Get Mystery Box with random crypto!

ተጀመረ Safaricom ከች ብሏል አማራጭ ተገኘ እስቲ የዋጋ ሂደቱ ምነኛ ለተጠቃሚ ቅ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

ተጀመረ

Safaricom ከች ብሏል

አማራጭ ተገኘ

እስቲ የዋጋ ሂደቱ ምነኛ ለተጠቃሚ
ቅናሽ ይሆን አስረዱን። ምነኛ ዝቅ ብላችሁ ይሆን አሳውቁን።

ተወዳዳሪ ሲኖር ሸጋ ነው
በመሀል ህዝቡ ተጠቃሚ ይሆናል።

ናይጄሪያ 6 አማራጭ አይችያለሁ
ሰዉ እንደአቅሚቲ በተመቸው ይጠቀማል።

ሳፋሪኮም የተባለው የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ዙሪያ በሚገኙ አስር
ከተሞች የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን ያካሄደው ሳፋሪኮም ዛሬ በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል።

የአዲስ አበባ 07 ኔትወርክ ደንበኞች የ4G ዳታ፣ የድምፅ ጥሪ እና የጽሁፍ መልዕክት አገልግሎቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ደንበኞች 700 ላይ በመደወል የሳፋሪኮም የጥሪ ማዕከልን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤ አገልግሎቶቹም በ5 ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሱማሊኛ፣ ትግሪኛ እና እንግሊዝኛ የሚሰጡ ይሆናል ተብሏል።

እናመሰግናለን !! በርቱልን

➨እስቲ እኛም እጃቸው ከምን መሆኑን እናጤናለን። ያው ለተጠቃሚው ምነኛ ቅናሽ ይሆን።

ጉዞ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ወደፊት ይሁን !



መ/ር አካሉ አብራሐም

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
@wektawi_Merej