሊዝኛ የሚሰጡ ይሆናል ተብሏል።

እናመሰግናለን !! በርቱልን

➨እስቲ እኛም እጃቸው ከምን መሆኑን እናጤናለን። ያው ለተጠቃሚው ምነኛ ቅናሽ ይሆን።

ጉዞ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ወደፊት ይሁን !



መ/ር አካሉ አብራሐም

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
2.1K views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 13:31:08
አዲስ አበባ

ከቀጨኔ ወደ መነን በሞተር ሳይክል በተደጋጋሜ ጊዜ ህዝብን ያማረሩ ሌቦች ከነ ሞተራቸው ተይዘዋል።
ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
2.3K views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 12:57:30
ሳፋሪኮም በአዲስ አበባ የቴሌኮም አገልግሎት በይፋ አስጀመረ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሳኡሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፣  ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የቴሌኮም ኩባንያ በርካታ ቅድመ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ሳፋሪኮም ትልቅ ሚና ይኖረዋል ያሉት ስራ አስፈጻሚው፣ ከባለድርሻ አካላትና ከክልሎች ጋር በጋራ በመስራት በሁሉም ቦታ ተደራሽ ለመሆን እንሰራለን ብለዋል። የሳፋሪኮም ቴሌኮምኒኬሽን ኢትዮጵያ ምርቃት ስነስርዓት ላይ ለመታደም የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶም  አዲስ አበባ መግባታቸው ተሰምቷል።

ሳፋሪኮም ለደረሰበት ደረጃ የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮ ቴሌኮም እገዛ ትልቅ መሆኑን በመግልጽ አመስግነዋል።  ኩባንያው ባለፉት ሳምንታት በድሬዳዋ፣ በባህርዳር፣ በአወዳይ፣ ጎንደር ፣ሞጆ፣ ሐረር፣ አዳማ፣ ሀረር፣ ቢሾፍቱና ደብረ ብርሃን የኔትዎርክ ሙከራ አገልግሎቱን መጀመሩ ይታወሳል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
120 views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ