Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካ በጥንቆላ ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች ጥንቆላ በአሜሪካ ለ100 ሺህ ገደማ ዜጎች | Skyline media

አሜሪካ በጥንቆላ ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች

ጥንቆላ በአሜሪካ ለ100 ሺህ ገደማ ዜጎች ስራ እድል ሲፈጥር 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢም አስገኝቷል።

አሜሪካ በጥንቆላ ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች
ዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ከዚህ በፊት ጥንቆላ እና ከዚሁ ጋር የተያያዙ ሁነቶችን በይፋ አግዳ ነበር፡፡

በተለይም በቨርጂኒያ ግዛት ጥንቆላ በተለያዩ መንገዶች በስፋት ከሚፈጸሙባት ግዛቶች መካከል ዋነኛዋ ስትሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የተጠቃሚዎች መብዛት ህጉ እንዲሻር ምክንያት ሆኗል፡፡

የ45 ዓመቷ አሽሊ ብራንተን በዚሁ ግዛት ላለፉት ዓመታ በጥንቆላ ሙያ ተሰማርታ ማሳለፏን እና የደንበኞቿ ቁጥርም በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ለቪኦኤ ተናግራለች፡፡

ወደ ጥንቆላ ሙያ ከመግባቷ በፊት የስነ ውበት ባለሙያ እንደ ነበረች የምትናገረው ብራንተን ሰዎች ስለ ጥንቆላ ያላቸው አመለካከት ያለ ማስታወቂያ በየጊዜው እየጨመረ መጥቷል ብላለች፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ በተለይም ከባድ ውሳኔ ያለባቸው ሰዎች፣ የተበላሸ የፍቅር ግንኙነት ያላቸው እና ከሀገር ሀገር የሚያጓጉዝ ስራ ያለባቸው ሰዎች ዘብዝተው ወደ እሷ ይመጣሉ፡፡

አብዛኞቹ ደንበኞቿ ለዚሁ ስራ ተብለው የተዘጋጁ ካርዶች ወይም የእጣ ፈንታ ማንበቢያ ካርድን የሚጠቀሙ እንደሆኑ የምታነገረው ይህች አሜሪካዊት ጠንቋይ ደንበኞቿ ትንበያዎቿን እንደሚወዱት እና እንደሚሳካላቸውም አክላላች፡፡

አሜሪካ ጥንቆላን በይፋ ህገ ወጥ ነው ብላ አውጃ ቢሆንም በርካታ የሀገሬው ዜጎች ግን በድብቅ ሲጠቀሙ መቆየታቸውን በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

የተጠቃሚዎችን መብዛት ተከትሎ ጥንቆላ ህገ ወጥ መሆኑ የቀረ ሲሆን ባሳለፍነው ዓመት ብቻ ይህ ዘርፍ ለ100 ሺህ አሜሪካዊያን የስራ እድል እንደፈጠረ እና 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱ ተገልጿል፡፡

የቨርጂኒያ ከተማ ህግ አውጪ ምክር ቤት በጥንቆላ ላይ ተጥሎ የነበረውን እግድ በይፋ ማንሳቱ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

በአሜሪካ ከዚህ በፊት በተደረገ ጥናት ከ10 አሜሪካዊያን አራቱ በጥንቆላ የሚያምኑ ሲሆን ከ10ሩ ዜጎች ውስጥም ቢንስ አንዱ ጠንቋዮችን አማክሮ ያውቃል ተብሏል ሲል አልአይን ዘግቧል። ጫደታ