Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Update
Silver
Platinum
Golden
Choleraupdate
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.37K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 143

2023-01-09 17:40:15
ስለ ከፍተኛ የደም ግፊት ከዶ/ር የወንድወሰን ጋር

ከምንወያይባቸው አርዕስቶች መካከል፦

   - የደም ግፊት ደረጃዎችና ዓይነቶች (የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ)

   - እንደ ስርጭት፣ ወዘተ ያሉ እውነታዎች

   - ምልክቶች፣ አጋላጭ ምክንያቶች እና ውስብስብ ችግሮች።

በዚህ ሳምንት ረቡዕ ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ይጠብቁን!

@tikvahethmagazine
11.4K viewsedited  14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 16:40:58
አፋልጉኝ!

ዛሬ በአዳማ ከተማ ተርጋ ቁጥሩ ኮድ 3 አአ A14970 የሆነ መኪና ከቆመበት እንደጠፋቸው ለቲክቫህ በላኩት መልዕክት ገልጸዋል። መኪናውን የተመለከታችሁ በቀጣዩ ስልክ አሳውቁን ሲሉ ጠይቀዋል።

0912295727
0911252572

@tikvahethmagazine
15.5K viewsedited  13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 16:24:27
#ኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል ከታህሳስ 23 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ12ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፤ በ21 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ14 ሰዎች  ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በንብረት ላይ የደረሰዉ ዉድመት በገንዘብ ሲተመን  ከ1ሚሊየን 4መቶ ሺ ብር በላይ እንደሚገመት ተነግሯል።

የአደጋዎቹ ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የጨመረ ሲሆን ፤ መንስኤዎቹ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ፣የተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር፣ርቀትን ጠብቆ አለማሽርከር መሆኑን ተገልጿል።

Credit: Bisrat FM 101.1

@tikvahethmagazine
16.4K viewsedited  13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 16:17:10
የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ባለፉት አምስት ወራት 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

ባለፉት አምስት ወራት ብቻ ከ500 ሺህ ቶን በላይ ጭነት በማጓጓዝ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱ የተገለፀ ሲሆን ይህም ከ2014 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ወደ 600 ሚሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ተነግሯል።

ማኅበሩ ካጓጓዘው ጭነት አንጻር በ2015 በጀት ዓመት ባለፉት አምስት ወራት በወጪና ገቢ ንግድ ያደረገው አስተዋጽኦ 15 በመቶ የደረሰ ሲሆን ይህም ቀደም ሲል ከነበረው 11 ነጥብ 2 በመቶ ጋር ሲነጻጸር እድገት እያሳየ መሆኑ ተብራርቷል።

ማህበሩ የአፈር ማዳበሪያ፣ ዘይት፣ ስንዴ፣ ተሽከርካሪና ሌሎች ጭነቶችን ጨምሮ ባለፉት አምስት ወራት ከ500 ሺህ ቶን በላይ ጭነት አጓጉዟል ተብሏል።

በተጨማሪም ስኳርና ጋዝን ጨምሮ በማዕድን ዘርፍ ሲሚንቶን በስፋት ለማጓጓዝ ዝግጅት ማጠናቀቁን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethmagazine
14.6K viewsedited  13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 16:15:14
The class will start on Jan 14,2023

የኦንላይን  ኮዲንግ  ስልጠና ለልጆች

ከ9 እስከ 18 ለሆኑ ህጻናት የ6 ሳምንታት የኮዲንግ ስልጠና( ጌም እና አኒሜሽን እየሰሩ ነው ሚማሩት)።

ስልጠናው የ6 ሳምንታት ፕሮግራም ሲሆን በኦንላይን  ነው የሚማሩት።

የምስክር ወረቀት ያገኛሉ

ክፍያ ለ6 ሳምንት ፕሮግራም 2000 ብር ነው።

በቴሌግራም መረጃ ለማግኘት ያግኙን።
@BeleyeA

ይህንን ሊንክ በመጠቀም ሬጅስተር ያርጉ።

https://forms.gle/AAZT7BXJs8Rss9hG8
14.2K views13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 11:38:14
በጉራጌ ዞን በደረሰ የእሳት አደጋ 12 ቤቶች ከነሙሉ የቤት ዕቃቸው በእሳት ቃጠሎ ወደሙ፡፡

በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ በእስኩት ቀበሌ በትላንትናው ዕለት 12 ቤቶች ከነሙሉ የቤት ዕቃቸው በእሳት ቃጠሎ መውደማቸው ተገልጿል፡፡ በተመሳሳይ በወረዳው ከቀናት በፊት በፉቻሬ ቀበሌ ወንቃነ መንደር ሶስት ቤቶችን ላይ ተመሳሳይ አደጋ ደርሶ ነበር።

በሁለቱም ቀበሌያት የተከሰቱትን ቃጠሎዎች መንስኤና የወደሙ ንብረቶች ግምት በሚመለከታቸው አካላት ተጠንቶ መረጃው ሲደርሰን የምናሳውቅ ይሆናል ሲል የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።

@tikvahethmagazine
20.9K viewsedited  08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 11:28:01
በታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም በደረሰ የእሳት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ።

በደብረሊባኖስ ገዳም በጠበልተኞች ማረፊያ ክፍል ውስጥ በተነሳ ድንገተኛ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉም ታውቋል።

በትላንትናው ዕለት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ በገዳሙ የጠበልተኞች ማረፊያ ክፍል በተነሳው የእሳት አደጋ ከ20 በላይ ክፍሎች ወድመዋል ተብሏል።

እሳቱ ሌሎች አደጋዎችን እንዳያደርስ በገዳሙ መነኮሳት፣ በአካባቢው ምእመናን እና በጸጥታ ኃይል አባላት ከፍተኛ ርብርብ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

Credit : Mahibere Kidusan FB page

@tikvahethmagazine
19.1K viewsedited  08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 11:27:26
በመዲናዋ ከገና ዋዜማ አመሻሽ ጀምሮ እስከ እሁድ ምሽት ድረስ 8 አደጋወች ማጋጠማቸው ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከገና ዋዜማ አመሻሽ ጀምሮ እስከ እሁድ ምሽት ድረስ 2 ድንገተኛ አደጋወችን ጨምሮ 6 የእሳት አደጋዎች በድምሩ 8 አደጋዎች ማጋጠማቸው እና በአንደኛው አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

አደጋወቹ የተከሰቱት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዲስ ትምህርት ቤት ጀርባ ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ሰፈራ አካባቢ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ቡልቡላ አካባቢ እንዲሁም በሌሎች ክፍለ ከተሞች አደጋዎቹ ተከስተዋል።

የሞት አደጋው የተከሰተው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሲሆን እድሜው 23 አመት የሆነው ወጣት የአደጋው ሰለባ መሆኑን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሜሽን የህዝብ ግንኙት ባለሙያው አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በኦሮሚያልዩ ዞን አለም ገና ኬንተሪ አካባቢ የተነሳው የእሳት አደጋ አንድ የጤና ጣቢያ ላቦራቶሪን ክፍልን  ጨምሮ 8 የንግድ ሱቆች ላይ ጉዳት ማድረሱን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል።

በዚህ አደጋ በአጠቃላይ 5 ሚሊየን 500 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ሲወድም  ከ100 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ለማትረፍ ተችላልም ተብሏል። (Balageru Tv)

@tikvahethmagazine
16.3K viewsedited  08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 11:27:08
በኤሌክትሪክ መኪና የቴክኖሎጂ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስራት ዝግጁ ኖት?

በቀን ከ 2,000 ብር በወር ከ 60,000 ብር በላይ ገቢ ያግኙ፤
ከ 10% ጀምሮ ቅድመ ክፍያን በመክፈል የኤሌክትሪክ መኪኖችን የማግኛ እድል፤
በ 60 ብር የኤሌክትሪክ ቻርጅ ከ 300 ኪሎ ሜትር በላይ ይጠቀሙ፤
አገልግሎቱን በግልዎ አሊያም ከሰለጠኑ ሹፌሮቻችን ጋር መስጠት ይችላሉ፤
ቀሪ ክፍያዎን ዋስትና በማቅረብ ከእኛ ጋር በመስራት የሚከፍሉት፤

ከስማርት ጋር ይስሩ ፤ ከጊዜ ጋር ይበልጽጉ!

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቤተሰብ ይሁኑ!
https://t.me/SmartHibret

በኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/smarthibret/

በፌስቡክ ገጻችን ይከታተሉን!
https://www.facebook.com/profile.php?id=100087358936762
#ስማርትህብረት
16.3K views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 11:26:57
REGISTRATION UNDERWAY!

REQUIREMENT
First degree in any field of study (Logistics related work experience is preferable)
Fluency in English language

REGISTRATION
https://www.effsaa.org/training-program-on-free-trade-zone-and-logistics-in-collaboration-with-pum-netherlands-senior-experts/

SHOULD YOU REQUIRE MORE INFORMATION?
Please call us at +251 115 589045 / +251 903 182525
OR
Visit our telegram channel
https://t.me/EFFSAAOfficial
18.8K views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ