Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wektawi_merej — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wektawi_merej
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.68K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-11-02 22:15:52
3.0K views19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 09:51:18
ሰሜን ኮሪያ ከባህር ድንበሯ በስተደቡብ በኩል ሚሳኤል ተኮሰች

ሰሜን ኮሪያ ወደ ደቡብ ድንበሯ ሚሳኤል የተኮሰች ሲሆን ከኮሪያ ክፍፍል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሁለቱን ሀገራት የባህር ድንበር ያቋረጠ ጥቃት ሆኗል፡፡አጭር ርቀት የሚምዘገዘግ ባለስቲክ ሚሳኤሉ በደቡብ ኮሪያ ምሥራቃዊ የባህር ዳርቻ እና በኡሌንግዶ ደሴት አቅራቢያ በሚገኝ ውሃማ ስፍራ ላይ ማረፉ ተሰምቷል፡፡

ዛሬ ጠዋት ፒዮንግያንግ ቢያንስ 10 ሚሳኤሎችን በምስራቅ የባህር ዳርቻዋ መተኮሷን የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡የሴኡል የጋራ የጦር አዛዦች እንደተናገሩት ሚሳኤሎቹ የተለያዩ አይነት ሲሆኑ ፕሬዚዳንቱ ለፒዮንግያንግ የአጸፋ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ ማዘዛቸውን ጨምረዉ ተናግረዋል።

ፒዮንግያንግ በዚህ ሳምንት በኮርያ ልሳነ ምድር አካባቢ ደቡብ ኮርያ እና አሜሪና የሚያደርጉትን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እንዲያቆሙ ካስጠነቀቀች ከአንድ ቀን በኋላ ሚሳኤል ተኩሳለች፡፡በትላንትናዉ እለት ሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ “ኃይለኛ” እርምጃን ያስከትላል ስትል ዝታ ነበር፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
1.5K views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 00:03:51
ተይዛለች

የገዛ ቀጣሪዋን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ወንጀሉ የተፈጸመው ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 10:45 ሰዓት ሲሆን ቦታው ደግሞ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው አስኮ ሊዝ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።

ተከሳሽ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ከምትሠራበት ከወ/ሮ ፋሲካ ተሾመ ቤት ሲሆን በመሃላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ሟችን በቡና ዘነዘናና በስለት የተለያዩ የሰውነት አካላቸው ላይ ጉዳት በማድረስ የመግደል ወንጀል ፈጽማለች።

ፖሊስ መረጃው ከህብረተሰቡ ከደረሰው በኋላ በአደረገው ብርቱ ፖሊሳዊ ክትትልና ምርመራ ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ከፈጸመች ከሦስት ቀናት በኋላ በቁጥጥር ስር

መዋሏን ገልጾ ምንም እንኳ የፖሊስ ተግባር ወንጀልን አስቀድሞ መከላከል ቢሆንም ተፈጽሞ ሲገኝም ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ተጠርጣሪዎችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚቻል ገልጿል።

ህብረተሰቡ የቤት ሠራተኞችን ሲቀጥር በቂ ዋስትናም ማቅረብ እንዳለባቸው ጭምር ሊያስገድድ እንደሚገባ ፖሊስ መልዕክቱን ያስተላልፋል።
@wektawi_Merej
Via AAP



3.2K views21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 20:30:59
"ጥቅምት 24-መቼም የማንረሳው ዕለት "~አረመኔውና አሸባሪው ህወሓት፤ ቀን በጠራራ ፀሐይ አንበጣ ሲያባርርና የትግራይን አርሶ አደር ሰብል ሲያጭድ የዋለውን የሰሜን ዕዝ፤ ምሽት በውድቅት ሌሊት በግፈኛው ወያኔ በሚዘገንን ሁኔታ ከጀርባው የተጨፈጨፈበትን ዕለት ከቶም አንረሳውም ~ሰሜን ዕዞች ሁሌም በልባችን ውስጥ ትኖራላችሁ

ክብር ለሰሜን ዕዝ ሰማዕታት

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
3.2K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 19:48:25 የትግራይ ህዝብ የህወሃት ሰላዮችና ጆሮ ጠቢዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል!
ህዝቡ ከተቀረው ኢትዮጵያዊ እህት ወንድሙ ጋር በፍቅርና በመቻቻል ለመኖር የግፈኞችን ስርዓተ ቀብር እያፋጠነው ነው!


ትግራዋይ ለሃምሳ አመታት እንደ መርግ ተጭኖት የኖረው የህወሓት አመለካከትና አገዛዝ ያንገሸገሸው ይመስላል፡፡ የሰሞኑ ጉምጉምታዎችም ይህን ይጠቁማሉ፡፡ አምጠን የወለድናቸው ለፍተን ያሳደግናቸው ልጆች በየጊዜው ለጦርነት ቢማገዱም በምቾት የሚንደላቀቁት ጥቂቶች ናቸው፤ ለልማት የሚውሉ ክንዶቻችን ነፍጥ ተሸክመው ወንድሞቻችንን ሲገድሉ ኖሩ፤ በዙሪያችን ከሚገኙ ሀገራትና ከጎረቤት ሕዝቦች ጋር የነበረን መልካም ግንኙነት እየሻከረ በክፉ አይን መተያየትና ቁርሾ በዛ የሚሉት በርካታ ትግራዋይ ለዚህ ሁሉ የዳረጋቸው ግፈኛው ህወሓት መሆኑን በየጓዳቸው የሚያነሱትና የሚብሰለሰሉበት ጉዳይ ሆኗል፡፡

እነዚህ ትግራዋይ ሰሞኑን ሰላም እንዲወርድ ካደረባቸው ልባዊ መሻት  በላይ ለአመታት የተጫናቸው ጥቂት የአድዋ አካባቢ ልሂቃን በበላይነት የሚዘውሩት   የህወሓት አገዛዝ እንዲያከትም ፀሎትና ምህላ መያዛቸው እየተነገረ ነው፡፡ ለፅዮን ማርያም ስለት ያስገቡ ጭምር መኖራቸውም መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ ሰቆቃው ይበቃ ዘንድ  በድርድር ስም ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀኑት አመራሮች በዚያው እብስ እንዲሉ፤ በክልሉ መሽገው ዜጎችን እንደ መያዣ የሚጠቀሙትም ብን ብለው  እንዲጠፉለት ከልቡ ይመኛል፡፡ መመኘት ብቻ ሳይሆን በየአካባቢው የሚደረጉትን የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችንም እያጠናከረ ቀጥሏል፡፡ ይህም የአሸባሪውን ቡድን አመራሮች ልብ በፍርሃት እያራደ ይገኛል፡፡

በተለይ በመቀሌ ዙሪያ በምትገኘው ኩያ፤ በእንደርታ፣በተንቤን ፣ወጂራት፣ ሽሬ እንዳስላሴና በሌሎችም አካባቢዎች ነዋሪዎች የአሸባሪውን ህወሓት ተላላኪዎችና ጆሮ ጠቢዎች እየለዩ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸው ፤ በወገን ኃይል በተያዙ አካባቢዎችም ለመሸሸግ የሚሞክሩትን እያጋለጡ ማስረከባቸው ትግራዋይ በጠመንጃ አፈሙዝ ተገዶ መተዳደሩ እንዳስመረረው ይመሰክራል፡፡

ያም ሆነ ይህ በርካታ ስፍራዎችን የተቆጣጠረውን ጥምር ጦር  ግስጋሴ የሚያስቆም ምንም ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ሰሞኑን ያስመዘገባቸው ወሳኝ ድሎች ያረጋግጣሉ፡፡ የምንከፍለው መስዋዕትነትም የትግራይ ሕዝብ ለአመታት እንደ መርግ የተጫነውን ስርዓት በማስወገድ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በነጻነት፣በእኩልነት፣በሰላም፣ በፍቅርና በመቻቻል አዲስ ምዕራፍ የሚጀመርበትን ቀን ለማብሰር ነውና አይቆጭም፤ አያስገርምም፡፡

በርካታ ትግራዋይ ይህን ተገንዝበው  መራር ትግል እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ይህ መስዋዕትነታቸው  በቅርቡ ፍሬ አፍርቶ በግፈኞች መቃብር ላይ በነጻነት፣በእኩልነትና በሰላም የሚኖሩባትን ኢትዮጵያ የማየት ጉጉታቸው እውን እንደሚሆን አንጠራጠርም  . . .
ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
3.3K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 14:57:15 የህወሓትና የፌደራል መንግስቱ የሰላም ንግግር እስከ ዕሮብ ተራዘመ!

በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያን ጦርነት በሰላም ይፈታል ተብሎ የታመነበት የሰላም ንግግር እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. መራዘሙ ተሰማ።

ቢቢሲ ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው በድርድሩ ስለተነሱ ሃሳቦች ምንም ፍንጭ ማግኘት አልተቻልም ያለ ሲሆን እሮብ ሲጠናቀቅ የጋራ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስነብቧል።

ከአንድ ሳምንት በፊት ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በፌደራል መንግስት እና ህወሓት መካከል የሰላም ንግግር መጀመሩ ይታወሳል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
3.6K views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 17:05:01 በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ትላንት በተፈፀመው የሽብር ጥቃት በትንሹ 100 ሰዎች ሲሞቱ 300 ሰዎች ተጎድተዋል

በሁለት መኪና በተፈፀመውን የቦንብ ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ተገድለዋል።

የሶማሊያ ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ፤ የትላንቱን የሽብር ጥቃት " ጭካኔ የተሞላበት እና የፈሪዎች ጥቃት " ሲሉ ገልፀው ድርጊቱን የፈፀመው ሽብርተኛው አልሸባብ መሆኑን አመልክተዋል።

በጥቃቱ ሲቪሎች መሞታቸውን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ የአልሻባብ የሽብር ቡድን ድርጊት ተስፋ ሊያስቆርጠን አይችልም ፤ ይልቅ ለአንዴና ለመጨረሻ ጌዜ ለማሸነፍ (አልሸባብን) ያለንን ቁርጠኝነት ያጠናክራል ሲሉ ገልፀዋል።

ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ የሽብር ጥቃቱ የተፈፀመበትን ቦታ በአካል የተመለከቱ ሲሆን በጥቃቱ በትንሹ 100 ሰዎች መገደላቸውን እና 300 የሚደርሱ ሰዎች መጎዳታቸውን ገልጸዋል።

የተጎዱትን ለማከም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህክምና ዶክተሮች እና የህክምና ቁሳቁሶችን እንዲልክ ተማፅነዋል።

ህዝቡም ወደ ሆስፒታል እየሄደ ደም እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

በትላንቱ እንዲሁም በሌሎች የአልሸባብ የሽብር ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ህፃናት ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚመቻች ፕሬዜዳንቱ ቃል ገብተዋል።

የትላንቱ የመኪና የቦምብ ጥቃት በመዲናዋ ሰው ከሚበዛባቸው መገናኛዎች ውስጥ በሚገኘው የትምህርት ሚኒስቴር ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ተነግሯል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
4.0K views14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 15:45:07
የትግራይ ሕዝብ ሕወሐት ከጫነበት ቀንበር ነጻ እንዲሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መሥዋዕትነት እየከፈለ ነው

የመከላከያ ሰራዊቱ መሥዋዕትነት የታሰበውን ግብ እንዲያሳካ የትግራይ ሕዝብ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

የመከላከያ ሠራዊቱን በመንከባከብ፣ ስንቅ በማቀበል፣ ስለተደበቁ ጀሌዎችና የጦር መሣሪያዎች መረጃ በመስጠት፣ መንገድ በመምራት እና አካባቢውን በመጠበቅ የትግራይ ሕዝብ ከሠራዊቱ ጋር ተሰልፏል።  ለዚህም መንግሥት ምስጋናውን ያቀርባል።

የትግራይ ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር ያለው ቅንጅት ሕወሐትን አስደንግጦታል። በዚህም የተነሣ "ምስለኔዎች ሊያስተዳድሩህ እየመጡ ነው" የሚል ውዥንብር እየነዛ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሕወሓት ጋር የታገለው የምስለኔ አስተዳደር እንዲቀር ነው። የምስለኔ አስተዳደርን በክልሎች ላይ እንደገና የዘረጋው ሕወሐት በመሆኑ።

የትግራይ ሕዝብ በራሱ ልጆች እንጂ በማንም ሊተዳደር አይገባም።

ፌዴራላዊ ሥርዓቱም ይሄንን አይፈቅድም። ሕወሐትም ይሄንን ያውቃል። ይደብቃል እንጂ። በመሆኑም የትግራይ ሕዝብ የሕወሐትን የምስለኔ ቴአትር፣ በምስለኔነት ለኖረው ለሕወሐት ትቶ፣ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር የጀመረውን ትብብር እንዲያጠናክር መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej
3.9K views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-29 16:43:22
#@wektawi_Merej:
ሰበር ዜና በዚህ ዘመን ቴሌግራም በጣም ተፅእኖ ፈጣሪ የመገናኛ ዘዴነው በመሆኑም ደርጅታችን የቴሌግራም ገፁን ተደራሽ ለማድረግ ባዘጋጃ ዘርፈ ብዙ የሽልማት ፓኬጅ ብዙዎችን በሽልማት እያንበሸበሸነው ፡፡ #ከድር_ጀማል ከጅማ የ150,000 እጅግ ዘመናዊ 2022  apple laptop ተሸላሚ ሆነ ታዲያ እርሶም የዚህ እድል ተሳታፊ ይሁኑ ፡፡ በጣም ቀላል ነው በዚህ ሊንክ  @wektawi_Merej  ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ ቀጥሎም ለ30 ሰዎች ይህን መረጃ ፎርዋርድ ያድርጉ በቀጥታ ለሽልማቱ እጩ ይሆናሉ ፡፡ አሁኑኑ ይሞክሩ ይሸለሙ መልካም እድል dw Amharic
@wektawi_Merej
4.8K views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 13:09:07
በሺዎች የሚቆጠሩ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎችና አመራሮች የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር ስፍራ በጨርጨር ተገኘ

በመከላከያ ሰራዊት መስዋዕትነት ከህወሓት እየተላቀቁ በሚገኙት አካባቢዎች የአሸባሪው ህወሓት ድብቅ ገመና መጋለጡን ቀጥሏል።

የሽብር ቡድኑ ቁንጮ አመራሮች አስገድደው በጦርነት ላሰለፏቸው ታጣቂዎች እንኳ ምንም አይነት ርህራሄ እንደሌላቸው በጨርጨር የተገኘው ጅምላ መቃብር ለዚህ ማሳያ ነው፡፡

ከጨርጨር ከተማ በስተምስራቅ በኩል በሺዎች የሚቆጠሩ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎችና የጦር አመራሮች የጅምላ መቃብር ስፍራ የተገኘ ሲሆን፥ ይህም የሽብር ቡድኑ ቁንጮ አመራሮች በትግራይ ህዝብ ደም በስልጣን ለመቆየት የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደሌለ ማሳያ ሆኗል፡፡

የጅምላ መቃብር ስፍራው መለያ ኮድ ያለውና በአንዳንዱ መቃብር ከ3 እስከ 5 አስከሬን በጋራ የተቀበረበት ሲሆን፥ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎቹን የቀበራቸው እንደ ኃላፊነታቸው እና ማዕረግ ደረጃቸው በመቃብራቸው ላይ ምልክቶችን በማድረግ ነው።

ተዋጊ የሚባለውን ኃይል በአንድ መቃብር ውስጥ ከ3 እስከ 5 እስከሬን እንዲሁም ለብቻቸው ኮድ ተሠጥቷቸው የተገኙ የመቃብር ስፍራዎች ደግሞ የአመራሮች መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ከዚህ በተጨማሪም የሞቱ የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች በአንድ ዋሻ ውስጥ አስክሬናቸው በሬሳ ሳጥን ውስጥ የተገኘ ሲሆን፥ በዋሻ ውስጥ በሬሳ ሳጥን የተገኙት አስከሬኖች በልዩ ሁኔታ የተቀመጡ በመሆኑ ውጊያውን ሲመሩ የነበሩ የሽብር ቡድኑ አመራሮች እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።

የተገኘው የጅምላ መቃብር ስፍራ በሶስት የተከፈለ ሲሆን፥ የመጀመሪያው የቡድኑ ታጣቂዎች የተቀበሩበት እንዲሁም ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ የሽብር ቡድኑ መካከለኛ አመራሮች እና ጦርነቱን ሲመሩ የነበሩ ከፍተኛ አመራሮች የተቀበሩበት ስፍራ ነው፡፡
@wektawi_Merej
5.0K views10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ