Get Mystery Box with random crypto!

#AfricaCDC ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋ | TIKVAH-MAGAZINE

#AfricaCDC

ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግና የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋቂ የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማዕከልን የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ መርቀው መክፈታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ማዕከሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሌ ጋርመንት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሊዝ ነፃ ባቀረበው በ90 ሺሕ ሜትር ስኩዌር መሬት ስፋት ያለው መሬት ላይ የሚገነባ ሲሆን የህንፃው ግንባታ ብቻ በ40 ሺሕ ሜትር ስኩዌር ላይ ያረፈ ነው፡፡

የቻይና መንግሥት 80 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት የግንባታውን ሙሉ ወጪ ሸፍኗል።

የማዕከሉ ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ማለትም አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ የማጠቃለያ ሥራዎች እየተካሄደ ሲሆን በቅርቡ ተጠናቆ ማዕከሉ ወደ ሥራ ይገባል ተብሏል።

በሕዳር ወር 2015 ዓ.ም የተጀመረው ግንባታው በ25 ወራት ሰርቶ ለማጠናቀቅ ታቅዶ የነበር ሲሆን የማዕከሉ ግንባታ የኮቪድ 19 ጫና ምክንያት መዘግየቶች ቢየጋጥሙትም ሥራው በተሳካ ሁኔታ መጓዙ ነው የተመለከተው።

የማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጫም ከኢትዮጵያ ውጪ እንዲሆን ምዕራባውያኑ አገሮች ከፍተኛ ጫና ሲያደርጉ እንደነበር አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ዲፕሎማትን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቧል።

በማዕከሉ ግንባትና ቀጣይ ተልዕኮ ውስጥ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማዕከሉ ተልዕኮ ማስፈጸሚያ ብለው፣ በእጅ አዙር 1.3 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ለአፍሪካ ኅብረት እንዳቀረቡ ዲፕሎማቱ ገልጸዋል። 

ማዕከሉ ተጠናቆ ሥራ ሲጀምር፣ አፍሪካ በየዓመቱ እያጋጠማት ያለውን ከ100 በላይ ተላላፊ በሽታዎችና ወረርሽኞች በራሷ አቅም መቆጣጠር ያስችላታል ተብሏል።

@tikvahethmagazine