Get Mystery Box with random crypto!

መንግስት በየወቅቱ የሚያደርገውን የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ በሸቀጦችና በመሰል ምርቶች ላይ ጭ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

መንግስት በየወቅቱ የሚያደርገውን የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ በሸቀጦችና በመሰል ምርቶች ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል

አንዳንድ የራሳቸውን ተጠቃሚነት ብቻ ለማረጋገጥ እቅድ ያላቸው ስግብግብ የህብረተሰብ ክፍሎች መሠረታዊ ሸቀጦች እና ምስል ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ሃላፊነት የጎደለው ህገ-ወጥ ድርጊት አብዛኛው የሃገሪቱ የህብረተሰብ ክፍላችን በተለይም በዝቅተኛው የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚኖሩ ወገኖቻችን ካሁን ቀደም ከሚያገኙት ዕለታዊ ገቢ በባሰ መልኩ የእለት ፍጆታቸውን መሸፈን ወደ ማይችሉበት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ እያስገደዳቸው ይገኛል፡፡

ስለሆነም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በዚህ የኢኮኖሚ አሻጥር ውስጥ ተሳትፎ የሆኑ አካላት ከዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት መታቀብ ይኖርባቸዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርም ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት በህገ-ወጥ አካላት ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡ በቀጣይም ከሚመለከታቸው የክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን መሰል እርምጃዎችን እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej