Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Update
Silver
Platinum
Golden
Choleraupdate
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.37K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 142

2023-01-10 16:30:19
Design + Build ለሚያሰሩ ደንበኞቻችን ነፃ የዲዛይን አገልግሎት እንሰጣለን።

የምንሰጣቸው አገልግሎት
የኢንቴርየር ዲዛይን እና የፊኒሺንግ ስራ
የህንፃ ዲዛይንና ማማከር አገልገሎት
አጠቃላይ የእንጨት ስራ
የኢፓክሲ ስራ ( Epoxy Work )

Contact us  @etheldesign1
0939902740
0919361804

ኢትኤል ዲዛይን ጥራትና ውበት አንድ ላይ Ethel Design

Join Telegram: t.me/etheldesign
14.0K views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 13:42:17
የደራሲና ጋዜጠኛ አቤ ጉበኛ ሀውልት እንደ አዲስ ለማሰራት እንቅስቃሴ ተጀመረ።

ደራሲና ጋዜጠኛ አቤ ጉበኛ በምዕራብ ጎጃም ዞን በ አቸፈር ወረዳ ልዩ ስሙ ኮረንች አቦ በተባለ ቀበሌ ከአባቱ ከአቶ ጉበኛ አምባየና ከእናቱ ከወ/ሮ ይጋርዱ በላይ ሰኔ25 ቀን 1925 ዓ.ም ነው የተወለደው።

በዘመኑ በሚጽፋቸው መጽሐፍት፣ የግጥም መድብሎችና ተውኔቶች ፖለቲካዊ፣ ማበራዊና ሀይማኖታዊ ትችቶችን ይሰነዝር የነበረ ደፋር ደራሲ እንደነበር ሥራዎቹና የህይወት ታሪኩ ያስረዳል።

በዚህም በተለያዩ ጊዜያት እስር ድብደባና የግዞት ህይወት ለመምራት ተገዷል። በ1957 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ በተካሄው የህዝብ እንደራሲነት ምርጫ ለመወዳደር የሚያስችለውን የህዝብ ድጋፍ ቢያገኝም በፀጥታ ሀይሎች ተያዞ ብዙ ስቃይና እንግልት አሳልፏል።

አቤ በህይወት ዘመኑ ከ27 በላይ መፅሀፍቶችን እንደጻፈ ይነገርለታል። ከእነዚህም ውስጥ አልወለድም፣ የሮም አወዳደቅ፣ ሰይፈ ነበልባል፣ የሀሜት ሱሰኞች፣ አንድ ለእናቱና ሌሎችም የጥበብ ሥራዎቹ ተጠቃሽ ናቸው።

የብዕር ታጋዩ ጋዜጠኛውና ደራሲው ታላቁ የጥበብ ሰው አቤ ጉበኛ ብዙ ስቃዮችንና እስሮችን አሳልፎ የካቲት 1/ 1972 ተደብድቦ ተገደለ። የካቲት 4 /1972 በይስማላ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ስርአተ ቀብሩ ተፈጽሟል።

መታሰቢያ ሀውልቱ በዚህ ቤተ ክርስቲያን በር ላይ ተሰርቶ አሁንም ድረስ ያለ ቢሆንም ደራሲውን አይመጥንም በሚል በተለያዩ ጊዜያቶች ሲነሳ ይስተዋላል።

ይህን ተከትሎም የይስማላ ከተማና አካባቢዋ ወጣቶች የአቤን ሀውልት ጀግንነቱንና መልካም ስራውን በሚመጥን መልኩ ለማቆም ስራ መጀመራቸው ተገልጿል። እስካሁን በተሰራው ኮሚቴ የተዋቀረ ሲሆን ሥራም ሀውልቱ በነሀስ እንደሚሰራ ተወስኗል። ዲዛይኑም በመሰራት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethmagazine
11.6K viewsedited  10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 12:59:51
#PressRelease

- ባለፉት 5 ወራት በተለያየ የአለም ክፍል ያሉ ኢትዮጵያዊያን ከ1.36 ቢሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ ወደ አገር ቤት መላኩን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት አስታውቋል።

- በአምስት ወራቱ ከ27 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ የዲያስፖራ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች  ተመዝግበዋል።

- ባለፉት 3 ዓመታት በሬሚታንስ የተላከው ገንዘብም ከ14 ቢሊየን ዶላር በላይ መሆኑን ተነግሯል።

- የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አይ ኤስ ፕሮሞሽንና ከሌሎችም ተቋማት በመተባበር ጥር 18 ቀን በዲፕሎማሲ፣ በህዳሴው ግድብ ተሳትፎ እና በሌሎችም ዘርፎች የላቀ ስራ ሰርተዋል ለተባሉ 45 የዲያስፖራ ማህበራት እውቅና ሰጣለው ብሏል።

Credit : Sheger FM 102.1 , EDS

@tikvahethmagazine
13.3K viewsedited  09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 12:34:21
#Gambella

- በጋምቤላ ክልል በዓመት 12 ሺህ ቶን ዓሳ ማምረት የሚያስችል ስነ ምህዳር ቢገኝም እስካሁን በመመረት ላይ ያለው 41 ነጥብ 7 በመቶ ወይም ከአምስት ሺህ ቶን የማይበልጥ ምርት ብቻ ነው፡፡

- በክልሉ በሚገኝ የውሃ ሀብት ከ113 በላይ የሚደርሱ የዓሳ ዝርያዎች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 15ቱ በገበያ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው ናቸው።

- በክልሉ መንግስትና በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በተደረገ ጥናት ጎግ፣ አቦቦ፣ጋምቤላ፣ ኢትንግ፣ካንካንና ቡርቤ የተሰኙት ስድስት ወረዳዎች የዓሳ ሀብት ያለባቸው ናቸው።

- በትላንትናው ዕለት በጋምቤላ ከተማ፣ በአቦቦ ወረዳ እና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ሦስት የዓሳ ማቀነባበሪያና ግብይት ማዕከል ተመርቆ ተከፍቷል።

- ለምረቃ በበቃው ፕሮጀክት ከአምስት ሺህ የሚበልጡ ወጣቶችና ሴቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጠርላቸውም ተመልክቷል፡፡

@tikvahethmagazine
13.5K viewsedited  09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 12:24:05
በሀገር ውስጥ የሚበለጽጉ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ፖሊሲ እተዘጋጀ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

በሀገር ውስጥ የሚበለጽጉ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ፈቃድ አሰጣጥ እና ቁጥጥር ፖሊሲ እተዘጋጀ እንደሚገኝ የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ አቶ ሃብታሙ ተሾመ መግለጻቸውን አሐዱ ሬዲዮ ዘግቧል።

እንደ ዘገባው ከሆነ ተቋሙ ከፍትህ ሚንስቴር እንዲሁም ሌሎች ከሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ጋር በመሆን መሰል የማህበራዊ ትስስር ገጾች ፈቃድ አሰጣጥ እና ቁጥጥር ዙሪያ የተለያዩ ፖሊሲዎችን እና ህጎች እየተዘጋጁ እንደሚገኙ ነው የጠቆመው፡፡

Credit : አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን

@tikvahethmagazine
13.0K viewsedited  09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 11:42:23
"IP Market" የተሰኘ የአዕምሯዊ ንብረት የገበያ ስርዓት ፕላትፎርም ይፋ ሆነ

የአዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን መ/ቤት የፈጠራ ባለመብቶችንና ባለሀብቶችን የሚያገናኝ የአዕምሯዊ ንብረት የገበያ ስርዓት ፕላትፎርም በማበልጸግ ተግባራዊ ማድረጉን አሳውቋል፡፡

ፕላትፎርሙ የአዕምሯዊ ፈጠራ ባለመብቶች የፈጠራ ስራዎቻቸውን ወደተግባር በማሸጋገር እና ለገበያ በማዋል ረገድ የሚገጥማቸውን የፋይናንስ ተግዳሮት ለመቅረፍ የሚረዳ ነው ተብሏል፡፡

የአለም አዕምሯዊ ድርጅትን ተሞክሮ በመውሰድ የተዘጋጀው ፕላትፎርሙ ከባለቤትነት ጋር ተያይዞ የሚመጡ ቅሬታዎችን ከግንዛቤ በማስገባት የበለጸገ መሆኑና ባመልጸጊያው ላይ እና መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች ብቻ እንጂ ዝርዝር ነገሮች እንደማይካተቱ ተብራርቷል፡፡

ፕላትፎርሙ ላይ የቀረቡ የፈጠራ ስራዎች መረጃን በመመልከት ስራዎቹን ለማልማትና ወደገበያ ለማቅረብ የሚፈልጉ ባለሀብቶች የሚፈልጉትን የፈጠራ ሰዎች በተዘጋጀ የፍላጎት መጠየቂያ ቅጽ ላይ በመሙላት ለተቋሙ ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

Credit፦ EBC

@tikvahethmagazine
13.6K viewsedited  08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 11:41:55
#ጥቆማ

ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከዳውሮ ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና በታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ከጥር 02_05/2015 ድረስ መሰጠት እንደተጀመረ የታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ለንጫ አሳውቀዋል።

በመርሃ ግብሩ ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና የህክምና አገለግሎት ከመስጠትም ባለፈ በህክምና ሂደት መነፅር ከታዘዘ ነፃ የመነፅር አገለግሎት እንደሚሰጥም ስራ አስኪያጁ አብራርተዋል።

የህክምና አገለግሎቱ እስከ ጥር 05/2015 ብቻ ስለሚቆይ አገለግሎት ፈላጊ የማህበረሰብ ክፍል ወደ ታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል በመምጣት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆንም ጥሪ ቀርቧል።

[ የዳውሮ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ]

@tikvahethmagazine
12.2K viewsedited  08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 11:41:42
በኤሌክትሪክ መኪና የቴክኖሎጂ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስራት ዝግጁ ኖት?

በቀን ከ 2,000 ብር በወር ከ 60,000 ብር በላይ ገቢ ያግኙ፤
ከ 10% ጀምሮ ቅድመ ክፍያን በመክፈል የኤሌክትሪክ መኪኖችን የማግኛ እድል፤
በ 60 ብር የኤሌክትሪክ ቻርጅ ከ 300 ኪሎ ሜትር በላይ ይጠቀሙ፤
አገልግሎቱን በግልዎ አሊያም ከሰለጠኑ ሹፌሮቻችን ጋር መስጠት ይችላሉ፤
ቀሪ ክፍያዎን ዋስትና በማቅረብ ከእኛ ጋር በመስራት የሚከፍሉት፤

ከስማርት ጋር ይስሩ ፤ ከጊዜ ጋር ይበልጽጉ!

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቤተሰብ ይሁኑ!
https://t.me/SmartHibret

በኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/smarthibret/

በፌስቡክ ገጻችን ይከታተሉን!
https://www.facebook.com/profile.php?id=100087358936762
#ስማርትህብረት
12.0K views08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 11:41:42
REGISTRATION UNDERWAY!

REQUIREMENT
First degree in any field of study (Logistics related work experience is preferable)
Fluency in English language

REGISTRATION
https://www.effsaa.org/training-program-on-free-trade-zone-and-logistics-in-collaboration-with-pum-netherlands-senior-experts/

SHOULD YOU REQUIRE MORE INFORMATION?
Please call us at +251 115 589045 / +251 903 182525
OR
Visit our telegram channel
https://t.me/EFFSAAOfficial
13.5K views08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 17:40:38
በሀረር ከተማ የሚገኙ ተቋማት ታፔላቸው ላይ በክልሉ ስራ ቋንቋ መሠረት እንዲጽፉ ቀነ ገደብ ተቀመጠ።

በሀረር ከተማ ታፔላቸውንና የተለያዩ ሕትመቶችን  በክልሉ ስራ ቋንቋ መሠረት በማይጽፉ ተቋማት ላይ ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን የሀረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል። ተቋማቱ እስከ የ2015 አመት 3ተኛው ሩብ አመት ድረስ ታፔላቸውን እንዲያስተካክሉም ነው ጥሪ የቀረበው፡፡

"የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ የግል ድርጅቶች የሚለጥፉቸው ማስታወቂያዎች የክልሉን የስራ ቋንቋ ያላከበሩ እና የቋንቋ ሥርአትን የሚያፋልስ የሕዝቡን ማሕራዊና ኢኮኖሚያዊ ብሎም ታሪክ ላይ ጫና የሚያሳድር ነው" ሲሉ የቢሮው ም/ሀላፊ አቶ አብዱጀባር ኡስማኢል ገልጸዋል።

በቀጣይ የቋንቋ ባለሙያዎች በማሰማራት ማስታወቂያዎችና ታፔላዎች የክልሉን የስራ ቋንቋ ባከበረ ሁኔታ እንዲሰሩ የሚሰራበት መሆኑን ያነሱት  ም/ሀላፊው በተለይ ተሸከርካሪዎች ላይ የሚፃፍ ማስታወቂያዎች የቋንቋ ስርአቱን እንዲያሟሉ የማድረግ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።

@tikvahethmagazine
11.9K viewsedited  14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ