2022-09-29 00:14:00
የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ ተደረገ
የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታወቀ።
በዚሁ መሠረት ከመስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት 6:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ የሚከተለው እንዲሆን ተወስኗል።
1. ቤንዚን በሊትር - 57 ብር ከ05 ሣንቲም
2. ነጭ ናፍጣ በሊትር - 59 ብር ከ90 ሣንቲም
3. ኬሮሲን በሊትር - 59 ብር ከ90 ሣንቲም ሲሆን
4. በሥራ ላይ የነበረው ዋጋቸው ባለበት የሚቀጥል የነዳጅ ውጤቶች
4.1. የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር - 76 ብር ከ87 ሣንቲም
4.2. ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር - 43 ብር ከ89 ሣንቲም
4.3. ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር - 43 ብር ከ06 ሣንቲም እንዲሆን ተወስኗል።
በሌላ በኩል አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተረዘጋው የታለመ ድጎማ አሠራር ታቅፈው ሕዝቡን እንዲያገለግሉ የተመረጡት የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽክርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በሁለተኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደገረም።
እነዚህ ተሽከሪዎች በሐምሌ ወር በተወሰነላቸው ዋጋ ቤንዚን በብር 41.26 በሊትር እንዲሁም ነጭ ናፍጣን በብር 40.86 በሊትር እየገዙ እንዲቀጥሉ ብቻ ሳይሆን ከእጥፍ በላይ ያደገ ድጎማ ከመንግሥት እንዲያገኙ የተደረገ ስለሆነ በሚቀጥው ጊዜ ዋጋ እስኪሻሻል ድረስ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ አይደረግም ሲል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጿል።
ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
265 views21:14