Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi_merej
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.68K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-09-25 06:15:46
አዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች !

ሰኞ መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የሚካሄደውን የደመራ የመለኮስ ስነ-ስርአት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፦

•  ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም  ከኤድናሞል በአትላሳ ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ  ኡራኤል አደባባይ

• ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ

• ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ  ለገሃር  ለሚመጡ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛ ላይ

• ከቡልጋሪያ በሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር የሚሄዱ ጠማማ ፎቅ አካባቢ

•  ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ እንዲሁም ከጦር ኃይሎች በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ለገሃር  የሚወስደው ሚክሲኮ አደባባይ

• ከተከለ ሃይማኖት በጎማ ቁጠባ  ወደ ለገሃር ሰንጋተራ 40/60 ኮንደሚኒዬም አካባቢ

• ከጌጃ ሰፈር ፣ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎማ ቁጠባ

• ከመርካቶ በተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሜትሮሎጂ በር ላይ

• ከራስ ቴአትር በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ

• ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ ሼል

• ከፒያሳ በቸርችር ጎዳና ለገሃር ቴዎድሮስ አደባባይ

• በአሮጌው ቄራ ፍል ውሃ ንግድ ማተሚያ ቤት

• ከካዛቺስ ወደ ሂልተን ካዛንቺስ ቶታል

• ከአዋሬ በካዛንቺስ ወደ ፍል ውሃ የሚወስደው መንገድ የቀድሞ 6ኛ ፖሊስ መታጠፊያ ላይ ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

ህብረተሰቡ ይህን አውቆ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም መልዕክት አስተላልፏል።

በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም ክልክል ነው ተብሏል።

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
3.1K views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 00:06:03 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 77ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር

የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት በሚደረግ የሰላም ድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ ናት፣

ከአፍሪካ ሕብረት ውጭ የሚደረግ ሌላ አካሄድ ተቀባይነት አይኖረውም፣

ኢትዮጵያ እየተገበረችው ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በበርካታ ቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞች ተተክለዋል፣

ኢትዮጵያ ዘላቂነት ያለው የኢነርጂ ሽግግርና የአረንጓዴ እድገት እያስመዘገበች ነው፤ ይህ ተግባሯም እውቅናና ተግባራዊ ድጋፍ ሊቸረው ይገባል፣

አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ጠይቀዋል፣

አፍሪካዊያን ጥያቄያችን ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ሁልጊዜም ይህን ጥያቄ አጠናክረን እንቀጥላለን፣

የአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆን የሚችለው በፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ተገቢው ውክልና ሲኖራት ነው፣

ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት በማኅበራዊ ፣ ምጣኔ ሀብትና በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ለውጥ አሰመዝግባለች፣

ኢትዮጵያ የዓባይን ግድብ በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስር በሚደረግ የሦስትዮሽ ድርድር ጉልሕ ተፅዕኖ በማያደርስና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መርህን መሰረት በማድረግ ልዩነቶችን ለመፍታት አሁንም ፅኑ አቋም አላት፣

ሁሉም አገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቁ በካይ ጋዞችን ለመቀነስ ከአሁን በፊት የገቡትን ቃል ሊተገብሩት ይገባል፣

ዓለም በበርካታ ፈተናዎች እያለፈች ነው፤ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የከፋ ድህነት፣ ግጭት፣ ሽብርተኝነትና ጂኦ ፖለቲካዊ ሽኩቻዎች የባለብዙ ወገን የግንኙነት መድረክን እየፈተኑት መሆኑን ነው፣

የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ለመከላከል አሰፈላጊውን ፋይናንስ መመደቡ ላይም በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይገባናል፣

አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሆኑ በካይ ጋዝ ልቀት ያላት ድርሻ ከቁጥር የማይገባ ቢሆንም ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቁ በካይ ጋዟችን ለመቀነስ ግን የተለያዩ ስራዎችን እየከወነች ነው፣

የአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን ጉዳት አስቀድሞ በመተንበይ በትብብር መስራት ይገባናል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
3.1K views21:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 18:20:07
የሸኔ አባላት ከአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ጋር ተሰልፈው በግንባር ሲዋጉ ተያዙ

የሸኔ አባላት ከአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ጋር ተሰልፈው በግንባር ሲዋጉ መያዛቸው ተገለጸ።
ሁለቱ አሸባሪዎች ህወሓት እና ሸኔ ኢትዮጵያን ለማፍረስ አብረው ለመሥራት እንደተስማሙና እየሠሩ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወቃል። አሸባሪው ህወሓት በሁለት ዙር በከፈተው ጦርነትና በፈጸመው ወረራ በአማራ እና አፋር ክልሎች ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል፤ ንጹሀንን ገድሏል፤ ከአርሶ አደሩ ጓዳ ሽሮና በርበሬ ሳይቀር ዘርፏል።
አሁንም  በተመሳሳይ ህወሓት እና የግብር አጋሩ ሸኔ  በፈጸሙት ሦስተኛ ዙር ወረራ ተመሳሳይ ጥፋት እየፈጸሙ መሆናቸው ይታወቃል። ይህንንም በሠነድ ሳይቀር አስደግፈው እየሰሩበት መሆኑን ከተጋለጠው ሚስጢራዊው ሠነድ ለመረዳት ተችሏል። ከባቲ ተነስተው የሽብር ቡድኑን የተቀላቀሉት የሸኔ አባላት ከሌላኛው የጥፋት ኃይል ህወሓት ጋር ተሰልፈው ሲዋጉ እንደነበር መናገራቸውን የኢፕድ ዘገባ አመላክቷል።
ህወሓት ባቲ ከተማን ከወረረ በኋላ ተሸንፎ አካባቢውን ለቆ ሲሄድ ከግብረ አበሩ ሸኔ ጋር በመተባበር ተዋጊዎችን መመልመሉን እነዚሁ እጃቸውን የሰጡት ታጣቂዎች አስረድተዋል። በኋላም ወደ ትግራይ በማምራት ለወራት ወታደራዊ ስልጠና መውሰዳቸውን የገለጹት ታጣቂዎቹ፤ በመጨረሻም ከህወሓት አመራሮች የቀረበላቸውን ትጥቅ ይዘው አፋርና አማራ ክልል ላይ ወረራ ሲፈጸም መሳተፋቸውን ነው የገለጹት።
አላማ ለሌለው ጦርነት ህይወታቸውን መገበር እንደሌለባቸው የተረዱት የሽብርተኛው ሸኔ አባላት ግን መሹለኪያ መንገድ በማመቻቸት ለመከላከያ  ሠራዊት ዕጃቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል። ሠራዊቱም በተገቢው መንገድ እየተንከባከባቸው መሆኑን ዕጃቸውን የሠጡት የሽብር ቡድኑ አባላት ገልጸዋል።
    
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
3.5K views15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 12:34:38
#ጥንቃቄ

በአዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ፓሊስ በመምሰል የአንድን ግለሰብ ቤት ለመዝረፍ የሞከሩ ግለሰቦች ሙከራቸው በህብረተሰቡ እና በፀጥታ ኃይሎች ትብብር መክሸፉን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።

ድርጊቱ የተፈፀመው በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው " ቀጠና አንድ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን 4 የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱና 2 ሲቪሎች ሆኖው በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በመግባትና ሀሰተኛ የፌዴራል ፖሊስ መታወቂያ በማሳየት በር እንዲከፈትላቸው ካደረጉ በኃላ ሰራተኛዋን አግተው ዝርፊያ ሊፈፅሙ ሲሉ በአካባቢው በነበሩ የፀጥታ ሀይሎች እና ህዝባዊ ሰራዊቶች የዝርፊያ ሙከራቸው መክሸፉን አስተሳደሩ ገልጿል።

የፀጥታ ሀይሎች ቀድሞም በነበራቸው  ጥርጥሬ ዘራፊዎቹን ሲከታተሏቸው እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን ዘራፊዎች ከውጭ ባስቀመጧቸው ግብር አበሮቻቸው ቀድሞ አዘጋጅተውት በነበረው " ኮድ 3 ኦሮ " በሆነ ተሽከርካሪ ሊያመልጡ ችለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ቢያመልጡም በአካባቢው  የደህንነት ካሜራ ስለነበረ ጉዳዩን ፖሊስ ይዞት ክትትል እያደረገበት ይገኛል ተብሏል።

ማህበረሰቡ እራሱን ከመሰል አጭበርባሪዎች ሊጠብቅ ይገባል፤ አጠራጣሪ ነገሮችንም ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች ሊያሳውቅ ይገባል ተብሏል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
3.7K views09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 20:25:05
ለሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች በሙሉ፦

(መስከረም 13/2015 ዓ.ም) የፊታችን ማክሰኞ መስከረም 17/2015 የሚከበረው የመስቀል በዓል በሰላም ተከብሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ተወስኗል።
በዚሁ መሰረት ከእሁድ መስከረም 15/2015 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም 17/2015 ዓ.ም ማታ 12:00 ሰዓት ድረስ ምንም አይነት የሞተር እንቅስቃሴ በከተማዋ የተከለከለ መሆኑን ተገንዝባችሁ ተገቢውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ኤጀንሲው ያሳውቃል። ይሄንን ተላልፈው በሚገኙ ሞተረኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ጭምር ኤጀንሲው ያሳስባል።
#ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
3.9K views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 20:13:32
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ " SKYTRAX 2022 " የዓለም አየር መንገድ ሽልማት ላይ በ4 ዘርፎች ተሸለመ።

አየር መንገዱ 11 ደረጃዎችን በማሻሻል ከዓለም ምርጥ 100 አየር መንገዶች 26ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ተገልጿል። ደረጃው በዓለም ዙሪያ ባሉ የአየር መንገድ ደንበኞች በተሰጠ ድምጽ ነው።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሸለማቸው ሽልማቶች የትኞቹ ናቸው ?

የ2022 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ፣ ለ5 ተከታታይ ዓመታት ፤

  የ2022 የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ደረጃ አየር መንገድ፣ ለ4 ተከታታይ ዓመታት

የ2022 የአፍሪካ ምርጥ ኢኮኖሚ ክላስ ደረጃ ፤ ለ4 ተከታታይ ዓመታት

በአፍሪካ ውስጥ ምርጥ ቢዝነስ ክላስ ምግብ አቅራቢነትን ሽልማት አሸንፏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
3.7K views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 19:37:11
ሩሲያ አውሮፓንና አሜሪካን በሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል ልትመታ እንደምትችል አስጠነቀቀች!!

ሰባት ወራትን ያስቆጠረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት አሁን ደግሞ አዳዲስ ክስተቶችን ወደ ማስተናገድ በመሸጋገር ላይ ይገኛል።

በአሜሪካ እና ምዕራባዊያን የጦር መሳሪያ እርዳታ በመታገዝ ዩክሬን በሩሲያ የተያዙ ግዛቶችን በማስለቀቅ ላይ ስትሆን ሩሲያ ደግሞ አራት የዩክሬን ግዛቶችን ወደ ራሷ ለመጠቅለል ከዛሬ ጀምሮ ህዝበ ውሳኔ ታካሂዳለች።

ለዚህ ተልዕኮዋ እንዲረዳትም 300 ሺህ ተጠባባቂ ጦሯን የጠራችው ሩሲያ ብሄራዊ ደህንነቷ ስጋት ውስጥ ከገባ ደግሞ የኑክሌር ጦሯን ጨምሮ ማንኛውንም መንገድ እንደምትጠቀም ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናግረዋል።

የሩሲያን አዲስ ውሳኔ ተከትሎ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት እና ኔቶ በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ በመስጠት ላይ ሲሆኑ በአውሮፓ የተሰማራው የቀድሞው የአሜሪካ ጦር ጀነራል ቤን ሆጅስ ሩሲያ የምትመካበትን ጦር ኔቶ ማውደም ይችላል ብለዋል። ሩሲያ በዩክሬን ኑክሌር ጦር ከተጠቀመች ሞስኮ የምትመካበት እና በጥቁር ባህር ላይ ያሰፈረችው ጦር አውሮፓ ያለው የአሜሪካ ጦር ሊያወድመው ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።

የሩሲያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የሀገሪቱ ምክትል የጸጥታ ሀላፊ  ለአሜሪካው የጦር ጀነራል አስተያየት ምላሽ ሰጥተዋል።ሩሲያ ሀይፐር ሶኒክ በተሰኘው ሚሳኤል ብቻ የአውሮፓ እና አሜሪካ ከተሞችን ልትመታ እንደምትችል አስጠንቅቀዋል ሲል ራሺያን ቱዴይ ዘግቧል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
3.8K views16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 11:58:28 የኢፌዴሪ አየር ኃይል በ2022 ዓ.ም ከአፍሪካ ቀዳሚ አየር ኃይሎች አንዱ ለመሆን እየሠራ መሆኑን አስታወቀ።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ኃይሉ መኮንን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮችና ሠራተኞች ጋር አየር ኃይሉን በጎበኙበት ወቅት በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤ አየር ኃይሉ ለውጡን ተከትሎ በሠራቸው ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ሥራዎች በለውጥ ሂደት ውስጥ ይገኛል። በዚህም በ2022 ዓ.ም ከአፍሪካ ቀዳሚ አየር ኃይሎች አንዱ ለመሆን እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

አየር ኃይሉ በጦርነት ውስጥ እያለፈ ቢሆንም ባገኘው ጊዜ ሁሉ መዋጋት ያለበትን እየተዋጋ መሥራትና ማልማት ያለበትን እየሠራ ዛሬ ከደረሰበት ደረጃ ላይ ደርሷል ያሉት ምክትል አዛዡ፤ ተቋሙ ያሰበውን ራዕይ እንዲያሳካ እየሄደበት ያለው መንገድ ትክክል ነው ወይ የሚለውን ለመለየት የዜጎች ሚና ትልቅ በመሆኑ መሰል ጉብኝቶች ለእኛ ትልቅ አቅም የሚሆኑ ናቸው ብለዋል።

አየር ኃይሉ በፈጣን ለውጥ ውስጥ ቢሆንም ከዚህ በላይ እንዲያድግና እንዲዘምን እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡ "ከሕዝባችን የምናገኛቸው ድጋፎችና ሐሳቦች ትልቅ ብርታት የሚሆኑ ስለሆኑ መላው ኢትዮጵያውያን አየር ኃይሉ የራሳቸው መሆኑን ተገንዝበው በማንኛውም ጊዜ መጥተው መጎብኘት ይችላሉ" ነው ያሉት፡፡
በኢፌዴሪ አየር ኃይል የአቪየሽን ከባድ ጥገና አዛዥ ኮሎኔል መሠረት ጌታቸው በበኩላቸው፤ አየር ኃይሉ ከጥንት ጀምሮ የጀግኖች መፈጠሪያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አሁንም መሠራት ያለባቸው የሪፎርም ሥራዎች እየተሠሩ የሚሰጠውን ግዳጅ በአግባቡ እየፈጸመ መሆኑን ገልጸዋል።
አየር ኃይሉ ዘመኑ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ እንዲታጠቅ እየተሠራ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት አየር ኃይሉን ለማዳከም ሥራዎች የተሠሩ ቢሆንም ከለውጡ በኋላ በተሠሩ የሪፎርም ተግባራት ተቋሙ ከየትኛውም ወገንተኝነት ነጻ ሆኖ ለታላቋ ሀገር የሚመጥን ታላቅ አየር ኃይል እንዲሆን እየተሠራ ነው ብለዋል።
ከአፍሪካ ቀዳሚ ለመሆን ያስቀመጠውን ራዕይ ለማሳካት ቴክኖሎጂ ላይ አተኩሮ መሥራት፣ የሰው ሀብትን ማብቃትና መሠረተ ልማቶችን የማስፋት ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
ለዓመታት ያገለገሉ ጀቶችንና አውሮፕላኖችን በራስ አቅም በመጠገንና የማሻሻያ ሥራ በመሥራት ለተጨማሪ ዓመታት አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ተግባራት እየተከናወኑ ነው፤ በዚህም እንደ ሀገር ለግዢ ሊወጣ ይችል የነበረን በርካታ ሀብት ማዳን መቻሉን እንደገለጹ ኢፕድ ዘግቧል፡፡

የአፍሪካ አመራር አካዳሚ ምክትል ርእሰ አካዳሚ ወይዘሮ ሕይወት ዓለማየሁ "ጉብኝቱ በአየር ኃይላችን እንድንኮራና ሀገራችን ብዙ ተስፋ እንዳላት የተገነዘብኩበት ነው"ብለዋል፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
4.1K views08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ