Get Mystery Box with random crypto!

ሰሜን ኮሪያ ከባህር ድንበሯ በስተደቡብ በኩል ሚሳኤል ተኮሰች ሰሜን ኮሪያ ወደ ደቡብ ድንበሯ ሚሳ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

ሰሜን ኮሪያ ከባህር ድንበሯ በስተደቡብ በኩል ሚሳኤል ተኮሰች

ሰሜን ኮሪያ ወደ ደቡብ ድንበሯ ሚሳኤል የተኮሰች ሲሆን ከኮሪያ ክፍፍል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሁለቱን ሀገራት የባህር ድንበር ያቋረጠ ጥቃት ሆኗል፡፡አጭር ርቀት የሚምዘገዘግ ባለስቲክ ሚሳኤሉ በደቡብ ኮሪያ ምሥራቃዊ የባህር ዳርቻ እና በኡሌንግዶ ደሴት አቅራቢያ በሚገኝ ውሃማ ስፍራ ላይ ማረፉ ተሰምቷል፡፡

ዛሬ ጠዋት ፒዮንግያንግ ቢያንስ 10 ሚሳኤሎችን በምስራቅ የባህር ዳርቻዋ መተኮሷን የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡የሴኡል የጋራ የጦር አዛዦች እንደተናገሩት ሚሳኤሎቹ የተለያዩ አይነት ሲሆኑ ፕሬዚዳንቱ ለፒዮንግያንግ የአጸፋ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ ማዘዛቸውን ጨምረዉ ተናግረዋል።

ፒዮንግያንግ በዚህ ሳምንት በኮርያ ልሳነ ምድር አካባቢ ደቡብ ኮርያ እና አሜሪና የሚያደርጉትን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እንዲያቆሙ ካስጠነቀቀች ከአንድ ቀን በኋላ ሚሳኤል ተኩሳለች፡፡በትላንትናዉ እለት ሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ “ኃይለኛ” እርምጃን ያስከትላል ስትል ዝታ ነበር፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej