Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi_merej
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.68K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-11-05 14:44:03
አይኤምኤፍ (IMF) በኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት መደረጉን ተከትሎ ቀጣይ ፈንድ ለመልቀቅ እያሰበ መሆኑን አስታውቋል።

ብሉምበርግ እንደዘገበው የድርጅቱ የፈንድ ጉዳይን የሚከታተሉ ባለሙያዎች ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ውይይት እያረጉ መቆየታቸውን አስታውሶ ይህም አዲስ የፈንድ ፕሮግራም ለማሳካት ያስችላል ብሏል።

"ቀጣይ እርምጃዎችን እያሰብን ሲሆን ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር እንወያያለን" ብሏል ተቋሙ። ኢትዮጵያ ያለባትን 30 ቢልዮን ዶላር ብድር ለማስተካከል ውይይት ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ የ1 ቢልዮን ዶላር ዩሮቦንድ ሽያጭ ከፍ እንዳለ የተሰማ ሲሆን ይህም ከባለፉት ሶስት ወራት ዲህ ከፍተኛው ጭማሪ ነው ተብሏል።

*በቀጣይም ከአጎዋ ተጠቃሚነት የተሰረዘችበት እገዳ እንደሚነሳ ተስፋ እናድርግ።


ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
2.7K views11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 14:08:34
#Update

የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የወታደራዊ አመራሮች #ሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ/ም በጎረቤት ሀገር ኬንያ ፤ ናይሮቢ ሊገናኙ መሆኑ ተሰምቷል።

ይህ የተሰማው በዛሬው ዕለት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

በዚህ መድረክ ላይ የሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች በኬንያ ናይሮቢ ተገናኝተዉ በትጥቅ ማስፈታቱ ሂደት ላይ እንደሚወያዩ የተገለፀ ሲሆን በፕሪቶሪያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ #ስራዎች_መጀመራቸው ተገልጿል።

በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት ሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች የስልክ ልውውጥ ማድረጋቸውን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል።

የፊታችን ሰኞ ደግሞ ናይሮቢ ውስጥ ተገናኝተው እንደሚወያዩ መገለፁን የብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
2.6K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 18:34:31 የትግራይ መንግስት የህዝብ ግንኙነት ቢሮ (የተባለ) በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ አውጥቷል።

ቢሮው በመግለጫው በደቡብ አፍሪካ የተደረገውን የሰላም ስምምነት እንደሚቀበለውና ለተግባራዊነቱም እንደሚሰራ ገልፀጿል። አክሎም በድርድሩ የተገኘው ድል ከጦርነቱም በፊት ስንታገልለትና ስንጠይቅ የነበረው  ወደ ጦርነት ያስገባንም፣በጦርነት ውስጥ ሆነን ስንወተውት የነበረው  ህገመንግስቱ ይከበር የሚለው ገዳይ ነበር። ስለሆነው የሰላም ድርድሩ ለትግራይ ህዝብ ያሰገኘለት ድልም ይሄው ህገመንግስቱ ይከበር የሚለው ጉዳይ ላይ ከስምምነት መደረሱ ነው ሲል ቢሮው አሰርግጦ ገልጧል። በተጨማሪም በቀጣይ ቀናት  የትግራይ መንግስት በጉዳዩ ላይ ሰፊ ማብራሪያ አንደሚሰጥ ቃል በመግባት መግለጫውን አጠቃሏል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
1.6K views15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 14:11:27
ዛሬ " የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ " አባላት ፤ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አጠቃላይ ሂደት እና ቀጣይ ስራዎችን በሚመለከት ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ለሁለቱ ም/ቤቶች አፈ-ጉባኤዎች ፣ ለክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮች ፣ ለከፍተኛ ባለስልጣናት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሀሴን የተናገሩት ፦

- ስምምነቱ በዋናነት የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም፣ ሉዓላዊነትና የግዛት እንድነትን ማስጠበቅ ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝቦችን የጋራ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ተጠናቋል።

- በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ሁለት የታጠቀ ሀይል ሊኖር እንደማይችልና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ማክበር እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

- ከህገ-መንግስት ውጪ ያሉ እንቅስቃሴዎች ቆመው በትግራይ ክልል በህገ-መንግስቱ መሰረት ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ #ጊዜያዊ_አስተዳደር ይቋቋማል።

- ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከጉዳታቸው አገግመው ወደ ቀደመው ማህበራዊ ትስስር እንዲመለሱ በጋራ ይሰራል።

- የወደሙ ተቋማትን ጨምሮ የመልሶ ግንባታ ስራዎች በጋራ ርብርብ ሊከናወኑ ይገባል። የትስስርና የተግባቦት ስራዎች የህዝቦችን መጻኢ የጋራ ጉዞ ታሳቢ ያደረጉ ሊሆኑ ይገባል።

- በግጭቱ ምክንያት በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ እንዲሁም በሌሎች መስኮች የደረሰውን ጫና በማስተካካል ረገድ በትብብር መስራት ይጠበቃል።

- የመገናኛ ብዙሃን #ቁርሾዎችን ማባባስ ሳይሆን ዜጎች ከችግሩ ተምረው በቀጣይ አብሮነታቸውን አጠናክረው የሚሄዱበትን ሁኔታ መፍጠር ላይ ሊሰሩ ይገባል።

- #በማወቅም ሆነ #ባለማወቅ የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ የሚሰሩ ኣካላትን በጋራ ማስቆም ይገባል።

- ሁሉም ዜጋ ለሰላም ስምምነቱ #ተግባራዊነት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ  ይገባል።
@wektawi_Merej
2.3K views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 07:16:46
ቻይና የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አደንቃለሁ አለች!!

ቻይና የተደረሰውን የሰላም ስምምነት እንደምታደንቅ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን ገለጹ፡፡አምባሳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በሁለቱም ወገን በተደረገው የሰላም ስምምነት ደስ ብሎናል ብለዋል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
2.7K views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 20:04:56 ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች!

ደቡብ አፍሪካ በታካሄደዉ ድርድር በዋናነት ትህነግን ማትረፍ ተችሏል፡፡ የቤት ባሪያዎቹ ዥዋዥዌ ከመጫዎት ዉጭ ምንም ሚና ስለማይኖራቸዉ ስለእነሱ ብዙም መጨነቅ የለብንም፡፡ ይሁን እንጅ ከራሳችንና ከቀጠናዉ ጥቅም አንፃር ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮችን አነሳለሁ፡፡

1. በዚህ ድርድር ችግሮችን ለመፍታት የተቀመጠዉ ዋና አቅጣጫ ህገ-መንግስቱና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ነዉ፡፡ በዚህ መርህ መሰረት ዋናዎቹ ተጠቃሚዎች ትህነግና ኦህዴድ/ኦነግ ናቸዉ፡፡ ምክንያቱም ይህ ህገ-መንግስትና ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ፀረ- አማራ መሆኑ የታወቀ ሀቅ ስለሆነ፡፡

2. ይሄ ድርድር ዋናዉንና ወሳኙን የማንነትና የወሰን ጉዳይ (ወልቃይት፣ጠለምትና ራያ) በማድበስበስ ያለፈዉ በመሆኑ ችግሮች መቀጠላቸዉ አይቀርም፡፡

3. በዚህ ጦርነት ብዙ ጉዳት የደረሰባቸዉ አማራና አፋር በድርድሩ ባለመወከላቸዉ የሰላም ስምምነቱን ዘላቂነት ጥያቄ ዉስጥ ይከተዋል፡፡ የኤርትራ አለመሳተፍም ነገሩን ማወሳሰቡ አይቀርም፡፡ በዚህም የምስራቅ አፍሪካ የሰላም ጉዳይ አደጋ ዉስጥ ይገባል፡፡

4. የዚህ ጦርነት ዋና ግብ ትህነግን ማክሰምና ምልክቱን፣ አስተሳሰቡንና ስሙን መጠቀም ወንጀል የሚሆንበትን ስርዓት ማስፈን/ማንበር  መሆን ሲገባዉ ትህነግ ህልዉናዉ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡ ትህነግ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ተሳተፎዉ እስከቀጠለ ድርስ ለኢትዮጵያም ሆነ ለምስራቅ አፍሪካ የሰላም ስጋት ሆኖ መቀጠሉ አይቀርም፡፡ ትህነግ በምርጫ አሸንፎ ክልሉን ማስተዳደሩ ስለማይቀር ለአማራ ህዝብ የስጋት ምንጭ ሆኖ ይቀጥላል፡፡

5. ትህነግ በአማራና በአፋር ህዝብ ላይ ለፈፀመዉ የዘር ማጥፋት፣ የጦር መንጅልና በሰብአዊነት ላይ ለፈፀመዉ ወንጀል ተጠያቂ ስለማይሆን ቁርሾዉ ከህዝባችን ጋር አብሮ ይቀጥላል፡፡

6. በአማራና በአፋር ህዝብ ላይ የደረሰዉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳት ተገቢዉ ትኩረት ባለመሰጠቱ እነዚህን አከባቢዎች መልሶ የማልማትና ማህበራዊ ምስቅልቅሉን የማስተካከል ስራዎች ዝቅተኛ ይሆናሉ፡፡

7. የአማራን ህዝብ ጥያቄ በሚያነሱ ሀይሎች ላይ ትህነግ፣ ብአዴንና ኦህዴድ/ኦነግ በመተባበር ርምጃ ይወስዳሉ፡፡

( ደመወዝ ካሴ  የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህርና ጠበቃ )

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
1.7K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 20:04:30
1.6K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 11:12:36
ክቡር ጀኔራል እንኳን ደስ አለዎት

ክቡር ጀኔራል አበባው ታደሰ ከተገፉበት ፤ በጡረታ ከወጡበት ሙያና ተቋም ድጋሜ ጥሪ ተደርጎልዎት የእረፍት ጊዜዎን ለሀገር ክብር ፣ ለኢትዮጵያ ሉአላዊ አንድነት  ቀን ከለሊት ከጓዶችዎ ጋር ሆነው ሰርተው ትልቅ ለውጥና ውጤት አምጥተዋል።

ኢትዮጵያ እንደ እርስዎ አይነት ጀግና ፤ ታጋሽ ፤ አስተዋይና ጥበበኛ ፤ ቁጥብና ለውጥ አምጪ ጀኔራል ፈልጋ ነበርና እርስዎን አግኝታ እነሆ ወደ ታላቅነቷና ገነናናነቷ እየተመለሰች ነው።

ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ከአለም ካርታ ለመፋቅ ከውጭና ከውስጥ ተደራጅተው ቢወጓትም በአንድነት የአመራር ጥበብ ቁርጠኝነትና ትግዕስት የተሞላበት ጀግንነት እነሆ በዓለም አደባባይ አሸናፊነቷ ታየ።

ክቡር ጀኔራል አበባው ታደሰ እና ጓደኞቹ ገና ብዙ ስራ ቢጠበቅባችሁም ላመጣችሁት ልዩ ውጤት እጅግ ልትመሰገኑ ብሎም ታሪክ ሁሉ ሊዘክራችሁ የሚገባ ታላቅና ሀያል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አመራር ናችሁና ክብር ይገባችኋል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
2.9K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 11:09:56
በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጥቅምት 24 ቀን የተፈጸመዉ ጥቃት በመታሰብ ላይ ነዉ

"ጥቅምት 24 ቀን መቼም አንረሳውም" በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በመታሰብ ላይ ይገኛል።

በሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ የደረሰው ጥቃት 2ኛ ዓመት የመታሠቢያ ስነ-ስርዓት በተለያዩ የሠራዊቱ ክፍሎች  እየተከናወነ ይገኛል ሲል የኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሰራዊት አስታዉቋል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
2.7K views08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 22:15:58 የዛሬዉ የሰላም ስምምነት ቁልፍ መግባቢያዎች

¤ ህወሓት በቀጣዮቹ ሰላሳ ቀናት ዉስጥ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ለመፍታት ተስማምቷል በስምምነቱ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንደሚፈታ ፤ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በ24 ሰዓት ውስጥ አመቺ ቦታ መርጠው ንግግር ያደርጋሉ

¤ ስምምነቱ በተፈረመ አምስት ቀናት ውስጥ የሁለቱ ወገን ወታደራዊ አመራሮች የትጥቅ ማስፈታት ሂደቱ የሚመራበትን ዝርዝር አፈጻጻም በጋራ በማውጣት ተግባራዊ ሥራዎችን መሥራት ይጀምራሉ

¤ ህወሃት ያሉትን ሁሉንም የቡድን እና ከባድ መሣሪያዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያስረክባል ይህም የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በተገናኙ አስር ቀናት ውስጥ የሚተገበር ይሆናል

¤ በቀጣዮቹ ሰባት ቀናት ውስጥ የፌደራል መንግሥት መቀሌን ተረክቦ በከተማው ውስጥ እና ዙሪያ ሁሉንም አይነት የጦር መሣሪያ ትጥቅ ያስፈታል

¤ በመላዉ ትግራይ ክልል በአጭር ቀናት ውስጥ አሁን ያለው የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደር ይቋቋማል። በሚዋቀረው ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥም የትግራይን ሕዝብ የሚወክል አካል ይሳተፋል

¤ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጎረቤት ሀገራት የሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎችን ደኅንነትና ሰላም የሚያረጋግጥ ስምሪት የሚያደርግ ይሆናል። መከላከያ ሠራዊቱ በማንኛውም የትግራይ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ሕግ የማስከበር ስልጣኑን ከህወሓት ሙሉ በሙሉ ይቀበላል። ህወሓት ለተግበራዊነቱ ምንም አይነት እንቅፋት እንደማይፈጥር ተስማምቷል።

¤ የሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የማኅበራዊ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲጀመሩ ሁኔታዎች ያመቻቻል፤ ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል

¤ ህወሓት ያለ ፌደራል መንግሥት እውቅና ከማንኛውም የውጭ አካል ጋር ግንኙነት ማድረግ ያቆማል። እንዲህ አይነት ተግባር የሚፈጹ ግለሰቦች ካሉ በሀገሪቱ ሕግ የሚጠየቁ ይሆናል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
3.3K views19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ