Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.56K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 138

2023-02-01 18:36:28
ቦናፋይድ ትምህርት ቤት በሀዋሳ ከተማ በ26 ሚሊዮን ብር ያስገነባውን ተጨማሪ ህንጻ አስመረቀ

ሀዋሳ የሚገኘው ቦናፋይድ ትምህርት ቤት 26 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበትን ባለአራት ፎቅ ህንጻ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ እና የትምህርት መምሪያ ሀላፊው አቶ ደስታ ዳንኤል በተገኙበት ዛሬ አስመርቋል፡፡

ትምህርት ቤቱ በትምህርት ጥራት ረገድ፣ ደረጃ አራት ከተሰጣቸው በጣም ጥቂት የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች አንዱ ሲሆን፣ ከቅድመ አንደኛ እስከ ዘጠነኛ ክፍል ድረስ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል ተብሏል፡፡

በ2010ዓ.ም. የተመሰረተው ትምህርት ቤቱ 1054 ተማሪዎችን እያስተማረ የሚገኝ መሆኑን ከትምህርት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@tikvahethmagazine
29.9K views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 15:22:51
#ንግድባንክ

ባለፉት ስድስት ወራት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ አማራጮች በመጠቀም 1.3 ትሪሊዮን ብር ዝውውር መደረጉ ተገለፀ፡፡

በዲጂታል ባንክ አገልግሎቱ በርካታ ደንበኞች ገንዘባቸውን ለማስተላለፍ የዲጂታል ባንኪንግ አማራጮችን ተመራጭ አድርገዋል መባሉን ባንኩ አሳውቋል፡፡

@tikvahethmagazine
30.6K viewsedited  12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 15:22:00
በ6 ወራት ከ2.3 ቢሊየን ዶላር በላይ ወደ ሀገር ቤት መላኩ ተገለጸ

በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለውጭ ግንኙነትና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርቧል፡፡

በግማሽ በጀት ዓመቱ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን 2 ነጥብ 34 ቢሊዮን ዶላር ወደ ሀገር ቤት መላካቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡

በዓመቱ ከ102 ሺሕ በላይ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ታቅዶ እስካሁን ከ51 ሺሕ በላይ የሚሆኑትን መመለስ መቻሉንም ተገልጿል።

ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራዎች መተግበራቸው፣ ከህወሓት ጋር የተደረሰው የሠላም ስምምነት እና የተቋሙን በሰው ኃይል ማደራጀት በጠንካራ ጎን የተነሳ ሲሆን የጸጥታ ችግር እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት በተግዳሮትነት ተነስቷል።(WMCC)

@tikvahethmagazine
28.4K viewsedited  12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 14:00:49
STEMpower እና Visa ከTikvah-Ethiopia ጋር በመሆን የሚያዘጋጁት የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የፋይናንስ ክህሎት ስልጠና በሰባተኛ ዙር ተመልሶ መቷል።

ባለፉት ዙሮች ወደ 1500 የሚጠጉ ሰልጣኞች መሳተፍ ችለዋል። በዚህ 7ተኛ ዙር ደግሞ ተጨማሪ 300 ሰልጣኞችን ለማሳተፍ ዝግጅት ተደርጓል። እርስዎም ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ተመዝግበው የስልጠና እድሉን መጠቀም ይችላሉ።

ስልጠናው የሚያካትተው፦

* የ6 ቀን መሰረታዊ የገንዘብ አያያዝ ትምህርት እና የስራ ፈጠራ ክህሎት ስልጠና

* በተጨማሪ የ3 ወር የንግድ ማማከር እና ድጋፍ

* 9 ወር የማማከር ድጋፎች፣ የኔትዎርኪንግ እና የተለያዩ ክትትሎች በተጨማሪም ቢዝነ ፕሮቶታይፕ (prototype) የሚያስፈልገው ከሆነ ፕሮቶታይፕ መስሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ጨምሮ ነጻ የማምረቻ ላብራቶሪ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅታችንን በመጨረስ ላይ እንገኛለን።

በስልጠናው የሚሳተፉ፦

- የሥራ ፈጠራ ክህሎቱን ማዳበር እና ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች መጠቀም የሚፈልግ፤

- በግብርና፣ ጤና፣ አገልግሎት፣ ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ እና ሌሎችም ዘርፎች የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ቅድሚያ እንሰጣለን፤

- ሴት የሥራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ እናበረታታለን።

በሥልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ እና የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ እስከ ሰኞ ጥር 29፣ 2015 ዓም ተመዝግባችሁ ስልጠናውን እና ሌሎች አገልግሎቶቹን በነጻ መውሰድ ትችላላችሁ።

መመዝገቢያ ሊንክ፡ https://forms.office.com/r/6jrgpFiwtt

@tikvahethmagazine
27.6K viewsedited  11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 14:00:32
ከአያት አፓርታማ ለመግዛት ትክክለኛ ጊዜ!

ከ 30 - 35% ቅናሽ በእያንዳንዱ አፓርታማዎች ላይ

በአጭሩ እስከ 3 ሚሊዮን ብር  የሚደርስ ቅናሽ አድርገናል

አፓርታማዎቹ የ 99 ዓመት የሊዝ ክፍያ ተከፍሎላቸዋል

በመኖሪያ መንደሩ የከርሰ ምድር ውሃ ወጥቶለታል

የሰው እና የዕቃ ማመላለሻ አሳንሰር (elevator) አብሮ እየተሰራለት ነው

መብራት ሲጠፋ በራሱ ጊዜ የሚነሳ ጀነሬተር ይገጠምለታል

ለበለጠ መረጃ (Whatsapp/direct)፦ በ 0949734782 ወይም 0986009482 ይደውሉ
25.8K viewsedited  11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 14:00:32
ሴኩሪቲ ካሜራ ሽያጭና ነፃ ገጠማ
0911582926
security camera CCTV (ባለ 4 አና ባ 8 ካሜራ)
ለቤትዎ፤ ለድርጅት፤ ለሱቅ፤ ለፋርማሲ፤ ለዳቦ ቤት፤ ለቡቲክ፤ ለህንጻዎ ፤ ለመጋዘንዎ አና ለንብረትዎ የአመታት ልምድ ባለው ድርጅታችን ሴኩሪቲ ካሜራ ያስገጠሙ
-4 ካሜራዎች
-4 ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች  35,000 ብር
-8 ካሜራዎች
-8 ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች 50,000 ብር
28.5K views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 21:20:49 ባለፈው ሳምንት ስለ ስኳር ህመም ከዶ/ር ጌታሁን ታረቀኝ ጋር የተደረገ ቆይታ ከተከታዩ የድምጽ ፋይል ማድመጥ ይችላሉ።

በዚህ ጉዳይ ለሚኖራችሁ ጥያቄ ነገ ምሽት 1:00 ላይ ዶ/ር እሴተ ጌታቸው ምላሾቹን ይዛ ትቀርባለች።

ከስኳር ህመም ጋር ተያይዞ ለሚኖራችሁ ጥያቄ በ @eseteg  ላይ መላክ ትችላላችሁ።

@tikvahethmagazine
33.9K viewsedited  18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 18:34:39
ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞችን ችግር የሚፈቱ ሶስት አዳዲስ አገልግሎቶችን አስተዋውቋል።

እነዚህም፦

#ቴሌ_ድራይቭ፦ ደንበኞች መረጃዎቻቸውን ለማስቀመጥ የሚያገለግል ልክ እንደ ‘ጎግል ድራይቭ’ አይነት መረጃ ማስቀመጫ ነው፡፡

በዚህ አገልግሎት ደንበኞች በሞባይል ስልኮቻቸው የሚገኙ እንደ ፎቶ፣ ቪዲዮና የመሳሰሉ ከፍ ያለ መጠን ያላቸውን ፋይሎች አስተማማኝ በሆነ የክላውድ መረጃ ቋት በማስቀመጥ በፈለጉ ጊዜ ሁሉ መጠቀም የሚችሉበት መፍትሄ ሲሆን ተጠቃሚዎቹ የሞባይል ስልካቸው ቢጠፋ ወይም ቢበላሽ ፋይሎቻቻውን ያለሃሳብ መልሰው ማግኘት ያስችላቸዋል፡፡

#እልፍ_ፕላስ፦ ሙዚቃ በቀጥታ መከታተል የሚያስችል አማራጭ ነው። ይኸው አገልግሎትም ሙዚቃዎችን በመተግበሪያው በመግዛት የሞባይል ዳታ ሳይጠቀሙ በፈለጉ ጊዜ ማዳመጥ እንዲችሉ እንዲሁም በአምስት ቋንቋዎች የሚተላለፍ የቀጥታ ስርጭት (online) ሬዲዮ ፕሮግራም ያለው ነው፡፡

#ክላውድ_ሶሊሽን፦ ሲስተሞችና ሶፍትዌሮችን ለማስቀመጥ የሚያስችል አገልግሎት ነው።

ይህም፦

- የ Infrastructure as a Service (IaaS) ተጠቃሚዎች እንደ አስፈላጊነቱ ካሉበት ሆነው የግል መረጃዎቻቸውን ማስቀመጥ፣ መቀመር፣ ለደንበኞቻቸው የተለያዩ አገልግሎችን መስጠት የሚያስችል የክላውድ አገልግሎት ነው፡፡

-እንዲሁም Software as a Service (SaaS)- ደንበኞች የተለያዩ በውጭ ምንዛሪ የፈቃድ ክፍያ በመክፈል ያገኟቸው የነበሩ ሶፍትዌሮችን በተመጣጣኝ ክፍያ በብር ማግኘት የሚችሉበትንና ሌሎችንም አገልግሎቶች ያካተተ ነው፡፡

@tikvahethmagazine
20.5K viewsedited  15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 17:51:42
#ኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል ከጥር 14 እስከ ጥር 21 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ13 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፤ በ9 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ10 ሰዎች  ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በንብረት ላይ የደረሰዉ ዉድመት በገንዘብ ሲተመን ከ960 ሺ ብር በላይ እንደሚገመት የተነገረ ሲሆን አደጋዎቹ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3፡30  ሰዓት የተመዘገቡ መሆናቸው ተገልጿል።

የአደጋዎቹ ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የቀነሰ ሲሆን ፤ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ፣ እና ሌሎችም ለአደጋዎቹ መንስኤ መሆናቸውን ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል፡፡

ፎቶ፦ ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን

@tikvahethmagazine
22.4K views14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 13:40:31
በክልሉ ለ4 ሺህ 401 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለ4 ሺህ 401 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ አስታወቀ።

የይቅርታው ተጠቃሚ ከሆኑት የሕግ ታራሚዎች መካከልም 93 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው ተነግሯል።

በይቅርታ ከተፈቱ በኋላ 3(ሶስት) ዓመት ሳይሞላቸው በሌላ ወንጀል ተግባር ገብተው የተገኙ 13(አስራ ሶስት) የሕግ ታራሚዎች ይቅርታቸው እንዲሰረዝ ተወስኗል ተብሏል፡፡

የይቅርታው ተጠቃሚ የሆኑት በይቅርታ አሰጣጥ መመሪያው ላይ የተገለፁ፣የእስራት የዕድሜና የጤና መስፈርቶችን ያሟሉ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ይቅርታ የተደረገላቸው የሕግ ታራሚዎችም ከጥር 20 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ ከያሉበት ማረሚያ ቤት እንዲፈቱ መደረጉን ከክልሉ ፍትህ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@tikvahethmagazine
26.4K viewsedited  10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ