Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi_merej
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.68K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-09-28 00:15:10
" እስካሁን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰው የለም፤ ነገር ግን አንድ ሐኪም ቃል እንዲሰጥ ተደርጎ ተለቋል። " - የአዲስ አበባ ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አስክሬን ምርመራ እንደተጠናቀቀ ውጤቱ ለህዝብ ይገለፃል ሲል አሳውቋል።

ማምሻውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰን ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል፤  " ማዲንጎ ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 17/2015 ዓ.ም. ጠዋት 1፡30 አካባቢ ለሐኪሙ ስልክ እንደደወለና ወደ ክሊኒክ መሄዱን ፖሊስ ተረድቷል። " ብለዋል።

ከዚያም በኋላ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወደሚገኘው አንድ የግል ክሊኒክ በመሄድ የህመም ማስታገሻዎችን እና ሌሎች መድኃኒቶችን ወስዶ እንደነበር ተናግረዋል።

ማዲንጎ ሕይወቱ ያለፈው ረፋድ 3፡00 ሰዓት አካባቢ መሆኑን ገልፀዋል።

የድምጻዊ ማዲንጎ አስክሬን ሕይወቱ ካለፈበት የግል ክሊኒክ ወደ አቤት ሆስፒታል ተወስዶ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር ማርቆስ " ፖሊስ በቀረበለት አቤቱታ መሠረት የድምጻዊውን ሞት መንስኤ ለማወቅ የአስክሬን ምርመራ ውጤቱን እየተጠባበቀ ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።

ምርመራው እንደተጠናቀቀ ውጤቱን ፖሊስ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ሲሉ አክለዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ከማዲንጎ ህልፈት ጋር በተያያዘ ህክምና ካገኘበት ክሊኒክ ሠራተኞች ታስረዋል ስለሚባለው ጉዳይ ም/ኮማንደር ማርቆስ " እስካሁን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰው የለም፤ ነገር ግን አንድ ሐኪም ቃል እንዲሰጥ ተደርጎ ተለቋል " ሲሉ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
86 views21:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 17:00:57
ጠ/ሚ አብይ አህመድ በድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተከታዩን መልዕክት አጋርተዋል።

"አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ በማረፉ የተሰማኝ ኀዘን ከባድ ነው። ለሀገሩ በአጭር እድሜው ብዙ የሠራ ከያኒ ነው። ሀገር በተደፈረች ጊዜ ሕመሙን እየቻለ ግንባር ተገኝቶ ሠራዊቱን አጀግኗል። ሠልጣኞችን አበርትቷል። ነፍሱ በሰላም ትረፍ።"

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
2.3K views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 16:44:30
ማዲንጎን አፈወርቅ ትላንት ምሽት ክለብ ስራ ላይ ነበር። ዛሬ ጠዋትም ወደአንድ ክሊኒክ የሄደው መኪናውን እየነዳ ነው። ክሊኒኩ ውስጥ ከገባ በኋላ ግን እስትንፋሱ በመቆሙ በኦክስጂን ጭምር ለማትረፍ ተሞክሮ አልተሳካም። አሁን አስከሬኑን ይዘን ወደሚኒሊክ ሆስፒታል እየሄድን ነው። ተጨማሪ መረጃ እነግራችኋለሁ።
የቅርብ ጓደኛው ለዘሐበሻ የላከው

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
2.3K views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 00:33:24
#እንድታውቁት

ከአዲስ አበባ ፖሊስ ፦

1ኛ. በከተማ ደረጃ የደመራ ስነ-ሰርዓት ወደ ሚከናወንበት መስቀል አደባባይ ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ ስፍራዎች የጦር መሳሪያ ፣ ስለታም ነገሮችን እና ህገወጥ ቁሳቁሶችን ይዞ መምጣት የተከለከ ነው።

2ኛ. ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር ሁሉም ህብረተሰብ ተገንዝቦ የተለመደ ትብብሩን ሊያደርግ ይገባል።

3ኛ. በመስቀል አደባባይ የሚካሄደው የደመራ ፕሮግራምን መጠናቀቅ ተከትሎ በከተማው በተለያዩ ደብሮች እና መንደሮች ደመራ የማብራት ስነ-ስርዓት የሚካሄድ ሲሆን  በየአካባቢው ደመራ ሲበራ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደረግ ይገባል። በማንኛውም ሁኔታ ርችት መተኮስ ፍፁም ክልክል ነው።

የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እንዲሁም 0111110111፣ 0111264359፣ 0111010297፣ መጠቀም ይቻላል።

የሚዘጉ መንገዶች #ማስታወሻ : https://t.me/tikvahethiopia/73882?single

#AddisAbabaPoliceCommission
ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
1.7K views21:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 21:02:53 * 77 ----79 አለህ 79-79-97-97
* አለሁ አለሁ 79 አጠገብህ አለ-
* አዎ ከኔጋ አለ
* እንደዚህ ተጠቀሙና 98 እየፈለጋቹሁ ነው
* እሺ 64 አለህ
89 አለህ
65 አለህ
እሺ 77ስ አለህ

*አለሁ
*79 አለህ
*አለሁ
*ለ99 እነግረዋለሁ ስሙኝ ትላንት የተደረገ መጥፎ ነገር ሁላቹሁም እንድታውቁት ነው::
*እሺ
* ከአንድ ቤት 4 ዶሮዎችን አርደው በልተው -
ሁለት ሞባይል
ጨውና በርበሬ
ልብሶች ዘርፈው ሂደዋል ::እሄ የምነግራቹሁ ከአንድ ቤት ብቻ ነው ::

ሸለቆው አከባቢ ያሉ ቤቶችን በሙሉ እየበረበሩ ነው::ስለዚህ እየመራን አይደለንም አካሄዳችንም በደምብ አድርገን እንፈትሽ ይሄ አደጋ ነው በጣም አደገኛ ነው ::

በጣም የሚያስገርም ነው ከአንድ ቤት ትላንት ከእግሩ ላይ ጫማውን አስወልቀው የወሰዱ ታጋዮችም ጭምር አሉ ::
ትላንት ሙሉ ቀን ነው ቤቶቹ ሁሉ እየበረበሩ የዋሉት::
የሰው ሃይላችሁን ዙራቹሁ አረጋግጡ አለበለዝያ እኔ እያዞርኩ እርምጃ እወስዳለሁ ::

እቺን አሁን ተግብሯት እየዞራቹሁ ::

ይሄ 98 ተረድተሀኛል 89 ተረድተሀኛል 65 ተረድተሀኛል 94 ተረድተሀኛል እሺ 79
- ተረድቸሃሁ
ቤቶቹ ሙሉ በሙሉ በስርአት እዛ ማዶ እንዳደረግነው እዚህም ጀምረዋል ከአንዱ የተዘረፈው ቤት ላይ ፎቶ እና ደብዳቤያቸውን አግኝተናል ::

የማን መሆኑን እናሳያቹሃለን :: በጣም የሚያሳዝን ስራ ነው እየተሰራ ያለው ::

ከራበዉ ቢኮራመትም ቢሞትም ጭምር ከዚህ በላይ ግን ለትግራይ ህዝብ ሓዘን ልተውለት ተገቢ አይደለም ::

አሁንም በመንደሮች እየተበታተነ ነው:: በደምብ እዩት ሌላ ስራ የላቹሁም ከበታቻቹሁ ያለውን አደራጁት ::ከአዛዦች ውጭ ሁሉም ይሰማራ ይሂድ ::

ምክትሎቹ ከናንተጋ ያሉት ከአዛዦች ጋር ከበታቻቸውም እየተረዳዱ እያንዳንዱ በቦታው እንዳለ አረጋጣቹሁ ሪፖርት አድርጉ ::

ሪፖርት እፈልጋለሁ አሁን

ካልሆነ እንደ መጥፎ የሆነ እንሰሳ በየቦታው እየተዞረ መጥፎ የሆነ ስራ ነው እየተሰራ ያለው ይሄንን በፍጥነት አውርዱት አሁን::

79 ወስጃታለሁ
2.2K views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 18:50:04 ጀግናዉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ጥምር ጦሩ ለሀገሩ ልዖላዊነትና ለሕዝቡ ነፃነት ሽብርተኛዉ ህወሓትን የመደምሰስ ተጋድሎዉን አጠናክሮ ቀጥሏል።

ሰራዊቱና ጥምር ጦሩ በራያ ግንባር እያደረገ ባለዉ ተጋድሎ በራያ ቆቦ ጨፌ መንደር 028 ገደባ ቀበሌ የነበሩ የቡድኑ በርካታ ታጣቂዎች ለመሸሽ ከአካባቢው ሲወጡ ሌሎች ታጣቂዎች መውጣት የለብንም በማለት እርስ በርስ ባደረጉት የተኩስ ልዉዉጥ በርካት ታጣቂዎች መገደላቸው ታውቋል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
2.6K views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 18:37:00
በራያ ግንባር

እነዚህ ተሸከርካሪዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ጥምር ጦሩ በቅንጅት በግዳን ግንባር በጠላት ላይ እየወሰዱት ባለዉ እርምጃ  ቀይ አፈርን ሲቆጣጠሩ የማረኳቸው ጠላት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች በከፊል ናቸው።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
2.6K views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 13:48:01
በ48ኛው የበርሊን ማራቶን ኢትዮጲያዊቷ ትግስት አሰፋ አሸንፋለች።

#በነገራችን ላይ በበርሊን ማራቶን ኢትዮጲያውያን ሴት አትሌቶች ለሶስት ተከታታይ አመት ማሸነፍ ችለዋል።በወንዶችም ቢሆን የባለፈው ዓመት ጉዬ አዶላ ካቻምና ደግሞ ቀነኒሳ በቀለ አሸናፊ እንደነበሩ ይታወሳል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
2.9K views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 13:39:05
“የቱርክ እና ኢትዮጵያ ግንኙነት አሳስቦኛል”፦ ግብጽ

በቱርክ እና ኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረው የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳሳሰባት ግብጽ አስታውቃ ነበር።

ካይሮ በአንካራ እና አዲስ አበባ መካከል የተፈጠረው ትብብር እንቅልፍ እንደነሳት ለወዳጆቿ አሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት መግለጿን ሮይተርስ የዜና ማዕከል ዛሬ አስነብቧል።

ካይሮ ይሄንን ቅሬታዋን ለአሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት ያቀረበችው አንካራ አዲስ አበባን በወታደራዊ አቅም በተለይም በሰው አልባ የጦር አውሮፕላን /ድሮን/ በገፍ እያስታጠቀች ነው በሚል መሆኑን ሮይተርስ ከ2 የግብጽ የደህንነት የመረጃ ምንጮቼ አገኘው ባለው ዘገባ ላይ ጠቅሷል።

በኢትዮጵያ እና ቱርክ መካከል የተፈጸመ የሰው አልባ የጦር አውሮፕላን /ድሮን/ የግዢ ስምምነት ካለ አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት አስፈላጊውን ማጣራት አድርገው ስምምነቱን ያስቁሙልኝ ሲል የፕሬዝደንት አል ሲሲ መንግስት ደብዳቤ መጻፉንም ዘገባው አንስቷል።

ካይሮ ከአንካራ ጋር ዳግም የሁለትዮሽ ግንኙነት ለመጀመር የምታደርገውን ጥረት የሁለቱ ሀገራት (ኢትዮጵያ እና ቱርክ) ወታደራዊ ስምምነት ሊጎዳው ይችላል ያለው የግብጽ መንግስት ከህዳሴው ግድብ ውዝግብ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ በሰው አልባ የጦር አውሮፕላን /ድሮን/ መጠንከር ካይሮን እንደሚያሳስባት ሮይተርስ ጨምሮ ጠቅሷል።

ምንም እንኳን ከአንካራም ሆነ አዲስ አበባ በኩል በይፋ ማረጋገጫ ባይሰጠውም በሰው አልባ የጦር አውሮፕላን /ድሮን/ ምርት በዓለም ከቀዳሚዎቹ ሀገራት አንዷ ለመሆን የበቃችው ቱርክ ከአፍሪካ አህጉር ሁለት ሀገራትን (ማለትም ኢትዮጵያ እና ሞሮኮን) እያስታጠቀች ስለመሆኑ ሮይተርስ በዘገባው ጠቅሷል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
2.9K views10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ