Get Mystery Box with random crypto!

ጦርነትን ኖረንበታል። የተወሰኑ ችግሮቻችንን ፈትተንበታል። አብዮትን ደጋግመነዋል። የተወሰኑ ችግ | Skyline media

ጦርነትን ኖረንበታል። የተወሰኑ ችግሮቻችንን ፈትተንበታል።

አብዮትን ደጋግመነዋል። የተወሰኑ ችግሮችን ፈትተንበታል።

በሁለቱም ያልተፈቱትን ችግሮች ለመፍታት የቀረን መንገድ ምክክር ነው።

ምክክርን ግን አልተጠቀምንበትም።

ጦርነትና አብዮት የተሟላ መፍትሔ የማያመጡት አሸናፊ እና ተሸናፊ ስለሚያስከትሉ ነው።

ቢዘገይም የተሸነፈው ለማሸነፍ ይታገላል። ያሸነፈውም ድሉን ለመጠበቅ ይዋጋል።

ምክክር ግን ሁሉንም አሸናፊ ያደርጋል። ከተሸነፍንም ሁላችንም ለሀገራችን ብለን ነው የምንሸነፈው።

ይሄ የምክክር ሂደት ሦስት ነገሮች ያስገኝልናል።

1. ሁሉንም ባይሆን እንኳን ዋና ዋና ችግሮችን ይፈታል
2. ከጦርነት ይልቅ ምክክር ባህል እንዲሆን ያደርጋል
3. በተቃራኒ ኃይሎች መካከል መቀራረብና መግባባት ይፈጥራል። ይሄንን መቀራረብ በመጠቀምም ወደፊት በጉዳዮች እየተነጋገርን ለመቀጠል ያስችለናል። በመሆኑም ይኽንን እድል ሳናበላሽ ወደ ተሟላ ድል እንድናሸጋግረው እጠይቃለው።