Get Mystery Box with random crypto!

የሶማሌላንዱ ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ አብዲ የኢትዮጵያና የሶማሌላንድን የባህርበር ስምምነት በዛሬው | Skyline media

የሶማሌላንዱ ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ አብዲ የኢትዮጵያና የሶማሌላንድን የባህርበር ስምምነት በዛሬው እለት ለፓርላማ አቅርበዋል።

"ሁለታችንም የምንፈልገው ይታወቃል ኢትዮጵያ ባህር በር ትፈልጋለች፣ እኛም እድሜ ዘመናችንን ሀገር ለመሆን ታትረናል ።

" ያሉት ፕሬዝደንት ሙሴ ...ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር "ስምምነት ከሰሞኑን ይፈፀማል ፤ ከኢትዮጵያ ጋር ግልፅ የሆነ ስምምነት ላይ ደርሰናል፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ታገኛለች እኛም የሀገርነት እውቅና ከኢትዮጵያ ይሰጠናል ሁሉም ስምምነቶች አልቀዋል መፈረም ብቻና ለፓርላማዎቻችን ማፅደቅ ነው የቀረን ብለዋል።

በሌላ በኩል ሁለቱ ሀገራት የተግባር እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ ሲሆን የሶማሌላንድ ፖሊስ ኦፊሰሮች በኢትዮጵያ ሀዋሳ ከተማ ስልጠና መውሰድ ጀምረዋል። በተጨማሪም የሶማሌላንድ አየር መንገድ ለማቋቋም ዝግጅት የተጀመረ ሲሆን ሶማሌላንድ 4 የመለማመጃ አነስተኛ አውሮፕላኖችን መግዛቷን ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ ተናግረዋል።