Get Mystery Box with random crypto!

የታደሰ ወረደ (ጄ) መግለጫ አጠሬራ! ጀነራል ታደሰ ወረደ በትናትናው እለት በትግርኛ ለአንድ ሰአ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የታደሰ ወረደ (ጄ) መግለጫ አጠሬራ!

ጀነራል ታደሰ ወረደ በትናትናው እለት በትግርኛ ለአንድ ሰአት ከአምስት ደቂቃ የቆየ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫው ከ3ቀናት በፊት የክልሉ ፕሬዚዳንት ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ከሰጡት የተቃረኑ ብዙ ሃሣቦች አሉት።

ለምሳሌ ደብረጽዮን የኢትዮጵያ መከላከያና ሻቢያ ወደ ትግራይ የገቡበትን አላማ ሲያብራራ

"አላማቸው አንድና አንድ የትግራይን ህዝብ ከምድረ ገጽ ለማ*ጥፋት ነው" ብሏል።

ጄኔራል ታደሰ ወረደ ግን የሁለቱን አላማ ነጣጥሎ ይመለከተዋል።

"የኤርትራ ሃይሎች አላማ የትግራይን ህዝብ ከቤት ንብረቱ በማፈና*ቀል ግማሹ ወደ አማራ ክልል ገብቶ በስደተኛነት ተበት*ኖ እንዲኖር ቀሪው ደግሞ በትግራይ በየሰፈሩ በሚተከሉ ድንኳኖች ውስጥ ተበትኖ እንዲኖር ነው" ብለዋል።

"በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መከላከያ አላማ ደግሞ የትግራይ ሃይሎችን ትጥቅ አስፈትቶ ጸጥ ረጭ አድርጎ ትግራይን በምስለኔ ማስተዳደር ነው። ለዚህም ኦሮሞውን አለሙ ስሜ ትግራይን እንዲያስተዳድር ሹሞቷል" ይላል ታደሰ።

ታደሰ ወረደ ከዚህ በፊት ከነበረው ቃለመጠይቆች በተለየ ተቀዛቅዞና ባልተለመደ መልኩ የጦርነቱ አከባቢዎች ሁሉ እየተዘነጉት ሲጨነቅ ይታያል። አድዋና አክሱም ወይም ከተሞች ስለተያዙብን ጦርነቱን ተሸነፍን ማለት አይደለምም ብሏል።

በኔ መረዳት የትግራይ ሃይሎች በዚህ ሰአት በአንድ እዝ ስር የነበራቸው ገመድ ተበ*ጣጥሷል። ምናልባትም እየተዋጉ ያሉት እነ ታደሰ ወረደ Plan B ብለው ባስቀመጡት ከተበተኑ በኋላ ሁሉም በየጥሻው የሽምቅ ውጊያ እንዲያደርግ በሚለው ነው። ታደሰም በንግግሩ የሚጠቅሳቸው የውጊያ ቦታዎች እዚህ ግባ የማይባሉና በኢትዮጵያ ጥምር ጦር ስር የሚገኙ ናቸው። ከጠቀሳቸው የራያውን የባላና የዋጉን ዛታ ለአብነት መጥቀስ ይቻላል። መቶ በማይሞሉ ታጣቂዎች ለሰአታት ያልቆየን የሽምቅ ውጊያ እንደ ትልቅ ጦርነት አድርጎ አቅርቦታል።

የሰላም ድርድሩን በተመለከተ

ለቀረበለት ጥያቄ "ሰላም ከተገኘ የኛም የመጀመሪያ አማራጭ ነው። አሁን ላይ በሚካሄደው ድርድር ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ የኤርትራን ጦር ያስወጡልን፣ የኢትዮጵያ መከላከያና የአማራ ሃይልም ተኩሱን ያቁም፣ ከዛ በኋላ ለሰላም መደላድል ይሆናል መነጋገር እንችላለን።" ብሏል።

በመጨረሻ ባስተላለፈው መልዕክት

ለአማራ ህዝብ
"የአማራ ሃይሎች በተለይ ልዩ ሃይሉ፣ ፋኖና ሚሊሻው ወደ ትግራይ በሃይል ገብተው እየተዋጉን ነው። ከንድ ወር በፊት በነበሩት ውጊያዎች የአማራ ሃይሎች ብዙም አልነበሩም፣ አሁን ግን ፋኖም ልዩ ሃይሉም ሚሊሻውም በተለያዩ ቦታዎች ፊለፊት እየተዋጉን ነው።

ለምሳሌ
❶ ዛታን የያዘው የአማራ ፋኖና ሚሊሻ ነው፣

❷ በሪ ተኽላይን ተዋ*ግቶ ከዛም አልፎ ስንኮማጀት ግንባር ላይ ቆርጦ ለመግባት አሁንም እየተ*ዋጋ ያለው የአማራ ልዩ ሃይል ነው፣

❸ ጨርጨር ላይ እየ*ተዋጋ ያለው ብቻውን የአማራ ልዩ ሃይል ነው፣

❹ በተለይ በሪተኽላይ ላይ የተሰማሩት ሁለቱ "መክት አማራ እና ሪፐፕሊካን ጋርድ " የተባሉት ናቸው። ይህ መክት አማራ የሚባለው ጦር በውጭ ሃይሎች የሰለጠነ ሃይል ነው። እነዚህ ሆነው ነው መስመሩን የቆ*ረጡት። ይህ መክት አማራ የተባለው ሃይል ከልዩ ሃይሉ የተለየ ሲሆን በኮማንዶነት ደረጃ የሰለጠነና የተደራጀ ነው።  ሽራሮንም ከፊት ሆኖ የገባው ይሄው ሃይል ነው።

❻ ባሁኑ ሰአት የአማራ ሃይሎች በተለየ መልኩ ከፊት ናቸው። ለምን? እኔ ጥያቄ ነው ምጠይቃቸው። ከተቻለ ወላጆቻቸው ይመልሱልን። ከትግራይ ይውጡ።

የአማራ አመራሮች የአማራ ወጣቶች ትግራይ ገብተው ወንጀል እንዲፈጽሙ እያደረጓቸው ነው። ይሄ ወንጀል ለነገ በወንድማማችነት ለመቀጠል ከባድ ጠባሣ ይጥላል። ጊዜ ያልፋል፣ የአማራ ልሂቃን ይሄንን አስበውበት ቶሎ ማስቆም ካልቻሉ አሁን ያለው የአማራ በታሪክ ተጠያቂ ይሆናል። " (ታደሰ ሸዋ ድረስ ገብተው ስለጨፈጨፉ የትግራይ ሃይሎች ትንፍሽ አላለም)

ለኤርትራ ህዝብ
"እኛ የኤርትራ ህዝብ ጋር ያለን ግንኙነት (እንደሌላው አይደለም) በደም ነው። ልጆቻችሁን የራሳቸውን ህዝብ ለማፈናቀል ለመግደል እንዳይመጡ ሰብስቧቸው። እዚህ እየገቡ እያለቁም ነው።"

ለኦሮሞዎች
"እናንተ ለኛ ምስለኔ የምትመድቡልን አይደለንም። ታሪክን ወደኋላ ሄዳችሁ እዩ። በቀዳማይ ወያኔ ጊዜ አማራ ምስለኔ ንጉሱ አማራ ምስለኔ ልከውብን ነው ካልአይ ወያኔ የተፈጠረው። ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አፋር አማራ ሌላም ብሔረሰብ ወደ ክልላችን ለማስተዳደር የተመረጡ ፖሊሶቻችሁን ከልክሏቸው..."

ለትግራይ ህዝብ
"ሁላችንም ከዚህ ከፍ ባለ መልኩ ለፍልሚያ መዘጋጀት አለባችሁ።"

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej