Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Tikvahfamily
Cloudbridge
Traininginstitute
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.20K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 145

2022-12-30 09:46:24
#እናመሰግናለን

የሁለተኛው ዙር የመማሪያ መፅሀፍት እና ቁሳቁስ የማሰባሰብ ስራን ተከትሎ ፖሊኪዩር መድሃኒት ቤት 10 ሺህ ብር የወጣባቸውን መፅሀፍት ገዝቷል። በቀጣይ ቀናትም ያስረክባል።

ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል 5 ሺህ ብር የወጣበት መፅሀፍ ልብወለዶችን ጨምሮ አስረክቧል (ለህዝብ ቤተመፅሀፍ)።

ውድ ቤተሰቦቻችን በጦርነት የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን ለማገዝ ፦
- በቤታችሁ ውስጥ ያለ የማትጠቀሙበት / ያገለገለ ዴስክቶፕ / ላፕቶፕ ኮምፒዩተር፣
- ነጭ ወረቀት
- ፕሪነተር
- የፕሪንተር ቀለም
- ከ9 - 12 ማንኛውም መፅሀፍ
- ከ1-8 አጋዥ መፅሀፍ አበርክቱ።

አዲስ አበባ ያላችሁ #ቅዳሜ እና #እሁድ በየአካባቢያችሁ የምንመጣ ይሆናል ፦ 0919743630

በሀዋሳ ከቀናት በኃላ ይጀምራል።

@tikvahethiopia
12.6K views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 19:53:49
#Update

በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ላለፉት 6 ቀናት በስቴም ፖወርና በቲክቫህ ኢትዮጵያ ትብብር ሲሰጥ የነበረው የወጣቶች የመጀመሪያ ደረጃ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በነገው ዕለት ይጠናቀቃል።

በሥልጠናው በርካታ ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን ቅዳሜ ዕለት በሚካሄድው የምርቃትና የሰርተፊኬት አሰጣት ሥነ-ስርዓት የመጀመሪያ ዙር ስልጠናው ማብቂያውን ያገኛል።

ቅዳሜ ዕለት በሚኖረን መርሐግብር ወደ 200 የሚጠጉ ከተሰጡት ስልጠናዎች ከ90 % በላይ የወሰዱ ወጣቶች በአካል ተገኝተው ሰርተፊኬታቸውን የሚቀበሉ ይሆናል። ሌሎች ተሳታፊዎች በሰለጠኑበት ርዕስ ሰርተፊኬታቸውን በዲጂታል መልኩ ይቀበላሉ።

የሚሳተፉት ሰልጣኞች ከዚህ ቀደም በወጣው ማስታወቂያ ቅድሚያ ተመዝግበው ማረጋገጫ የተሰጣቸው ሲሆኑ በቀሩት ቀናት አዲስም ሆነ ማረጋገጫ ከተሰጣቸው ተሳታፊዎች ውጭ የማናስተናግድ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

#STEMPower #TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
16.1K viewsedited  16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 19:35:51
በሲዳማ ክልል ባለፉት አምስት ወራት 82 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው አልፏል

በዘንድሮዉ በጀት ዓመት አስከ ታህሳስ አጋማሽ ባለዉ ጊዜ በሲዳማ ክልል በተለያዩ ቦታዎች 132 የትራፊክ አደጋዎች ተከስተዋል። በአደጋውም 82 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፤ ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረትም ሲወድም 91 ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

አደጋዉ ካለፈዉ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ብልጫ እንዳለዉ ተገልጿል፤ አብዛኛዉ አደጋ የተከሰተዉ ከሀዋሳ ወደ ዲላ በሚወስደዉ አስፋልት መንገድ ላይ ሲሆን በተለይ በአለታ ጩኮ ከተማና አካባቢዉ ላይ በርካታ ጉዳት መድረሱና ንብረት መውደሙ እንዲሁም በአንድ ቀን ብቻ በአከባቢው 12 ሰዎች በአደጋዉ መሞታቸው ተገልጿል፡፡

በርካታ የትራፊክ አደጋዎች እየተከሰቱ ያሉት ባለሁለት ጎማ ሞተር ሲሆን፣ እስከ አምስት የሚደረርስ ትርፍ ሰዉ በመጫንና ከተፈቀደዉ ፍጥነት በላይ በማሽከርከር መሆኑ የተነገረ ሲሆን የአሽከርካሪዎች ብቃት ማነስ፣ ሀሰተኛ መንጃ ፈቃድ፣ ጠጥቶና ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር፣ አልፎ አልፎ የመንገድ መበላሸትና ሌሎችም ለአደጋዉ መንስኤ ምክንያት ናቸው ተብሏል፡፡

የገጠሩ ማህበረሰብ በአብዛኛዉ ለትራንስፖርት የሚጠቀመዉ ባለ ሁለት ጎማ ሞተር እንደመሆኑ መጠን አደጋዉን ለመቆጣጠር አመቺ አለመሆኑንና መፍትሄ ካልተበጀለት አደጋዉ እየጨመረ እንደሚሄድ ተጠቁሟል።

Credit: - EPA

@tikvahethmagazine
15.9K viewsedited  16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 13:23:16
#አማራባንክ

አማራ ባንክ ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 8.8 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ማግኘቱን እና ከግብር በፊት 237 ሚሊዮን ብር ማትረፉ ተነግሯል።

የባንኩ የሃብት መጠን 7.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል።በተጨማሪም የተከፈለ የካፒታል መጠን 4.8 ቢሊዮን መሆኑ ተመላክቷል።

አማራ ባንክ አንድ መቶ አርባ አንድ ሺህ የሚሆኑ ባለአክስዮኖች እንዳሉት እና የባንኩ የደንበኞች ቁጥር በአሁን ሰዓት ከአምስት መቶ አምስት ሺህ በላይ ደንበኞች መድረሱ ተገልጿል።

ባንኩ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ከ201 በላይ ያሳደገ መሆኑ የተለጸ ሲሆን በተጨማሪም ባንኩ አዳዲስ ቅርንጫፎችን ለመክፈት ማቀዱንና ያሉትን 8 የኤቲኤም ማሽኖች ቁጥር ወደ 125 ለማሳደግ የማሽን ግዢ መፈጸሙ ተነግሯል።

አማራ ባንክ ከ6.5 ቢሊየን ብር በላይ የተፈረመ ፣ 4.8 ቢሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል እንዲሁም ከ170ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች ይዞ በሰኔ 2014 ወደ ስራ የገባ ባንክ ነዉ፡፡

ይህ የተነገረው የባንኩ ባለ አክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ እና አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ነው

@tikvahethmagazine
14.5K viewsedited  10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 12:32:18
"እስራኤል ዳንሣ ነኝ" በማለት በሀይማኖት ሽፋን የማታለል ወንጀል የፈፀመዉን ግለሰብ . . .

በቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ በሚዛን አማን ከተማ አዲስ ከተማ ቀበሌ ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ግለሰቡ የግል ተበዳይ ማንነት በማጥናትና ስልክ በመደወል "እኔ እስራኤል ዳንሣ ነኝ" በማለት ራሱን የፀሎት ሰው በማስመሰል ልጅህ በቅርብ ቀን ወደ ካናዳ ሀገር እንድትሄድ ፀሎት አድርጊያለው የሚልና የመሳሰሉ ሃሣቦችን ይሰጣል።

ከዚያም የተጀመረውን ህንፃ ግንባታ ለማጠናቀቅ የገንዘብ ድጋፍ አደርጉልኝ በማለት ከግል ተበዳይ በመጀመሪያ ዙር 30 ሺህ ብር በባንክ አካውንት ቁጥሩ ይገባለታል፡፡

ከሌሎች አራት ሰዎችመ ማንነታቸውንና የስራ ቦታቸውን ጥናት በማድረግ መሰል ተግባር በማከናወን 109 ሺህ 500 ብር የማታለል ወንጀል ሲፈጽም ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

@tikvahethmagazine
17.8K viewsedited  09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 12:23:45
በከባድ ዝናብ ምክንያት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

በጎፋ ዞን በቶ ከተማ አስተዳደር ትናንት አመሻሹን የጣለው ከባድ ዝናብ በ3ቱም ቀጠናዎች በመኖሪያ ቤት ፣ በንብረት እና በሰብል ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱ ተገልጿል።

ጉዳቱ በባላ ቀጠና እና መሀል ከተማ አጠቃላይ በ 95 ቤቶች እና ቤተሰብ ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 19ኙ ሙሉ በሙሉ መኖሪያ ቤታቸው ላይ በደረሰው ጉዳት ተፈናቅለዋል ሲል የዞኑ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ገልጿል።

ጉዳት የደረሰባቸው አንድ ህፃን እና አንድ አዛውንት በህክምና ማዕከል እየተረዱ መሆኑንና ዝናቡ በእንስሳትም ላይ ጉዳት ማስከተሉንና የአካባቢው ህብረተሰብ እና የከተማዋ አመራሮች በቅንጅት የደረሰውን ጉዳት ማጣራት ላይ መሆናቸውን ከዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@tikvahethmagazine
16.9K views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 12:20:33
ባለፉት 3 ዓመታት ከአንድ ሺህ በላይ አርሶ አደሮች የቡና ላኪነት ፈቃድ ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የቡና ላኪነት ፈቃድ ከወሰዱት አርሶ አደሮች መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑ ቡናቸውን በቀጥታ ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል፡፡

ባለፈው በጀት ዓመት 302 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ በመላክ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር የተገኘ ሲሆን በዘንድሮ በጀት ዓመት 360 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ዕቅድ መያዙ ተበግሯል።

ባለስልጣኑ የዓለም የቡና ገበያ ተለዋዋጭነትን መሰረት በማድረግ ተጨማሪ የገበያ መዳረሻዎችን የማፈላለጉን ስራ በትኩረት እያከናወነ መሆኑን እንደ ኤዥያ ባሉ አካባቢዎች አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎችን ለማስፋት እንቅስቃሴ መጀመሩን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

@tikvahethmagazine
14.2K viewsedited  09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 12:19:55
ነፃ የሽያጭ ስልጠና ላይ ይሳተፉ!

በሪልስቴት ሽያጭ ሙያ ላይ ተሰማርተው ገቢዎን ዕጥፍ ማድረግ ይፈልጋሉ? የሽያጭ ክፍል ኃላፊስ ሆነው የተሻለ ደመወዝ ማግኘት እና የስራ ደረጃዎትን ከፍ ማድረግ ይፈልጋሉ? ቢዝነስዎትንስ በዲጂታል ማርኬቲንግ አስተዋውቀው የሽያጭ መጠንዎን ማብዛት ይሻሉ?

ለጥያቄዎቹ መልስዎት አዎ ከሆነ፣ እኛ መልኅቅ ማርኬቲንግ እና ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት ለእርስዎ የሚሆን ነፃ የሽያጭ ስልጣን አዘጋጅተንልዎታል። 0967280828 ወይም 0115572357 በመደወል ይመዝገቡ!

ታህሳስ 20፣ 2015 ከ11:30 ጀምሮ

ጊዮን ሆቴል
13.1K views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 12:19:33
https://t.me/Amirshifon1
availabe now
ከ ነፃ ዴሊቨሪ አዲስአበባ ዉስጥ ለሆናቹ
ይደዉሉልን 0933471055
                0979224310
በብዛት ለምትወስዱ ሽፎን ቤቶች ቅናሽ አለን
አድራሻችን
መርካቶ ሚሊተሪ ተራ አዲሱ ህንፃ F1-128C
telegram channal
https://t.me/Amirshifon1
13.0K views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 10:00:16
ሁለተኛው ዙር የትምህርት መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ ዛሬ ይጀመራል።

በዚህ ዙር በጦርነት የተጎዱ ትምህርት ቤቶች ከሚያስፈልጋቸው ቁሳቁስ አንፃር መማሪያ መፅሀፍ ብቻ ሳይሆን ፦

+ ነጭ ወረቀት
+ ያገለገለ ፕሪንተር
+ የፕሪንተር ቀለም
+ ማንኛውም አይነት ያገለገለ ኮምፒዩተር መስጠት ይቻላል።

ውድ ቤተሰቦቻችን በመጀመሪያው ዙር በጥቂት ቀናት ዘመቻ 8 ሺህ ገደማ መፅሀፍ መሰባሰቡ አይዘነጋም አሁን በትንሹ 30 ሺህ መፅሀፍ ለማግኘት ታቅዷል።

መስጠት የሚቻለው መፅሀፍ ፦

- ከ1-8 #አጋዥ_መፅሀፍ_ብቻ
- ከ9-12 ማኛውም መደበኛ (ቴክስት) እና አጋዥ መፅሀፍ

በተጨማሪ ፦ ከከተማ ወጣ ብሎ ለሚገኝ የህዝብ ቤተመፅሀፍ ማንኛውም አይነት አሉታዊ መልዕክት የማያስተላልፍ ልብወለድ መፅሀፍ መለግስ ይቻላል።

#አዲስ_አበባ ስልክ ፦ 0919743630

በቅርብ ቀናት በሀዋሳ ተመሳሳይ ዘመቻ ይኖራል።

ማሳሰቢያ ፦ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰበሰብ ባለመሆኑ ከላይ የተዘረዘሩትን ቁሳቁሶች #የመግዛት_አቅም ያላችሁ ቁሳቁሶቹን ገዝታችሁ ማበርከት ትችላላችሁ።

የማሰባሰብ ስራው የሚያበቃበት ቀን ከየካቲት 30 በፊት።

@tikvahethiopia
18.1K views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ