Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹 ወ
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi_merej
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.68K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-10-28 10:28:50 የታደሰ ወረደ (ጄ) መግለጫ አጠሬራ!

ጀነራል ታደሰ ወረደ በትናትናው እለት በትግርኛ ለአንድ ሰአት ከአምስት ደቂቃ የቆየ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫው ከ3ቀናት በፊት የክልሉ ፕሬዚዳንት ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ከሰጡት የተቃረኑ ብዙ ሃሣቦች አሉት።

ለምሳሌ ደብረጽዮን የኢትዮጵያ መከላከያና ሻቢያ ወደ ትግራይ የገቡበትን አላማ ሲያብራራ

"አላማቸው አንድና አንድ የትግራይን ህዝብ ከምድረ ገጽ ለማ*ጥፋት ነው" ብሏል።

ጄኔራል ታደሰ ወረደ ግን የሁለቱን አላማ ነጣጥሎ ይመለከተዋል።

"የኤርትራ ሃይሎች አላማ የትግራይን ህዝብ ከቤት ንብረቱ በማፈና*ቀል ግማሹ ወደ አማራ ክልል ገብቶ በስደተኛነት ተበት*ኖ እንዲኖር ቀሪው ደግሞ በትግራይ በየሰፈሩ በሚተከሉ ድንኳኖች ውስጥ ተበትኖ እንዲኖር ነው" ብለዋል።

"በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መከላከያ አላማ ደግሞ የትግራይ ሃይሎችን ትጥቅ አስፈትቶ ጸጥ ረጭ አድርጎ ትግራይን በምስለኔ ማስተዳደር ነው። ለዚህም ኦሮሞውን አለሙ ስሜ ትግራይን እንዲያስተዳድር ሹሞቷል" ይላል ታደሰ።

ታደሰ ወረደ ከዚህ በፊት ከነበረው ቃለመጠይቆች በተለየ ተቀዛቅዞና ባልተለመደ መልኩ የጦርነቱ አከባቢዎች ሁሉ እየተዘነጉት ሲጨነቅ ይታያል። አድዋና አክሱም ወይም ከተሞች ስለተያዙብን ጦርነቱን ተሸነፍን ማለት አይደለምም ብሏል።

በኔ መረዳት የትግራይ ሃይሎች በዚህ ሰአት በአንድ እዝ ስር የነበራቸው ገመድ ተበ*ጣጥሷል። ምናልባትም እየተዋጉ ያሉት እነ ታደሰ ወረደ Plan B ብለው ባስቀመጡት ከተበተኑ በኋላ ሁሉም በየጥሻው የሽምቅ ውጊያ እንዲያደርግ በሚለው ነው። ታደሰም በንግግሩ የሚጠቅሳቸው የውጊያ ቦታዎች እዚህ ግባ የማይባሉና በኢትዮጵያ ጥምር ጦር ስር የሚገኙ ናቸው። ከጠቀሳቸው የራያውን የባላና የዋጉን ዛታ ለአብነት መጥቀስ ይቻላል። መቶ በማይሞሉ ታጣቂዎች ለሰአታት ያልቆየን የሽምቅ ውጊያ እንደ ትልቅ ጦርነት አድርጎ አቅርቦታል።

የሰላም ድርድሩን በተመለከተ

ለቀረበለት ጥያቄ "ሰላም ከተገኘ የኛም የመጀመሪያ አማራጭ ነው። አሁን ላይ በሚካሄደው ድርድር ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ የኤርትራን ጦር ያስወጡልን፣ የኢትዮጵያ መከላከያና የአማራ ሃይልም ተኩሱን ያቁም፣ ከዛ በኋላ ለሰላም መደላድል ይሆናል መነጋገር እንችላለን።" ብሏል።

በመጨረሻ ባስተላለፈው መልዕክት

ለአማራ ህዝብ
"የአማራ ሃይሎች በተለይ ልዩ ሃይሉ፣ ፋኖና ሚሊሻው ወደ ትግራይ በሃይል ገብተው እየተዋጉን ነው። ከንድ ወር በፊት በነበሩት ውጊያዎች የአማራ ሃይሎች ብዙም አልነበሩም፣ አሁን ግን ፋኖም ልዩ ሃይሉም ሚሊሻውም በተለያዩ ቦታዎች ፊለፊት እየተዋጉን ነው።

ለምሳሌ
❶ ዛታን የያዘው የአማራ ፋኖና ሚሊሻ ነው፣

❷ በሪ ተኽላይን ተዋ*ግቶ ከዛም አልፎ ስንኮማጀት ግንባር ላይ ቆርጦ ለመግባት አሁንም እየተ*ዋጋ ያለው የአማራ ልዩ ሃይል ነው፣

❸ ጨርጨር ላይ እየ*ተዋጋ ያለው ብቻውን የአማራ ልዩ ሃይል ነው፣

❹ በተለይ በሪተኽላይ ላይ የተሰማሩት ሁለቱ "መክት አማራ እና ሪፐፕሊካን ጋርድ " የተባሉት ናቸው። ይህ መክት አማራ የሚባለው ጦር በውጭ ሃይሎች የሰለጠነ ሃይል ነው። እነዚህ ሆነው ነው መስመሩን የቆ*ረጡት። ይህ መክት አማራ የተባለው ሃይል ከልዩ ሃይሉ የተለየ ሲሆን በኮማንዶነት ደረጃ የሰለጠነና የተደራጀ ነው።  ሽራሮንም ከፊት ሆኖ የገባው ይሄው ሃይል ነው።

❻ ባሁኑ ሰአት የአማራ ሃይሎች በተለየ መልኩ ከፊት ናቸው። ለምን? እኔ ጥያቄ ነው ምጠይቃቸው። ከተቻለ ወላጆቻቸው ይመልሱልን። ከትግራይ ይውጡ።

የአማራ አመራሮች የአማራ ወጣቶች ትግራይ ገብተው ወንጀል እንዲፈጽሙ እያደረጓቸው ነው። ይሄ ወንጀል ለነገ በወንድማማችነት ለመቀጠል ከባድ ጠባሣ ይጥላል። ጊዜ ያልፋል፣ የአማራ ልሂቃን ይሄንን አስበውበት ቶሎ ማስቆም ካልቻሉ አሁን ያለው የአማራ በታሪክ ተጠያቂ ይሆናል። " (ታደሰ ሸዋ ድረስ ገብተው ስለጨፈጨፉ የትግራይ ሃይሎች ትንፍሽ አላለም)

ለኤርትራ ህዝብ
"እኛ የኤርትራ ህዝብ ጋር ያለን ግንኙነት (እንደሌላው አይደለም) በደም ነው። ልጆቻችሁን የራሳቸውን ህዝብ ለማፈናቀል ለመግደል እንዳይመጡ ሰብስቧቸው። እዚህ እየገቡ እያለቁም ነው።"

ለኦሮሞዎች
"እናንተ ለኛ ምስለኔ የምትመድቡልን አይደለንም። ታሪክን ወደኋላ ሄዳችሁ እዩ። በቀዳማይ ወያኔ ጊዜ አማራ ምስለኔ ንጉሱ አማራ ምስለኔ ልከውብን ነው ካልአይ ወያኔ የተፈጠረው። ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አፋር አማራ ሌላም ብሔረሰብ ወደ ክልላችን ለማስተዳደር የተመረጡ ፖሊሶቻችሁን ከልክሏቸው..."

ለትግራይ ህዝብ
"ሁላችንም ከዚህ ከፍ ባለ መልኩ ለፍልሚያ መዘጋጀት አለባችሁ።"

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
4.3K views07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 08:19:35 በሕገ ወጥ የውጭ ሀገራት ገንዘብ ምንዛሪ በተሰማሩ አካላት ላይ በጥናት የተመሰረተ እርምጃ መወሰዱን አገልግሎቱ አስታወቀ!!!

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስና ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በሕገ ወጥ የውጭ ሀገራት ገንዘብ ምንዛሪ በተሰማሩ ግለሰቦችና ድርጅቶቻቸው ላይ ጥናትን መሰረት ያደረገ እርምጃ መወሰዱን አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ ዛሬ ለዋልታ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ባለፉት ሁለት ወራት በሕገ ወጥ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች ምንዛሪ ዙሪያ ሰፊና ጥልቀት ያለው ጥናት ሲካሄድ እንደነበር አመልክቷል፡፡

ችግሩ በጥናት ከተለየ በኋላም መረጃዎችንና ማስረጃዎችን መነሻ በማድረግ በተከናወነው ክትትል በሕገወጥ የውጭ ምንዛሪ ላይ ተሳታፊ የነበሩ 48 ግለሰቦችና ከፍተኛ መጠን ያላቸው የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች እንዲሁም ከድርጊቱ ጋር የተያያዙ የባንክ ደብተሮችና ልዩ ልዩ ሰነዶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል ነው የተባለው፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች የውጭ ሀገር የምንዛሪ ዋጋን የሚተምኑ፣ የሚሰበስቡና ሰብሳቢዎችንም የሚያሰማሩ መሆናቸውን መግለጫው ጠቁሟል፡፡ ሕገወጥ ድርጊታቸውንም ሕጋዊ ፈቃድ ባላቸው የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች፣ የችርቻሮ ሱቆች፣ ቡቲኮች፣ ግሮሰሪዎችና ሱፐርማርኬቶች ሽፋን እንደሚያከናውኑ፤ በተሽከርካሪዎች ላይም ጭምር ይፈጽሙ እንደነበር አመላክቷል፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ የሚሰበሰበው የውጭ ምንዛሪ በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ከሀገር ለማሸሽ እንዲሁም የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ አቅም በማሳጠት ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት በማስከተል ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመፍጠር ታቅዶ ሲከናወን እንደነበር በጥናት መለየቱን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መግለጫ ጠቁሟል፡፡

በወንጀል ድርጊቱ ተጠርጥረው ከተያዙት ውስጥም ለህወሓት ድጋፍ ከሚያደርጉ የሽብር ቡድኑ ደጋፊዎች ጋር በትስስር የሚሠሩና ቀደም ብሎም የውጭ ምንዛሪን በሕገወጥ መንገድ ወደ ትግራይ ሲያስገቡ የነበሩ ይገኙበታል፡፡ ይህም በተቀናጀ መልኩ በውጭም በሀገር ውስጥም ሀብት ለማሸሽና  የውጭ ምንዛሪ አቅምን ለማዳከም ይሠራ እንደነበር ያሳያል ብሏል መግለጫው፡፡

እንደ አገልግሎቱ መግለጫ ሕገ ወጥ የውጭ ሀገራት ገንዘብ ዝውውሩ ወንጀል ከኢትዮጵያ እስከ ሶማሌ ላንድ ሀርጌሳ፤ ከዱባይና አሜሪካ እንዲሁም በሌሎች ሀገራትም ጭምር በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ቤተሰባዊ በሆነ ኔትዎርክ ጭምር የተደራጀና የሚታዘዝ ነበር፡፡ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሕገወጥ የውጭ ምንዛሪ አስተላላፊዎቹ መካከል አንዳንዶቹ ከዚህ ቀደም በቁጥጥር ስር ውለው ፍርዳቸውን ጨርሰው የተለቀቁ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ከ100 ሺሕ ብር በላይ በማስከፈል ወደ ውጭ እንልካለን በማለት የዜጎችን ሀብትና ንብረት ሲዘርፉ የነበሩም በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀልና በውጭ ምንዛሪ ዝውውሩ በነበራቸው ተሳትፎ እንዲያዙ ተደርጓል፡፡

መንግሥት ሕገወጥ ድርጊቱን ለመከላከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች ከኢትዮጵያ የሚወጡባቸውን መንገዶችና ስልቶች በመረጃ በመለየትና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ጥብቅ ቁጥጥር ማድረጉንና በወንጀለኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጫው አስታውቋል፡፡

የሀገርን ሀብትና ንብረት ዘርፈው ገንዘቡን በውጭ ምንዛሪ በማሸሽ ከሚፈጠሩ ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ሀገሪቷን ለመታደግ የሚደረጉ ጥረቶችንም በከፍተኛ ትኩረት እየተከታተለና አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑንም አመልክቷል፡፡

ኅብረተሰቡ ሕገወጦች በቁጥጥር ሰር እንዲውሉ ጥቆማ በመስጠት ያበረከተው አስተዋጽዖ ከፍተኛ በመሆኑ ምስጋናውን ያቀረበው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በቀጣይም ከደኅንነትና ከጸጥታ ተቋማት ጎን በመሆን ድጋፉን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርቧል፡፡
ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
3.9K views05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 00:10:35
በዛሬው የተመድ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የኢትዮጵያ ድምፅ ምን ይመስል ነበር? ብላችሁ በinbox ለጠየቃችሁን ይኸው መልሱ።
ተአቅቦ።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
1.1K views21:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 11:30:25
በትላንቱ የመተከል ጥቃት የተገደሉ የጓንግ ወረዳ ተወላጆች!
            
1ኛ አቶ ሰማነህ ዘለቀ በቀድሞ መተከል አውራጃ ጓንጓ ወረዳ ተወልደው ያደጉት አቶ ሰማነህ ዘለቀ የወረዳውን ህዝብ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች እና በጎ አድራጎት ተግባር ከማገልገላቸው ባሻገር በቀድሞ ስርዓት በመረብ ኳስ ስፖርት ጎጃም ክፍለ ሀገርን በመወከል ኤርትራ ክፍለ ሀገርን ጨምሮ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በመሳተፍ ለጎጃም ክፍለ ሀገር፣ለመተከል አውራጃ እና ለጓንጓ ወረዳ በርካታ የጀግንነት ሽልማቶችን አበርክተዋል።

አቶ ሰማነህ ዘለቀ ትላንት ህይወታቸው እስኪያልፍ ድረስ በጓንጓ ወረዳ አስተዳደር ፅቤት በማህበራዊ ዘርፍ ባለሙያነት ሲያገለግሉ ቆይተው በህክምና ሲረዱ ቆይተው አርፈዋል።
              
2ኛ አቶ ሂስ ሄጮ በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ዳች ሉምቢያ ተወልደው በጓንጓ ወረዳ ዳች ትቤት የተማሩት እና ከጓንጓ ወረዳ ጨረቃ ቀበሌ ህዝብ ጋር ያደጉት አቶ ሂስ ሄጮ በማንዱራ ወረዳ በተለያዩ ሙያ ዘርፎች እና ኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።

ለቤተሰቦች እና ለሁለቱ ወረዳ ህዝብ መፅናናትን ይመኛል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
2.0K viewsedited  08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 00:00:49 የአላማጣ እምቢተኝነትና የህወሓት ጭንቀት
የአላማጥን ነዋሪዎች በብረት መዳፌ ቀጥቅጬ ካልገዛሁ የሚለው አሸባሪው ህወሓት ከፍተኛ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ተቃውሞ እየገጠመው ይገኛል፡፡
ሰሞኑን አላማጣ አካባቢ ስብሰባ የጠራው አሸባሪው ህወሓት በሰዎች አጀብ ይጨናነቃል ያለው መድረክ በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ያውም የቡድኑ ደጋፊዎችና አባላት ብቻ የተገኙበት መሆኑ አስደንግጦታል፡፡ ይህ ሕዝባዊ እምቢተኝነት አንዳች የተደበቀ ነገር ከጀርባው አዝሏል በሚልም ጭንቀት ውስጥ ገብቷል፡፡
እንደ አሸባሪ ቡድኑ ግምገማ ትናንት እንደ ልቡ የሚያዘው ኅብረተሰብ ዛሬ የልብ ልብ ተሰምቶት ፊቱን ያዞረበት በጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሚመራው ጥምር ጦር ወደ ቀጣናው መግባቱ አይቀርም በሚል ነው፡፡  
በዚህ ስሌት የተደነባበሩት በአላማጣ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ  የህወሓት አመራሮች እና መረጃ አቀባዮች ሁኔታው ተባብሶ ከቀጠለ ሕዝቡ  ከእምቢተኝነት አልፎ  ግልጽ ወደ ሆነ ተቃውሞ ይሸጋገራል የሚል ሥጋት ውስጥ ወድቀዋል፡፡ ነገም ኅብረተሰቡ ለጥምር ጦሩ አሳልፎ ይሰጠናል በሚል ከአካባቢው ለመሸሽ ቢያስቡም፤ አሸባሪው ህወሓት ከወረዳ ወደ ወረደ የመንቀሳቀስ እገዳ በመጣሉ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መግባታቻው ታውቋል፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
2.5K views21:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 23:41:53 የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የጅቡቲ የመረጃ ተቋም በድንበር አካባቢ የጸጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፥ በጅቡቲ የመረጃ ተቋም ዳይሬክተር ጀነራል ሐሰን ሰይድ የተመራ ከሀገሪቱ የጸጥታና ደኅንነት አካላት የተወጣጣ የልዑካን ቡድን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን ጎብኝቷል፡፡
የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ሲሳይ ቶላና ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ለልዑካን ቡድኑ አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን፥ ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ልዑኩ እና የኢትዮጵያ አቻ ተቋማት የተካፈሉበት የሁለትዮሽ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ሁለቱ ሀገራትም በድንበር እንዲሁም በቀጣናው በሚስተዋሉ የጸጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ የሚያከናውኗቸውን ስምሪቶች አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል፡፡
ኢትዮጵያና ጅቡቲ ከዲፕሎማሲዊ ግንኙነት ባሻገር በጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የተሳሰሩ ሀገራት እንደመሆናቸው የጋራ የጸጥታና የደኅንነት ሥጋት እንዳለባቸው በውይይት መድረኩ ተነስቷል፡፡
በተለይ ሽብርተኝነት፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች፣ ሕገወጥ የገንዘብ፣ የመሣሪያና የሰዎች ዝውውር የጋራ የጸጥታ ሥጋት በመሆናቸው፤ ችግሮችን ለማስቀረት የመረጃ ልውውጥ ማድረግ እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የኢትዮጵያና የጅቡቲ የመረጃና የጸጥታ አካላት በሁለቱ ሀገራት የድንበር አካባቢዎች የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮችን እና ሕገወጥ ታጣቂዎችን ለመከላከል በጋራ የሚሠሩትን ተግባር ለማጠናከር መስማማታቸውን የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መረጃ ያስረዳል፡፡
ውይይቱ በድንበርም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የሁለቱን ሀገራት ዜጎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማስጠበቅ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ገልጿል፡፡
የሁለቱ ሀገራት ደኅንነትና እጣ ፈንታ እጅጉን የተሳሰረ በመሆኑ የጅቡቲ መጠቃት በኢትዮጵያ ላይ እንደደረሰ እንደሚቆጠር በኢትዮጵያም የሚፈጸም ጥቃት ጅቡቲን እንደሚመለከት በውይይት መድረኩ ተነስቷል ነው ያለው፡፡
በዚህ መነሻነትም ጅቡቲ ከየትኛውም አካል የሚፈጸምባትን ትንኮሳና የሚያጋጥማትን የደኅንነት ሥጋት ለመቀልበስ ኢትዮጵያ ከሀገሪቱ ጎን እንደምትቆም ተጠቅሷል፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መረጃ እንደጠቆመው በውይይቱ የሁለቱ ሀገራት የመረጃና የጸጥታ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ተካፍለዋል፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
2.5K views20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 20:32:10 "የበልዬ" አንጀት አርስ ጥቃት በመቀሌ

"በላይነሽ አመዴ" (በልዬ) ዛሬ በመቀሌ ውጤታማና ዒላማውን የጠበቀ ጉብኝት አድርጋለች። ጉብኝቷ ያለመው በወያኔ የጃጁ ሽማግሌዎችና ወታደራዊ አቅሞች ላይ ነበር። ሁሌም እንደሚሆነው ዛሬ ቮድካው ጌቾ ከጥቃቱ ካመለጠ፤ እንደምንም ተጋግጦ "ንፁሐን ተጎዱ" የሚለውን ወያኔያዊ ነጠላ ዜማ ይዞ ብቅ ይል ይሆናል። የወያኔው ጡሩንባ ዛሬ ጧት ፈረንጆቹ እንዲሰሙት በማሰብ በጉዳዩ ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነችውን ኤርትራን አዳብሎ "በሶስት ግንባሮች መጠነ ሰፊ ዘመቻ ተከፍቶብናል" ከማለት ውጭ፤ የመቀሌውን "የበልዬን" አንጀት አርስ ጥቃት እስካሁን ድረስ በአማርኛም፣ በትግርኛም፣ በእንግሊዝኛም ሆነ በሌላ ቋንቋ በየትኛውም የመለፍለፊያ ዘውጉ ትንፍሽ አላለም። እናንተዬ ምናልባት የሚናገረውን የሚወስንለት የጁንታው ሽማግሌ "በበልዬ" ጉብኝት ተበልቶ ይሆን እንዴ ወይስ ጌታቸው ረዳ ከመሸገበት ገጠር ኢንተርኔት ወዳለበት በአህያ ተጭኖ እየመጣ ይሆን ...ጌቾ እንዴት ነህ ደህና ነህ በሕይወት አለህ

ድል በጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ለሚመራው ጥምር ጦራችን
ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
1.3K views17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 13:50:02
#Update

የሲዳማ ክልል ሠላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ጥዋት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፤ በዋናው ግቢ እና በቴክኖ ግቢ መካከል ያለው የተማሪዎች መሸጋገሪያ ድልድልይ #በመደርመሱ የደረሰውን ድንገተኛ አደጋ በተመለከተ አሁናዊ ሁኔታ ላይ ለደ/ሬ/ቴ/ድ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እንደ ኃላፊው ማብራሪያ ፦

- 415 ተማሪዎች በድልድዩ ላይ ሆነው ድልድዩ ተደርምሷል።

- የአንድ ተማሪ ህይወት በአደጋው አልፏል።

- በድልድዩ መደርመስ አደጋ ከደረሰባቸው መካከል 310 ተማሪዎች ቀላልና 110 ተማሪዎች ላይ መካከለኛና ከባድ ጉዳት ደርሷል። 20 ተማሪዎች የአጥንት ስብራተ ያጋጠማቸው ሲሆን 85 በሚሆኑት ላይ ቀላል አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- ተጎጂዎች  በሪፌራል፣ ያኔት፣ አዳሬ እና ሞቲቴ ፉራ ሆስፒታሎች ህክምና እየተሰጣቸው ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል ፤ የሲዳማ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ተማሪዎች ተረጋግተው ወደ ግቢው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ፈተናውን አስመልክቶ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን መመሪያ እንዲከታተሉ አሳስቧል።

የተማሪ ወላጆችም ተማሪዎችን በማረጋጋት ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን የክልሉ መንግስት በጸጥታው ረገድ የሚጠበቅበትን እየተወጣ መሆኑን አስታውቋል።

#SRTA

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
2.3K views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ