Get Mystery Box with random crypto!

የቤንዚን፣ የናፍጣ እና የኬሮሲን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ***************** | Skyline media

የቤንዚን፣ የናፍጣ እና የኬሮሲን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል
******************

በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም የቤንዚን፣ የናፍጣ እና የኬሮሲን (ነጭ ጋዝ) የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በግንቦት ወር ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የተጠቀሱት ምርቶች መሸጫ ዋጋ በዓለም ገበያ ቢጨምርም፤ መንግሥት የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ለማስቻል የምርቶቹ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ያለምንም ለውጥ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።