Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi_merej
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.68K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-11-11 07:15:24
ፖለቲከኛ ጀዋር መሐመድ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠው አስተያየት እንደሚከተለው በአማርኛ በወቅታዊ መረጃ ይቀርባል።
#wektawi_Mereja
እውነት ለመናገር ባለፉት አራት አመታት የተገደሉት የኦሮሞ ልጆች ቁጥር በወያኔ እና በደርግ ዘመን ሁለቱ ተደምረው የአሁኑ ይበልጣል። ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀያቸው ተፈናቅለው በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ።  ኦሮሚያን ለማልማት የተማሩ ወጣቶች ታጥቀው እርስ በርስ እየተገዳደሉ ነው።  ይህ ለመናገር የሚሳፍር ነው።

ዛሬም እንደትናንቱ እንጮሃለን፣ የዚህ ጦርነት መነሻ የፖለቲካ ግጭት ነው። በውይይት እንጂ በመድፍ አይፈታም። በሰሜን እንዳየነው ይህ ጦርነት የቱንም ያህል ቢቆይ በድርድር ይጠናቀቃል። ለማይቀር ነገር ደሆችን አትጨርሱ።

በሰሜን ያለውን የኢትዮጵያን ችግር በሰላማዊ መንገድ እንፈታዋለን በኦሮሚያ ያለው በጦር እናስወግደዋለን ማለት ራስን ማታለል ነው። የቤቱን አንድ ጎን በማቃጠል ከሌላው ጎን መስራት የማይሆን ነገር ነው።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
1.2K views04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 16:12:26
#Tigray , #Mekelle

የፕሪቶሪያውን #የሰላም_ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ በምግብ እና ሸቀጦች ላይ የታየው ቅናሽ (በቀዳማይ ወያነ ገበያ) ፦

- ሰርገኛ ጤፍ 11,000 ብር ይሸጥ የነበረው አሁን ከ6,000 እስከ 6,500 እየተሸጠ ነው።

- ነጭ ጤፍ 14,000 እስከ 13,500 ይሸጥ የነበረው አሁን 10,000 ብር እየተሸጠ ነው።

- የስንዴ ዋጋ በኩንታል ከ10 ሺህ ብር ወደ 7 ሺህ ብር ቀንሷል።

- ለአንድ ኪሎ ግራም 700 ብር የነበረው በርበሬ አሁን 500 ብር ገብቷል።

- ዘይት 1,700 እና 1,800 የነበረው ወደ 1,400 ቀንሷል። 5 ሊትር ዘይት 2,100 የነበረው በአንድ ጊዜ ወደ 1,500 እና 1,450 ብር ገብቷል።

- ፉርኖ ዱቄት በኩንታል እስከ 13,000 ብር የነበረው ወደ 9,000 ብር ወርዷል (እንደ የጥራቱ)።

- ስኳር አንድ ኪሎ 270 የነበረ 160 ገብቷል።

- 25 ኪሎግራም መኮሮኒ 2,700 ብር ሲሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን 1,800 ብር እየተሸጠ ነው።

- አንድ ፓስታ ከ130 ብር ወደ 60 ብር ቀንሷል።

- አንድ ኪሎ ኦቾሎኒ ከ370 ብር ወደ 160 ብር ቀንሷል።

(ሽኩርት ፣ ቲማቲም ፣ ድንች ዋጋ ላይ ለውጥ የለም።)

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
651 views13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 10:30:48
Good News : ትግራይ ቲቪ በለውጥ ላይ ትግራይ ቲቪዎች በርቱ ሰሳም ለኢትዮጵያ ሰላም ሁለት አመት ፍዳውን ለበላው ህዝብ

እነ ፀረ- ሰላም  ና ጭር ሲል አልወድም መንገድ ዘጊ ዲያስፖራ ተጋሩዎች ቢያንስ ከዚህ ትምህርት ውሰዱ ህዝቡን ሰላም ስጡት !!!

#EthiopiaPrevailed

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
1.6K views07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 10:17:37
በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሃ መካከል የተደረሰው ሥምምነት በኢትዮጵያ የመደራደር አቅምና በብዙ ባለድርሻ አካላት ጥረት እንጅ በሌላ ሃይል ተፅዕኖ የመጣ ያለመሆኑ ሊታወቅ ይገባዋዋ። 

ለኢንባሲ ተወካዮችና አምባሳደሮች ማብራሪያ የሰጡት አምባሳደር ሴዲዋን ሁሴን አሜሪካ ህወሓት ላይ ጫና በማሳደር  ወደ ሥምምነት እንዲመጣ አግዛናለች ማለታቸው ለፅንፈኞቹ አጀንዳ ሆንዋል። የአሜራካ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ስለዚህ ተጠይቀው ሥምምነቱ ላይ ጫና አልፈጠርንም ፤ የእኛ ሚና መታዘብና   ተፈፃሚ እንዲሆን ማገዝ ብቻ ነው ብለዋል።   ይህ ሥምምነት በኢትዮጵያ አቅምና ጥረት እንዲሁም  በመንግስት ውሳኔ እንጅ የማንም ሀይል ተፅዕኖ ያመጣው እንዳልሆነ መታወቅ አለበት። ኢትዮጵያ በራሳ ችግሯን ለመፍታት የሔደችበት ርቀትና  ብልሃት የወለደው ድል ነው።  ነገር ግን አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በድርድሩ የተሳተፉት ዶ/ር ጌታቸው ጀንበርና ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞጢዮንስ አንዳንድ ማብራሪያዎችን ጨምሮ መንግስት ስምምነቱን ለመፈፀም ያለውን ቁርጠኝነት ለህዝብ በሚዲያ ሊያብራሩ ይገባል።  ኢትዮጵያ አሸናፊ የነበረች አሁንም የአሸናፊዎቾ ሀገር ናት!

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
1.7K views07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 17:31:37
"እያንዳንዱ እርምጃችን፣ እያንዳንዱ ድርጊታችንና የምንፈርማቸው እያንዳንዱ ስምምነቶች የትግራይን ሕዝብ ፍላጎት የሚያረጋግጡ ናቸው። ህዝቡ ከምንም ነገር በላይ የሚፈልገው ሰላም ነው" ጌታቸው ረዳ ዛሬ የፃፈው

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
1.7K views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 13:29:02
መረጃ!

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አመራሮችና እና የህወሀት ወታደራዊ አመራሮች በኬኒያ ናይሮቢ ከተማ ዛሬ ውይይት እያደረጉ ነው።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የህወሓት ባለስልጣናት የትግራይ ታጋዮችን ትጥቅ መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየተወያዩ ነው። ስብሰባው አሁን እየተካሄደ ነው።
ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
2.3K views10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 21:22:36 Update ወለጋ
****
የነቀምት ከ
ተማ በኦነግ ሸኔ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውላለች። በከተማ የሚገኙ ባንኮችም ሙሉ በሙሉ ተዘርፈዋልም ወድመዋልም።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
3.1K views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 20:36:13
ድምፃዊ አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

እዉቁ እና ተወዳጁ የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ ድምፃዊ አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ባወጣዉ የሀዘን መግለጫ አስታዉቋል።

@wektawi_Merej በአርቲስቱ ህልፈተ ህይወት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
3.2K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 15:11:13
ጠ/ሚ አብይ አህመድ  ግብፀ ሻርም አልሸይክ  ገቡ ።

የመንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ግብፅ፣ ሻርም አል-ሼይክ ገብተዋል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
1.3K views12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 13:45:36
የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቀጣይ ወደ ትግራይ ክልል በመሄድ ህዝቡን እንደሚያወያይ ገለጸ

በቀጣይ ተግባራችን የሚሆነው ወደ ትግራይ ክልል ሄደን ሕዝቡን እስከታች ድረስ ማወያየት ነው ሲሉ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ መስፍን አርአያ (ፕ/ር) አስታወቁ።

ሰብሳቢው እንደገለጹት፤ መላው ኢትዮጵያውያን የተሳካ የምክክር ሂደት እንዲያከናውኑ የትግራይ ሕዝብ ተሳታፊነት አስፈላጊ ነው።

የፌዴራል መንግስትና ሕወሓት ያደረጉት የሠላም ስምምነት እኛም ቀድመን ስንፈልገው የነበረው ጉዳይ ነው ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም አገራዊ ምክክሩን በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል። ወደፊት  ኮሚሽኑ በክልሉ ከሚገኘው ሕዝብ ጋር አስፈላጊውን ውይይት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል።

የምክክር ኮሚሽኑን ቀጣይ ስራዎች የተሳለጠ ለማድረግ በተለያዩ ክልሎች ከሚገኙ የአስተዳደር አካላትና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።በትግራይ የሚገኘው ሕዝብም የእኛው ሕዝብ ነው ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ በአገራዊ የምክክር ሂደቱ ውስጥ ሕዝቡም ተሳታፊ እንዲሆንና ሃሳቡን መቀበል ያስፈልጋል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
1.6K views10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ