Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ የሥጋ ምርቷን ወደ ቻይና እና ኢንዶኔዥያ ገበያዎች ለመላክ የሚያስችሉ የዝግጅት ሥራዎችን | TIKVAH-MAGAZINE

ኢትዮጵያ የሥጋ ምርቷን ወደ ቻይና እና ኢንዶኔዥያ ገበያዎች ለመላክ የሚያስችሉ የዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነች መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ በዓመት ከ200 ሺህ ቶን በላይ የሥጋ ምርት ለውጭ ገበያ የማቅረብ አቅም ቢኖራትም አሁናዊ አቅርቦቷ ግን ከ22 ሺህ ቶን አይበልጥም። በዚህም የሥጋ ምርት መዳረሻ ከሆኑ የመካከለኛው ምስራቅ አገራት በተጨማሪ ወደ ሩቅ ምስራቅ ገበያ ለማስፋት እየሰራች መሆኗ ተገልጿል።

ከሦስት ዓመታት ወዲህ በዘርፉ ላይ በተሰሩ ሥራዎች ከመካከለኛው ምሥራቅ በተጨማሪ ወደ ቬትናም እና ኮሞሮስ የሥጋ ምርቷን ማቅረብ መጀመሯ ተጠቅሷል።

በተያዘው በጀት ዓመትም 28 ሺህ ቶን የሥጋ ምርት ለመላክ መታቀዱ የተገለጸ ሲሆን፤ ባለፉት ስድስት ወራት 7 ሺህ 200 ቶን ለውጭ ገበያ በማቅረብ 50 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገቢ ተገኝቷል፤ ይሁንና ካባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2 ሺህ 800 ቶን ቅናሽ ማሳየቱን ተነግሯል። (ENA)

@tikvahethmagazine