Get Mystery Box with random crypto!

የከባድ መኪና ሹፌሮች ኦሮሚያ ክልል ውስጥ መስራት አስቸጋሪ ኾኖብናል ማለታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። | Skyline media

የከባድ መኪና ሹፌሮች ኦሮሚያ ክልል ውስጥ መስራት አስቸጋሪ ኾኖብናል ማለታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የከባድ መኪና ሹፌሮች፣ "የኮቴ" በሚል በእያንዳንዱ ኬላ ላይ በሕገወጥ መንገድ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚከፍሉ መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። ባንድ ኬላ ላይ የተሰጠ ደረሰኝ ሕጋዊ ይኹን አይኹን እንደማይታወቅና ቀጣዩ ኬላ ላይ ደረሰኙን አሳይቶ ገንዘብ ሳይከፍሉ ማለፍ እንደማይቻልም አሽከርካሪዎች መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። አሽከርካሪዎች ለኦሮሚያ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ማጠናከሪያ በሚል ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ እንደሚገደዱም ተናግረዋል።(ዋዜማ)