Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Update
Silver
Platinum
Golden
Choleraupdate
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.37K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 141

2023-01-11 17:34:04
https://t.me/Mikimobiles

እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ
       MIKI_MOBILE_AND_LAPTOP

በአልን ምክንያት በማድረግ ስልኮት ላይ መጠነኛ ብር በመጨመር በተሻለ ዋጋ የተመረጡ ስልኮችን ይውሰዱ::
ከስር የሚገኘውን የቴሌግራም
ቻናል በመቀላቀል ORIGINAL ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ::

https://t.me/Mikimobiles
16.5K views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 17:25:30
ኢትዮጵያ የሥጋ ምርቷን ወደ ቻይና እና ኢንዶኔዥያ ገበያዎች ለመላክ የሚያስችሉ የዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነች መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ በዓመት ከ200 ሺህ ቶን በላይ የሥጋ ምርት ለውጭ ገበያ የማቅረብ አቅም ቢኖራትም አሁናዊ አቅርቦቷ ግን ከ22 ሺህ ቶን አይበልጥም። በዚህም የሥጋ ምርት መዳረሻ ከሆኑ የመካከለኛው ምስራቅ አገራት በተጨማሪ ወደ ሩቅ ምስራቅ ገበያ ለማስፋት እየሰራች መሆኗ ተገልጿል።

ከሦስት ዓመታት ወዲህ በዘርፉ ላይ በተሰሩ ሥራዎች ከመካከለኛው ምሥራቅ በተጨማሪ ወደ ቬትናም እና ኮሞሮስ የሥጋ ምርቷን ማቅረብ መጀመሯ ተጠቅሷል።

በተያዘው በጀት ዓመትም 28 ሺህ ቶን የሥጋ ምርት ለመላክ መታቀዱ የተገለጸ ሲሆን፤ ባለፉት ስድስት ወራት 7 ሺህ 200 ቶን ለውጭ ገበያ በማቅረብ 50 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገቢ ተገኝቷል፤ ይሁንና ካባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2 ሺህ 800 ቶን ቅናሽ ማሳየቱን ተነግሯል። (ENA)

@tikvahethmagazine
16.3K viewsedited  14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 15:12:16
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በጂኦሎጂ እና ተዛማጅነት ባለው የትምህርት መስክ አመልካቾችን አወዳድሮ በኮንትራት መቅጠር ይፈልጋል።

መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት /5/ ተከታታይ የስራ ቀናት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን አስታውቋል።

ዝርዝሩን ይመልከቱ https://telegra.ph/Notice-01-11

@tikvahethmagazine
20.5K viewsedited  12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 13:14:58
የኢትዮጵያን ጨምሮ የፌስቡክ ይዘቶችን የሚቆጣጠረው ተቋም አገልግሎቱን ሊያቆም ነው።

ኢንስታግራም፣ ፌስቡክን እና ዋትስአፕን የሚያስተዳድረው ሜታ ይዘት ተቆጣጣሪ የሆነው የምሥራቅ አፍሪካው ድርጅት፣ ሳማ በፈረንጆቹ ሚያዝያ ወር መጨረሻ የይዘት ቁጥጥር ሥራውን ለማቆም ማቀዱን አስታወቀ።

ሳማ በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኩ ላይ የሚሰራጩ ከጥላቻ አዘል ይዘቶች እስከ አሰቃቂ የሆኑ ምስሎችንና ቪዲዮዎችን ላይ ቁጥጥር ሲያደርግ ነበር።

የሜታ ቃል አቀባይ፣ ሳማ የይዘት ቁጥጥር አገልግሎቱን ለማቆም ያሳለፈውን ውሳኔ እንደሚያከብሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስአፕ ባለቤት የሆነው ሜታ፣ ሽግግሩ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኩ ላይ ተፅዕኖ እንዳይኖረው እንደሚያረጋግጥ ገልጿል። (BBC)

@tikvahethmagazine
23.1K viewsedited  10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 12:18:18
#AfricaCDC

ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግና የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋቂ የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማዕከልን የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ መርቀው መክፈታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ማዕከሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሌ ጋርመንት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሊዝ ነፃ ባቀረበው በ90 ሺሕ ሜትር ስኩዌር መሬት ስፋት ያለው መሬት ላይ የሚገነባ ሲሆን የህንፃው ግንባታ ብቻ በ40 ሺሕ ሜትር ስኩዌር ላይ ያረፈ ነው፡፡

የቻይና መንግሥት 80 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት የግንባታውን ሙሉ ወጪ ሸፍኗል።

የማዕከሉ ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ማለትም አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ የማጠቃለያ ሥራዎች እየተካሄደ ሲሆን በቅርቡ ተጠናቆ ማዕከሉ ወደ ሥራ ይገባል ተብሏል።

በሕዳር ወር 2015 ዓ.ም የተጀመረው ግንባታው በ25 ወራት ሰርቶ ለማጠናቀቅ ታቅዶ የነበር ሲሆን የማዕከሉ ግንባታ የኮቪድ 19 ጫና ምክንያት መዘግየቶች ቢየጋጥሙትም ሥራው በተሳካ ሁኔታ መጓዙ ነው የተመለከተው።

የማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጫም ከኢትዮጵያ ውጪ እንዲሆን ምዕራባውያኑ አገሮች ከፍተኛ ጫና ሲያደርጉ እንደነበር አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ዲፕሎማትን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቧል።

በማዕከሉ ግንባትና ቀጣይ ተልዕኮ ውስጥ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማዕከሉ ተልዕኮ ማስፈጸሚያ ብለው፣ በእጅ አዙር 1.3 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ለአፍሪካ ኅብረት እንዳቀረቡ ዲፕሎማቱ ገልጸዋል። 

ማዕከሉ ተጠናቆ ሥራ ሲጀምር፣ አፍሪካ በየዓመቱ እያጋጠማት ያለውን ከ100 በላይ ተላላፊ በሽታዎችና ወረርሽኞች በራሷ አቅም መቆጣጠር ያስችላታል ተብሏል።

@tikvahethmagazine
4.8K views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 12:17:57
በምዝገባ ላይ እንገኛለን!

ነጻ የንግድ ቀጣና እና ሎጂስቲክስ

ሥልጠናው፡-
-  ስለ ነጻ የንግድ ቀጣና የአሠራር ሥርዓት፣ ጥቅሞች እና የሌሎች አገራት ተሞክሮዎች ይዳስሳል፡፡
-  ማኅበራችን ካሉት ዓለም አቀፍ አጋሮች መካከል አንዱ ከሆነውና በሆላንድ ከሚገኘው ፓም ኔዘርላንድስ ሲኒየር ኤክስፐርትስ ከተሰኘው የባለሙያዎች ተቋም ጋር በመተባበር ይሰጣል፡፡
-  በተለይ በንግድና ሎጂስቲክስ የሥራ መስክ ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ጠቀሜታው ጉልህ ነው፡፡
-  ለዚህ ሲባል ከሆላንድ በሚመጡ ባለሙያ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

መስፈርት
-  የመጀመሪያ ዲግሪ በማንኛውም የትምህርት መስክ (ከሎጂስቲክስ ጋር ተያያዥነት ያለው የሥራ ልምድ ተመራጭነት ይኖረዋል)
-  የእንግሊዝኛ ቋንቋን በአግባቡ መረዳት የሚችል/የምትችል

ለመመዝገብ
ቀጥሎ ያውን ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) በመጠቀምና ተገቢውን መረጃ በመሙላት መመዝገብ ይቻላል፡፡
https://www.effsaa.org/training-program-on-free-trade-zone-and-logistics-in-collaboration-with-pum-netherlands-senior-experts/

ለተጨማሪ መረጃ
በ +251 115 589045 / +251 903 182525 ላይ ይደውሉልን
ወይም የቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EFFSAAOfficial
4.3K views09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 12:17:48
Samsung  Galaxy  note  3
አዲስ  አንደታሸገ 
32  gb
3 gb ram
ዋጋ 4000  ብር በማከፋፈያ ዋጋ
Call me
0909255008
0912739699
ተጨማሪ ስልኮችን  ለመመልከት
አና ስልክ ለመሽጥ ከፈለጉ ቤተሰብ ይውኑ
https://t.me/used_phone_ethiopia
4.3K views09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 16:34:08
#Update

የኮሌራ ወረርሽኝ ከተከሰተባቸው የኦሮሚያ ክልል ሶስት ዞኖች ችግሩ  በከፋባቸው ባሌ ዞን አካባቢዎች ሁለት ወረዳዎች ተለይተው ከፊታችን ሐሙስ ጀምሮ ክትባት እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡

ወረርሽኙ የመቀነስና የመጨመር ባህሪ በማሳየቱ የባሌ ዞን ወረዳዎች በሆኑት በርበሬና ጎሮ 79ሺህ ዶዝ የኮሌራ ክትባት በመዘጋጀቱ የንጽህና ችግር እና የውሀ አቅረቦት ችግር ባለባቸውና በጣም በተጎዱ በተመረጡ ቀበሌዎች ላይ እንደሚሰጥ ተነግሯል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡

እስካሁን ድረስ በሶስቱ ዞኖች 700 ሰዎች በኮሌራ መያዛቸው የተነገረ ሲሆን 12 ሰዎች በበሽታው ህይወታቸው ማለፉን ነው ዘገባው ያመላከተው፡፡

እንደሀገር የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ ስጋት ያለባቸው 80 ወረዳዎች የተለዩ ሲሆን 25 በክልሉ የሚገኙ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከዚህ ቀደም በክልሉ የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን እንዳሁም የመጀመሪያው የኮሌራ በሽታ በዚህ ዓመት በባሌ ዞን ነሃሴ 21 መገኘቱ እንደተጠቆመና የስደተኛ መጠለያ የሚገኝባቸውን ጨምሮ 114 ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 459 ሺ ሰዎችም አስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ መባሉን መዘገባችን ይታወሳል።

@tikvahethmagazine
18.2K viewsedited  13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 16:30:43
ጂቡቲ የሳተላይት እና የሮኬት ማስወንጨፊያ ማዕከል ልትገነባ ነው።

ጂቡቲ ለሳተላይቶች እና ለሮኬቶች ማስወንጨፊያ የሚሆን መሠረተ ልማት ግንባታ ለማከናወን ሆንግ ኮንግ ኤሮስፔስ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ከተባለ ተቋም ጋር የሀገሪቱ ባለሥልጣናት መፈራረማቸውን የሀገሪቱ ዜና ወኪል ዘግቧል።

በዚህ ስምምነት መሠረት ከሳተላይት እና ሮኬት ማስወንጨፊያ ማዕከሉ ጋር በተያያዘ የሚያስፈልጉ የግንባታ አቅርቦቶችን ለማቀላጠፍ በሰሜናዊ የአገሪቱ ኦቦክ ክፍል ውስጥ ወደብ እና አውራ ጎዳና የሚገነባ ይሆናል።

የመሠረተ ልማቱ አጠቃላይ የግንባታ ሥራውም 1 ቢሊዮን ዶላር ያህል የሚያስወጣ ሲሆን በአምስት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

የሳተላይት ማስወንጨፊያ ማዕከሉ ግንባታ ከተጠናቀቀ በኋላ ለ30 ዓመታት ያህል በሆንግ ኮንጉ ኩባንያ እና በጂቡቲ በጋራ የሚተዳደር ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ ጂቡቲ ማዕከሉን ሙሉ ለሙሉ ትረከበዋለች ተብሏል።

በአፍሪካ የሳተላይት ሮኬት ማስወንጨፊያ በሰባት አገራት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እነሱም በኬንያ፣ በግብፅ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በሊቢያ፣ በሞሪታኒያ፣ በዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ በአልጄሪያ ውስጥ ነው የሚገኙት።

ጂቡቲ ለመገንባት የተነሳችው የሳተላይት እና የሮኬት ማስወንጨፊያ ማዕከል ከአምስት ዓመታት በኋላ ሲጠናቀቅ በአህጉሪቱ ከሚገኙ ተመሳሳይ ማዕከላት አንዱ ይሆናል።

Credit : BBC, Ismail Omar Guelleh

@tikvahethmagazine
16.3K viewsedited  13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 16:30:29
https://t.me/Mikimobiles

እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ
MIKI_MOBILE_AND_LAPTOP

በአልን ምክንያት በማድረግ ስልኮት ላይ መጠነኛ ብር በመጨመር በተሻለ ዋጋ የተመረጡ ስልኮችን ይውሰዱ::
ከስር የሚገኘውን የቴሌግራም
ቻናል በመቀላቀል ORIGINAL ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ::

https://t.me/Mikimobiles
13.2K views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ