Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያን ጨምሮ የፌስቡክ ይዘቶችን የሚቆጣጠረው ተቋም አገልግሎቱን ሊያቆም ነው። ኢንስታግራም፣ | TIKVAH-MAGAZINE

የኢትዮጵያን ጨምሮ የፌስቡክ ይዘቶችን የሚቆጣጠረው ተቋም አገልግሎቱን ሊያቆም ነው።

ኢንስታግራም፣ ፌስቡክን እና ዋትስአፕን የሚያስተዳድረው ሜታ ይዘት ተቆጣጣሪ የሆነው የምሥራቅ አፍሪካው ድርጅት፣ ሳማ በፈረንጆቹ ሚያዝያ ወር መጨረሻ የይዘት ቁጥጥር ሥራውን ለማቆም ማቀዱን አስታወቀ።

ሳማ በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኩ ላይ የሚሰራጩ ከጥላቻ አዘል ይዘቶች እስከ አሰቃቂ የሆኑ ምስሎችንና ቪዲዮዎችን ላይ ቁጥጥር ሲያደርግ ነበር።

የሜታ ቃል አቀባይ፣ ሳማ የይዘት ቁጥጥር አገልግሎቱን ለማቆም ያሳለፈውን ውሳኔ እንደሚያከብሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስአፕ ባለቤት የሆነው ሜታ፣ ሽግግሩ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኩ ላይ ተፅዕኖ እንዳይኖረው እንደሚያረጋግጥ ገልጿል። (BBC)

@tikvahethmagazine