Get Mystery Box with random crypto!

ጂቡቲ የሳተላይት እና የሮኬት ማስወንጨፊያ ማዕከል ልትገነባ ነው። ጂቡቲ ለሳተላይቶች እና ለሮኬቶ | TIKVAH-MAGAZINE

ጂቡቲ የሳተላይት እና የሮኬት ማስወንጨፊያ ማዕከል ልትገነባ ነው።

ጂቡቲ ለሳተላይቶች እና ለሮኬቶች ማስወንጨፊያ የሚሆን መሠረተ ልማት ግንባታ ለማከናወን ሆንግ ኮንግ ኤሮስፔስ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ከተባለ ተቋም ጋር የሀገሪቱ ባለሥልጣናት መፈራረማቸውን የሀገሪቱ ዜና ወኪል ዘግቧል።

በዚህ ስምምነት መሠረት ከሳተላይት እና ሮኬት ማስወንጨፊያ ማዕከሉ ጋር በተያያዘ የሚያስፈልጉ የግንባታ አቅርቦቶችን ለማቀላጠፍ በሰሜናዊ የአገሪቱ ኦቦክ ክፍል ውስጥ ወደብ እና አውራ ጎዳና የሚገነባ ይሆናል።

የመሠረተ ልማቱ አጠቃላይ የግንባታ ሥራውም 1 ቢሊዮን ዶላር ያህል የሚያስወጣ ሲሆን በአምስት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

የሳተላይት ማስወንጨፊያ ማዕከሉ ግንባታ ከተጠናቀቀ በኋላ ለ30 ዓመታት ያህል በሆንግ ኮንጉ ኩባንያ እና በጂቡቲ በጋራ የሚተዳደር ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ ጂቡቲ ማዕከሉን ሙሉ ለሙሉ ትረከበዋለች ተብሏል።

በአፍሪካ የሳተላይት ሮኬት ማስወንጨፊያ በሰባት አገራት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እነሱም በኬንያ፣ በግብፅ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በሊቢያ፣ በሞሪታኒያ፣ በዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ በአልጄሪያ ውስጥ ነው የሚገኙት።

ጂቡቲ ለመገንባት የተነሳችው የሳተላይት እና የሮኬት ማስወንጨፊያ ማዕከል ከአምስት ዓመታት በኋላ ሲጠናቀቅ በአህጉሪቱ ከሚገኙ ተመሳሳይ ማዕከላት አንዱ ይሆናል።

Credit : BBC, Ismail Omar Guelleh

@tikvahethmagazine