Get Mystery Box with random crypto!

በክልሉ ለ4 ሺህ 401 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለ4 ሺህ | TIKVAH-MAGAZINE

በክልሉ ለ4 ሺህ 401 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለ4 ሺህ 401 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ አስታወቀ።

የይቅርታው ተጠቃሚ ከሆኑት የሕግ ታራሚዎች መካከልም 93 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው ተነግሯል።

በይቅርታ ከተፈቱ በኋላ 3(ሶስት) ዓመት ሳይሞላቸው በሌላ ወንጀል ተግባር ገብተው የተገኙ 13(አስራ ሶስት) የሕግ ታራሚዎች ይቅርታቸው እንዲሰረዝ ተወስኗል ተብሏል፡፡

የይቅርታው ተጠቃሚ የሆኑት በይቅርታ አሰጣጥ መመሪያው ላይ የተገለፁ፣የእስራት የዕድሜና የጤና መስፈርቶችን ያሟሉ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ይቅርታ የተደረገላቸው የሕግ ታራሚዎችም ከጥር 20 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ ከያሉበት ማረሚያ ቤት እንዲፈቱ መደረጉን ከክልሉ ፍትህ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@tikvahethmagazine