Get Mystery Box with random crypto!

የሸኔ አባላት ከአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ጋር ተሰልፈው በግንባር ሲዋጉ ተያዙ የሸኔ አባላት ከ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የሸኔ አባላት ከአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ጋር ተሰልፈው በግንባር ሲዋጉ ተያዙ

የሸኔ አባላት ከአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ጋር ተሰልፈው በግንባር ሲዋጉ መያዛቸው ተገለጸ።
ሁለቱ አሸባሪዎች ህወሓት እና ሸኔ ኢትዮጵያን ለማፍረስ አብረው ለመሥራት እንደተስማሙና እየሠሩ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወቃል። አሸባሪው ህወሓት በሁለት ዙር በከፈተው ጦርነትና በፈጸመው ወረራ በአማራ እና አፋር ክልሎች ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል፤ ንጹሀንን ገድሏል፤ ከአርሶ አደሩ ጓዳ ሽሮና በርበሬ ሳይቀር ዘርፏል።
አሁንም  በተመሳሳይ ህወሓት እና የግብር አጋሩ ሸኔ  በፈጸሙት ሦስተኛ ዙር ወረራ ተመሳሳይ ጥፋት እየፈጸሙ መሆናቸው ይታወቃል። ይህንንም በሠነድ ሳይቀር አስደግፈው እየሰሩበት መሆኑን ከተጋለጠው ሚስጢራዊው ሠነድ ለመረዳት ተችሏል። ከባቲ ተነስተው የሽብር ቡድኑን የተቀላቀሉት የሸኔ አባላት ከሌላኛው የጥፋት ኃይል ህወሓት ጋር ተሰልፈው ሲዋጉ እንደነበር መናገራቸውን የኢፕድ ዘገባ አመላክቷል።
ህወሓት ባቲ ከተማን ከወረረ በኋላ ተሸንፎ አካባቢውን ለቆ ሲሄድ ከግብረ አበሩ ሸኔ ጋር በመተባበር ተዋጊዎችን መመልመሉን እነዚሁ እጃቸውን የሰጡት ታጣቂዎች አስረድተዋል። በኋላም ወደ ትግራይ በማምራት ለወራት ወታደራዊ ስልጠና መውሰዳቸውን የገለጹት ታጣቂዎቹ፤ በመጨረሻም ከህወሓት አመራሮች የቀረበላቸውን ትጥቅ ይዘው አፋርና አማራ ክልል ላይ ወረራ ሲፈጸም መሳተፋቸውን ነው የገለጹት።
አላማ ለሌለው ጦርነት ህይወታቸውን መገበር እንደሌለባቸው የተረዱት የሽብርተኛው ሸኔ አባላት ግን መሹለኪያ መንገድ በማመቻቸት ለመከላከያ  ሠራዊት ዕጃቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል። ሠራዊቱም በተገቢው መንገድ እየተንከባከባቸው መሆኑን ዕጃቸውን የሠጡት የሽብር ቡድኑ አባላት ገልጸዋል።
    
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej