Get Mystery Box with random crypto!

Skyline media

የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
Fastmereja
የሰርጥ አድራሻ: @skyline7777
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 48.04K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኢትዮ ስካይላይን የቴሌግራም ቻናል ነው። 🙌 ዓላማችን እናንተን ውድ ተከታታዮቻችንን በቅድሚያ ማሳወቅ ፣ ማስተማርና ዘና ፈታ የሚያደርጉ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ማገልገል ነው 🙌
ቁም ነገሮች፣ ቀልዶች፣fun GIF:ትረካዎች:
መጣጥፎች ሌሎችንም ዜናዎች የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል🤗
ለጥቆማና አስተያየታችሁ
For any promotion 👉 @Skyline7777

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 34

2022-05-30 19:19:21
የቤንዚን፣ የናፍጣ እና የኬሮሲን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል
******************

በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም የቤንዚን፣ የናፍጣ እና የኬሮሲን (ነጭ ጋዝ) የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በግንቦት ወር ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የተጠቀሱት ምርቶች መሸጫ ዋጋ በዓለም ገበያ ቢጨምርም፤ መንግሥት የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ለማስቻል የምርቶቹ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ያለምንም ለውጥ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
2.0K viewsTopia Media, 16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 18:45:26 #ሀገራዊ_ምክክር

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕ/ር መስፍን አርአያ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦

" በሀገራዊ ምክክሩ #ሁሉም ኢትዮጵያዊ አጀንዳ የሚያስይዝበት አሰራር ይዘረጋል።

የውይይት ሃሳቦች ከታች ወደ ላይ ነው የሚሰበሰቡት።

በውይይቱ ይህ ይነሳ ያ አይነሳ የሚባል ነገር የለም ። ኮሚሽኑ በአጀንዳዎች ላይ ጣልቃ አይገባም።

ምክክሩ ልሂቁ ላይ ብቻ የተንጠለጠለ ባለመሆኑ ሁሉም ዜጋ ሐሳቡ በጥቂቶች እንዳይጨናገፍ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ እናቀርባለን።

በቀጣይ በየክልሉ እንደ አመቺነቱ ጽሕፈት ቤቶች ይቋቋማሉ ፤ የኮሚሽኑ ምክር ቤት መርሃ ግብር ያዘጋጀ ሲሆን ስትራቴጂክ ዕቅዱን ለባለድርሻ አካላት በማቅረብ ግብዓት ይሰበሰባል።

አጀንዳ የመሰብሰብ ሥራ በገጽ ለገጽ ማህበረሰቡ በሚረዳው ቋንቋ ስለ ኮሚሽኑ በማስረዳት ሃሳቡን እንዲገልጽ ይደረጋል። በሌሎች አማራጮችም በስልክ፣ ኢሜይል እና ፖስታ በመሳሰሉት ማቅረብም ይቻላል።

ማሕበረሰቡ ሃሳቡን ከማቅረብ በተጨማሪ በማዕከል ደረጃ ለሚደረገው ምክክር ወኪሎቹን እንዲመርጥ ይደረጋል።

የአጀንዳ ሃሳቦች መሰብሰብ የሚጀመርበት ጊዜ #በቅርቡ_ይፋ ይደረጋል። "
2.0K viewsTopia Media, 15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 10:00:33
የአዲስ አበባ ህንፃዎች ሁሉ ግራጫ ቀለም ሊቀቡ ነው በሚል ከሰሞኑ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው ሲሉ የከተማዋ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ አስታወቁ

የቢሮ ኃላፊው አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የህንፃ ስታንዳርድና የውጭ ማስታወቂያ ስታንዳርድ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው ሆኖም ግን ይህን መነሻ አድርጎ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች አዲስ አበባ ከተማ ግራጫ ቀለም ልትቀባ ነው በሚል በስፋት ሲዘዋወር የታየው መረጃ የተሳሳተ ነው ብለዋል፡፡

እስካሁን ድረስ የከተማዋ ህንጻዎች ቀለም ምን አይነት ይሁን የሚለው ጉዳይ ለውይይት ቀረበ እንጂ የከተማ አስተዳደሩ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ውሳኔ እንዳላሳለፈ አመልክተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ‹‹ከተማችን ቡራቡሬ ሆና ባለቤት አልባ መስላለች›› ማለታቸውን ያስታወሱት የቢሮ ኃላፊው ይህን ችግር ማንኛውም የመዲናዋ ነዋሪ ሊታዘብ ይችላል፤ የከተማ አስተዳደሩም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቷል ብለዋል

ችግሩን ለመፍታት የውጭ ማስታወቂያውና የከተማዋ ቀለም ሁኔታ የሚመራበት ስታንዳርድ ዝግጅት ተደረገ እንጂ ውሳኔ ላይ አለመድረሱን ጠቁመዋል

በቅርቡ በጉዳዩ ላይ ከባለሀብቶች ጋር ውይይት ተደርጎ እንደነበር ያስታወሱት ኃላፊው ይህን መነሻ አድርገው አንዳንድ ግለሰቦች ለግራጫ ቀለም የመሰላቸውን ትርጓሜ ሲሰጡ ተመልክተናል፤ ጉዳዩ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እንደሚዘዋወረው ተግባር ላይ የዋለ ሳይሆን ገና ለምክክር የቀረበ መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል

ከተማዋ ላይ አንድ አይነት ቀለም ብቻ ለቀለም ቅብ ሥራ ያስፈልጋል የሚል እሳቤ መያዝ እንደሌለበት የተናገሩት ኃላፊ ለአስፈላጊው ህንጻና አካባቢ የሚመጥን ዝብርቅርቅ ያልሆነና ለዓይን የሚማርኩ ቀለማትን የያዘ ስታንዳርድ እንደሚኖረን ይጠበቃል ብለዋል።
2.8K views@A, 07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 19:44:13
4.8K viewsTopia Media, 16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 14:15:05 https://www.facebook.com/106382618741910/posts/106430358737136/?substory_index=0&sfnsn=mo
2.5K viewsTopia Media, 11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 15:55:47
14ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመከላከያ፣ የጸጥታና ደኅንነት መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

On May 9, 2022  52

የአፍሪካ ሕብረት የመከላከያ፣ የጸጥታና ደኅንነት 14ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው ከዛሬ ግንቦት 1 እስከ ግንቦት 4 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አፍሪካ ህብረት ዋና መሥሪያ ቤት የሚካሄድ ሲሆን፥ የህብረቱ አባል አገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡

በጉባኤው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ግጭቶችን ፣ ሽብርተኝነትንና ፅንፈኝነትን እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለማስቆም እየተከናወነ ያለውን ጥረት ሪፖርት እንደሚያቀርብ ተነግሯል።

የሕብረቱን ተጠባባቂ ሃይል አቅም ለማሳደግም እየተደረገ ያለው ድጋፍና ስምሪት ላይ ያተኮረ ሪፖርት ያቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

የህፃናትን ደህንደነት ለመጠበቅ የተዘጋጀውን ረቂቅ ፖሊሲ በአፍሪካ የሰላምና ደኅንነት ፖሊሲ ውስጥ ለማካተት ያለመ ውይይት እንደሚካሄድም ተመላክቷል፡፡
5.6K viewsTopia Media, edited  12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 19:30:06
#ሜጀር_ጀኔራል_ገብረመድህን (#ወዲ_ነጮ)

አሸባሪው ህወሓት ጥቅምት 24 በሰሜን እዝ ላይ ለፈፀመው ጭካኔ የተሞላው ጭፍጨፋ አዲስ አበባ ሁኖ የመገናኛ ሬድዮዎችን በመዝጋት ሽፋን ሰጥቷል በሚል በአገር ክህደት ተከሶ ቃሊቲ ማረሚያቤት ታስሮ የቆየው #ሜጀር_ጀኔራል_ገብረመድህን (#ወዲ_ነጮ) ዛሬ ህይወቱ አልፏል።

@DondorTimes
9.6K viewsTopia Media, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 02:10:34
ከክፉዎች እራሳችሁን ጠብቁ።
10.4K viewsTopia Media, edited  23:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 23:38:04
9.8K viewsTopia Media, 20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 23:38:01 ከዓለም አቀፍ አሸባሪዎች ተቀድቶ በአማራ ላይ የተፈፀመ የሽብር ስልት

(ሚስጥራዊው የእነ አህመዲን ጀበል ሽብርን በሚዲያ የደገፉበት ሰነድ)

ከስር የምትመለከቱት የእነ አህመዲን ጀበል ቡድን የዓለም አቀፍ አሸባሪዎችን ሁነኛ የሽብር ፕሮፖጋንዳ ተከትሎ በአማራና በኦርቶዶክስ ላይ ተግባራዊ እያደረገው ያለው ነው። ሰነዱ ከአንድ አመት በፊት የተሰራ ሲሆን ላለፉት ወራት በርካቶችን አሰልጥነው ወደ ተግባር ገብተዋል። ሰሞኑን በጎንደሩም ሆነ ከዛ ቀደም ባሉት የሽብር ተግባራት የሚጠቀሙት ይህን ስልት ነው። ምን አልባት በዚህ ሰነድ ጠላትና ወዳጅ ተብላችሁ የተፈረጃችሁ ግለሰቦች፣ ሚዲያዎች፣ ፓርቲዎች ትኖራላችሁ። ተመልከቱት።

ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ለማዳን ከጠላት ጋር በተፋጠጡበት ወቅት እነ አህመዲን ጀበል የሽብር ፕሮፖጋንዳ ስራ ላይ ነበር። በቅርቡ ከገጠሙት የእነ ሙፍቲ መጅሊስ ጀምሮ በርካቶች በጠላትነት ተፈርጀዋል። ከእነ ቴዲ አፍሮ እስከነ ሀሰን ኢንጃሞ በጠላትነት ተፈርጀዋል። እነ አብንና እናት ፓርቲ በጠላትነት ተፈርጀዋል። ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ አላማቸውን የሚደግፍ ፓርቲ ተደርጎ ተቀምጧል። አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት እንቅፋት ይፈጥሩብናል ተብለዋል።

በዋነኛነት ጠላት የተባለው አማራው ነው። በፕሮፖጋንዳ እናሸብር የተባለው አማራውን ነው። የዚህ ፕሮጀክት ዋነኛ ተሳታፊ ሆነው የቀረቡት እነ አህመዲን ጀበል፣ ኢሳቅ እሸቱ፣ አብዱራሂም አህመድ፣ አብዱልጀሊል፣ ኢብራሂም ሙሉሸዋ ወዘተ ናቸው። የመጅሊሱ ከፍተኛ አመራሮች ጠላት ሲባሉ 17 ኮሚቴ ዋነኛው ደጋፊ ነው።

ይህን አላማቸውን ለማሳካት የማጥቃት ፕሮፖጋንዳን መጠቀም ቀዳሚው አጀንዳቸው እንደሆነ አስቀምጠዋል።

በአማራ ላይ የማጥቃት ፕሮፖጋንዳን እንጠቀማለን ብለው ካስቀመጧቸው 18 ስልቶች መካከል ጥቂቶቹ!
~ወጥመድ ውስጥ መክተት
~ማዋረድ
~ ፍርሃት መፍጠር
~ ችግራቸውን ማባባስ
~ማስጨነቅ
~ ጥርጣሬ መዝራት
~አንድነታቸውን መበታተን
~ማደናቀፍ ወዘተ ናቸው

ይህን ሁሉ በአማራ ላይ አድርገውታል። እያደረጉትም ይገኛሉ። ራሳቸው ሽብር ከፈጠሩ በኋላ እየፈፀሙት ያሉት በሙሉ በእነዚህ ሰነዶች የፃፏቸውን ነው። ይህን ሽብር የሚደግፍ ፋይናንስ ከተለያዩ አካላት አግኝተዋል። ይህን አላማ በአማራና በኦርቶዶክስ ላይ እየፈፀመ ነው። ሽብር ነው። ሽብርን በሚዲያ ማስፋፋት ነው። አልቃይዳ ይህንኑ አድርጎታል። ስልቱ ቃል በቃል የተቀዳውም ከአልቃይዳና ከሌሎች አሸባሪዎች ነው።


(የእነዚህን አሸባሪዎች በሕዝብ ላይ ያቀዱት ሕዝብ ይነቃበት ዘንድ ብታጋሩት ይመከራል)
8.7K viewsTopia Media, 20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ