Get Mystery Box with random crypto!

STEMpower እና Visa ከTikvah-Ethiopia ጋር በመሆን የሚያዘጋጁት የሥራ ፈጠራ እና | TIKVAH-MAGAZINE

STEMpower እና Visa ከTikvah-Ethiopia ጋር በመሆን የሚያዘጋጁት የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የፋይናንስ ክህሎት ስልጠና በሰባተኛ ዙር ተመልሶ መቷል።

ባለፉት ዙሮች ወደ 1500 የሚጠጉ ሰልጣኞች መሳተፍ ችለዋል። በዚህ 7ተኛ ዙር ደግሞ ተጨማሪ 300 ሰልጣኞችን ለማሳተፍ ዝግጅት ተደርጓል። እርስዎም ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ተመዝግበው የስልጠና እድሉን መጠቀም ይችላሉ።

ስልጠናው የሚያካትተው፦

* የ6 ቀን መሰረታዊ የገንዘብ አያያዝ ትምህርት እና የስራ ፈጠራ ክህሎት ስልጠና

* በተጨማሪ የ3 ወር የንግድ ማማከር እና ድጋፍ

* 9 ወር የማማከር ድጋፎች፣ የኔትዎርኪንግ እና የተለያዩ ክትትሎች በተጨማሪም ቢዝነ ፕሮቶታይፕ (prototype) የሚያስፈልገው ከሆነ ፕሮቶታይፕ መስሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ጨምሮ ነጻ የማምረቻ ላብራቶሪ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅታችንን በመጨረስ ላይ እንገኛለን።

በስልጠናው የሚሳተፉ፦

- የሥራ ፈጠራ ክህሎቱን ማዳበር እና ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች መጠቀም የሚፈልግ፤

- በግብርና፣ ጤና፣ አገልግሎት፣ ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ እና ሌሎችም ዘርፎች የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ቅድሚያ እንሰጣለን፤

- ሴት የሥራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ እናበረታታለን።

በሥልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ እና የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ እስከ ሰኞ ጥር 29፣ 2015 ዓም ተመዝግባችሁ ስልጠናውን እና ሌሎች አገልግሎቶቹን በነጻ መውሰድ ትችላላችሁ።

መመዝገቢያ ሊንክ፡ https://forms.office.com/r/6jrgpFiwtt

@tikvahethmagazine