Get Mystery Box with random crypto!

#Update የኮሌራ ወረርሽኝ ከተከሰተባቸው የኦሮሚያ ክልል ሶስት ዞኖች ችግሩ  በከፋባቸው ባሌ | TIKVAH-MAGAZINE

#Update

የኮሌራ ወረርሽኝ ከተከሰተባቸው የኦሮሚያ ክልል ሶስት ዞኖች ችግሩ  በከፋባቸው ባሌ ዞን አካባቢዎች ሁለት ወረዳዎች ተለይተው ከፊታችን ሐሙስ ጀምሮ ክትባት እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡

ወረርሽኙ የመቀነስና የመጨመር ባህሪ በማሳየቱ የባሌ ዞን ወረዳዎች በሆኑት በርበሬና ጎሮ 79ሺህ ዶዝ የኮሌራ ክትባት በመዘጋጀቱ የንጽህና ችግር እና የውሀ አቅረቦት ችግር ባለባቸውና በጣም በተጎዱ በተመረጡ ቀበሌዎች ላይ እንደሚሰጥ ተነግሯል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡

እስካሁን ድረስ በሶስቱ ዞኖች 700 ሰዎች በኮሌራ መያዛቸው የተነገረ ሲሆን 12 ሰዎች በበሽታው ህይወታቸው ማለፉን ነው ዘገባው ያመላከተው፡፡

እንደሀገር የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ ስጋት ያለባቸው 80 ወረዳዎች የተለዩ ሲሆን 25 በክልሉ የሚገኙ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከዚህ ቀደም በክልሉ የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን እንዳሁም የመጀመሪያው የኮሌራ በሽታ በዚህ ዓመት በባሌ ዞን ነሃሴ 21 መገኘቱ እንደተጠቆመና የስደተኛ መጠለያ የሚገኝባቸውን ጨምሮ 114 ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 459 ሺ ሰዎችም አስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ መባሉን መዘገባችን ይታወሳል።

@tikvahethmagazine