Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi_merej
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.68K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-10-06 01:15:59
አሸባሪው እና ወራሪው የትሕነግ ለአፍሪካ ሕብረት በሰጠው ምላሽ!

፩. ደቡብ አፍሪቃ ለመሄድ ተስማምቷል:: ግን እንዴት ብየ እዚያ እንደምደርስ ቀድማችሁ ንገሩኝ ብሏል::

፪. የኦሊሴንጎ ኦባሳንጆን አሸማጋይነት እንደማይቀበል/እውቅና እንደማይሰጥ አረጋግጧል::

፫. ምዕራባውያን አደራዳሪ ሁነው እንደሚገቡ ቀድማችሁ አሳውቁኝ የሚል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል::

፬. Cessation of Hostilities/ ቅጥቀጣውን እና ዱላውን ሳትውሉ ሳታድሩ አስቁሙልኝ ብሏል:: ምነው ዝም አላችሁሳ?! ብሏል::

ሲጠቃለል የሽብር ቡድኑ የአፍሪካን ሕብረት የሰላም ግብዣ ተቀብያለሁም/አልተቀበልኩምም የሚል ምላሽ ሰጥቷል::

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
108 views22:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 20:01:11
አሜሪካ ለዩክሬን የ625ሚሊየን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ ማድረጓን ተከትሎ ሩሲያ አስጠነቀቀች

ዩናይትድ ስቴትስ 625 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ወደ ዩክሬን እየላከች ሲሆን ከነዚህም መካከል ተንቀሳቃሽ የሮኬት መሳሪያ እንደሚገኝበት ተገልጿል፡፡ደጋፉ ጦርነቱን ሊያባብስ ይችላል ስትል ሩሲያ አስጠነቅቃለች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማክሰኞ እለት ከዩክሬን አቻቸው ቮሎዲሚር ዘለንስኪን ጋር ዉይይት አድርገዋል፡፡ዘለንስኪ ዩክሬን በሀገሪቱ ደቡብ እና ምስራቃዊ ክፍል በሩሲያ የተያዙ ቦታዎችን ነፃ ለማውጣት የምታደርገውን ጥረት ቀጥላለች ሲሉ ለባይደን ተናግረዋል፡፡

ዜለንስኪ እንደተናገሩት የዩክሬንን ግዛት ለማስመለስ የተደረጉ ዉጊያዎች “ፈጣን እና ሀይለኛ” ዉጤት ያስገኙ መሆናቸውን በማንሳት በሁለት የጦር ግንባሮች ላይ በርካታ መንደሮችን ከሩሲያ ነጻ አዉጥተናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ባይደን ዋሽንግተን ለኪየቭ የምታደርገውን ድጋፍ ቀጣይነት እንዳለዉ ገልጸዋል፡፡

ሩሲያ አራት የዩክሬን ግዛቶች ላይ የህዝበ ዉሳኔ ምርጫ በማከናወን አካባቢዎችን በይፋ እንደምትቀላቀል ካስታወቀች በኋላ አሜሪካ ይህንኑ ድጋፍ አድርጋለች፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
1.5K views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 15:22:47
ደራሲና ጋዜጠኛ አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተለቀቁ!

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም

@wektawi_Merej
2.2K viewsedited  12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 12:31:06 ትሕነግ በጻድቃን በኩል ስለ ሰላም ለመነጋገርና ለመደራደር መጀመሪያ ግጭትን ማቆም (cessation of hostilities) ያስፈልጋል እያለች ነው።

የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ምንም ቅድመ ኹኔታ ሳያስፈልግ (ያለቅድመ ኹኔታ) ነው ድርድሩ መካኼድ ያለበት እያለ ነው። ማለትም ለድርድሩ ግጭት ማቆም (cassation of hostilities) ፣ ግጭት መግታት (truce)፣ ተኩስ ማቆም (ceasefire) ወዘተ የሚባሉ ቅድመ ኹኔታዎችን አልቀበልም እያለ ይመስላል።

መቼም ለአራተኛ ጊዜ ወረራ ለትሕነግ የመዘጋጃ ጊዜ መስጠት ማለት ከትሕነግ በከፋ መልኩ የሰሜን ወሎ፣የዋግኽምራና የሰሜን ጎንደርን ሕዝብ መጉዳትና መበደል ነው የሚኾነው።

የናይጀሪያና የቢያፍራን መንገድ መከተል አዋጭ ነው!

#Wubshet_Mulat

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
465 views09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 10:39:42 https://vm.tiktok.com/ZMFFgvJRL/
976 views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 09:06:50 የተመድ ሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበርያ ቢሮ ሃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ "የሰብዓዊ ዕርዳታ ሠራተኞቻችን ከትግራይ በሰላም መውጣት መቻላቸው አበረታች ዜና ነው" ሲሉ ትናንት በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል። ግሪፊትስ በጦርነቱ ሳቢያ በትግራይ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራዎች መቋረጣቸውን ገልጸው፣ "ወደፊትም ተጨማሪ የዕርዳታ ሠራተኞችን የማዘዋወር ሥራ ይቀጥላል" ብለዋል። ሃላፊው አያይዘውም፣ ሁሉም ወገኖች "አስከፊው ግጭት" እንዲያበቃ ለድርድር እንዲቀመጡ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ከጉዳት እንዲጠብቁ እና የዕርዳታ ሠራተኞችና ያልተገደበ ዕርዳታ እንቅስቃሴ እንዲኖር እንዲያደርጉ ጥሪ አድርገዋል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
1.3K views06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 08:41:51
መንግስት በየወቅቱ የሚያደርገውን የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ በሸቀጦችና በመሰል ምርቶች ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል

አንዳንድ የራሳቸውን ተጠቃሚነት ብቻ ለማረጋገጥ እቅድ ያላቸው ስግብግብ የህብረተሰብ ክፍሎች መሠረታዊ ሸቀጦች እና ምስል ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ሃላፊነት የጎደለው ህገ-ወጥ ድርጊት አብዛኛው የሃገሪቱ የህብረተሰብ ክፍላችን በተለይም በዝቅተኛው የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚኖሩ ወገኖቻችን ካሁን ቀደም ከሚያገኙት ዕለታዊ ገቢ በባሰ መልኩ የእለት ፍጆታቸውን መሸፈን ወደ ማይችሉበት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ እያስገደዳቸው ይገኛል፡፡

ስለሆነም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በዚህ የኢኮኖሚ አሻጥር ውስጥ ተሳትፎ የሆኑ አካላት ከዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት መታቀብ ይኖርባቸዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርም ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት በህገ-ወጥ አካላት ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡ በቀጣይም ከሚመለከታቸው የክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን መሰል እርምጃዎችን እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
1.3K views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 07:33:40
የቀድሞው የባህርዳር ከተማ ከንቲባ አረፉ

የቀድሞው የባህርዳር ከተማ ከንቲባ አቶ ሙሉቀን አየሁ በህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዮ። አቶ ሙሉቀን ከአቶ አየነው በላይ የከንቲባነት መንበሩን ተረክበው ዶ/ር መሃሪ ታደሰ እስኪመጡ ድረስ ባለው ጊዜ ባህርዳርን ለዓመታት መርተዋል።

አስክሬናቸውም ከደቂቃዎች በኋላ ከጠዋቱ 2:00 ባህርዳር ደጃዝማች በላይ ዘለፋ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳል ተብሏል።

ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
1.5K views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 05:45:43 #ለወላጆች

" ወላጆች ያምኑናል ብለን ተስፋ እንደርጋለን " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ


የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ከቤተሰባቸው ርቀው ነው ፈተናውን የሚወስዱት በዚህ ወቅት ስልክን ጨምሮ ምንም አይነት የመገናኛ ቁሳቁስ ይዘው መሄድ አይችሉም ፤ ተማሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት ባለመቻላቸው የሚፈጠር #የስነልቦና_ጫና ይኖር ይሆን ? ይሄ እንዴት ይታያል ? የወላጆች ኃላፊነትስ ምንድነው ?

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ (የትምህርት ሚኒስትር) ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የተናገሩት ፦

" .... ሆን ብለው ችግሮችን ለመፍጠር ካሰቡ ብዙ ምክንያቶችን ማድረግ ይቻላል ግን አሁን እነዚህ ልጆች ማትሪክ ሲያልፉ ከቤተሰቦቻቸው ወጥተው ሊኖሩ ነው አይደለም እንዴ ለረጅም ጊዜ ፤ ለአራት ቀን ለአምስት ቀን ሲሆን እንደውም በዛ እድሜ ላይ ያሉ ልጆች ደስ እያላቸው የሚሄዱ ነው የሚመስለኝ።

ይሄ አድቬንቸርም ነው ከቤት ወጥተው ፣ ዩኒቨርሲቲ ሄደው ይፈተናሉ ይሄ አዲስ ነገር ነው። በዚህ አመት ለሚያደርጉት ይሄ ነገር የተጀመረው የመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች ስለሚሆኑ ለልጆቻቸውም የሚነግሩት ነገር ይዘው ነው የሚሆነው ፤ ታሪካዊም ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ይሄ የተደረገው ፤ በእኛ ጊዜ ነው ይሄ የሆነው ፣ ይሄ ነገር ምን አለው የሚለውን ያያሉ።

በእኛ በኩል ዋና ኃላፊነታችን ሰላማቸው እንዲጠበቅ ማድረግ ፣ በምግብ ችግር እንዳይኖርባቸው ማድረግ ፣ ህክምና ማዘጋጀት በየዩኒቨርሲቲዎቹ ይሄንን እያዘጋጀን ነው።

ሰላም መግባታቸውን ፣ ችግር በሚኖር ጊዜ ለማሳወቅ ከየክልሉ ትምህርት ቢሮ ተወካዮች አሉ አብረው የሚመጡ ወደ ግቢ አይገቡም ፤ ግን ችግር በሚኖር ጊዜ ከእነሱ ጋር ግንኙነት እየተደረገ ለቤተሰቦቻቸው መንገር የሚቻልበትን መንገድ አስቀምጠናል።

ሁሉን ነገር ለማየት ሞክረናል ይሄ ነገር አዲስ ስለሆነ ቀላል የሎጅስቲክስ ስራ አይደለም አንድ ሚሊዮን የሚደርስ ሰው አንቀሳቅሶ ይሄን ማድረግ በተወሰነ ደረጃ እንደ ሀገርም ያውም ጦርነት እየተዋጋን ባለንበት ሁኔታ መንግስት ይሄን ማድረግ መቻሉ በእውነት የሚገርም ነው። እኛ ውስጥ ስላለንበትም እያየን ስለሆነ ነው ይሄን የምናገረው ቀላል የሎጅስቲክስ ስራ አይደለም።

እጅግ በጣም ብዙ ሰው ነው የሚሳተፍበት ወደ 8 ሺ የፌዴራል ፖሊስ ይሳተፍበታል ፣ ሰላሳ / አርባ ሺህ ፈታኞች ከየዩኒቨርሲቲው ወጥተው ይሳተፋሉ ፣ ብዙ ምግብ አብሳዮች ይሳተፋሉ። በአጠቃላይ ትልቅ ሀገራዊ እንቅስቃሴ ነው። እንደ ሀገርም ችሎታችንን አቅማችንን፣ በተወሰነ ደረጃ እየተጠናከረ ትላልቅ ነገሮችን ለመስራት ያለን ብቃት እየጨመረ የሚሄድበት ነው ፤ ስለዚህ ደስ የሚልም ነገር አለው።

ለቤተሰቦች የምንለው በተቻለን መጠን የልጆቻችሁን ኃላፊነት ወስደን ነው ይሄን ነገር የምንሰራው። እንደ ልጆቻችን ልንጠብቅ ፣ እንደ ልጆቻችን እንዳይራቡ እንዳይጠሙ ልናደርግ ፤ ምንም አይነት የደህንነት አደጋ ውስጥ እንዳይገቡ ተጠንቅቀን ነው ይሄንን ነገር የምናደርገው። ያ ማለት ግን ምንም ነገር አይፈጠርም ማለት አይደለም መቶ በመቶ ማረጋገጫ መስጠት አይቻልም።

ማንኛውም ተማሪ ወደዚህም ቦታ ባይመጣ ቤቱም ሆኖ ሊታመም ይችላል ግን በእኛ በኩል ከህክምና ጋር በተያያዘ የጤና ባለሞያዎችን በየቦታዎቹ ላይ አስቀምጠናል ፤ ችግር በሚኖር ጊዜ ልጆቹ ህክምና እንዲያገኙ።

ቁርሳ ፣ ምሳ እንዲሁም እራታቸውን እንመግባቸዋለን ፤ ምግብ እንኳን ስናዘጋጅ የሃይማኖት ፤ የባህል ነገሮችም እንዳይመጡ እሱን ሁሉ ጥንቃቄ እያደረግን ነው። ወላጆች ያምኑናል ብለን ተስፋ እንደርጋለን።

...ወላጆች ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው። ልጆቻቸው ወደ ፈተና በሚሄዱበት ጊዜ ትብብር ማድረግ ፤ ፈተናውን ለመፈተን በሚሄዱበት ጊዜ የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው እንዳይሄዱ ከቤት ነው ይሄ ነገር የሚጀምረው ምክንያቱም የ12 ዓመት ጥረት አፈር ነው የሚገባው አንድ የተከለከለ ነገር ይዘው ቢገቡ ፤ ስለዚህ እኛ እንደውም ፍተሻው ፖሊስ ጋር መጥቶ ከመድረሱ በፊት ቤት ወላጆች ናቸው አይተው መላክ ያለባቸው።

ወላጆች ለልጆቻቸው የሚሰጧቸው የሚያስፈልጋቸው ነገሮች ይኖራሉ ለምሳሌ ፦ እንደ ደረቅ ምግብ ድንገት ለሊት ሲያጠኑ ቢያስፈልጋቸው ቆሎም ይሁን ሌላ የሚሰጧቸው ነገር ካለ ፣ አንሶላ፣ ብርድልብስ እነዚህን እንደሚያዚዟቸው ሁሉ የዛን ያህል የተከለከሉ ነገሮችን እንዳይዙ መቆጣጠር አለባቸው፤ ይህንንም ያደርጋሉ ብለን እናምናለን።

ከዛ ውጭ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚጮኸውን አለመስማት ነው ፤ ምክንያቱም ዋነኛው ስራቸው በእንዲህ አይነት ነገር ማህበረሰብን ማሸበር እንደ ችሎታ እና እንደእውቀት የወሰዱ ጤነኛ ያልሆኑ ብዙ ሰዎች ያሉበት ዘመን ላይ ነው ያለነው።

ወላጆች የልጆቻችሁን ጉዳይ በሚመለከት በቀንጥታ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር፤ የምንነግራችሁ ቁጥሮች አሉ፣ የምንልካቸው የአካባቢው ትምህርት ተወካዮች አሉ በዛ በኩል መገናኘት ያስፈልጋል።

አንድ ነገር ቢፈጠር #በእርግጠኝነት የምንነግራችሁ ፤ ከእኛ ውሸት አትጠብቁ የሆነውን ነገር ይሄ ነው የሆነው ብለን እንነግራችኃለን። ምንም የምንደብቅበት ምክንያት የለም።

ይሄ የፖለቲካ ስራ አይደለም ፤ ይሄ የትምህርት ስራ ነው። የትምህርት ስራ ደግሞ ሁላችንንም የሚያገናኝ እና የሚያጣብቅ ስራ ነው።

ወላጅን ከአስተማሪዎች፣ አስተማሪዎችን ከአጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱና ከትምህርት አስተዳዳሪዎች ጋር የሚያይዘው ውስጣችን ለልጆቻችን ጤንነት ፤ ለልጆቻችን የእውቀት ጥማት እና ህይወትን ለማሻሻል የሚያደርጉትን ጥረት ከማገዝ በላይ ምንም ሌላ ነገር የለም ከዚህ የሚገኝ የፖለቲካ ጥቅም ሆነ ትርፍ የለም።

ይሄን ማወቁ ምንም የፖለቲካ ልዩነቶች እንኳን ቢኖሩ ትምህርትን የዛ መጠቀሚያ አናድርገው ፣ ትምህርትን ከዛ ውስጥ እናውጣው ትምህርት ስለልጆቻችን ነው። "

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej
1.8K views02:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 05:45:41
1.7K views02:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ