Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxtewahedo
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 47.96K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ።
‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ››
ት.ኢሳ 58÷3
https://youtu.be/csxxAMGtC4I
ለመቀላቀል
http://t.me/ortodoxtewahedo

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-24 15:56:42
“እስከ ትበጽህ ለሞት ተበዓስ በእንተ ጽድቅ እስመ እግዚአብሔር አምላክከ ይትበአስ
በእንቲአከ”

“እስክትሞት ለእውነት ታገል። እግዚአብሔር ላንተ ይታገልለሀልና”

           ሲራክ 4 ፡ 2

ምዕመናን መረጃ ይደርሳቸውና ይነቁ ዘንድ ይሄን ሊንክ ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ አድርሱ ቀላል የሚመስል ግን ብዙ ጥቅም አለው አድርጉት።

በዚ ግዜ ለዚያልሆንን መቼ ልንታዘዝ ነው። 

#share #share #share 

http://t.me/ortodoxtewahedo
1.7K viewsedited  12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 15:54:15
“ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ፤ ደማቸውን ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ፤ ስለ መንግሥተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሱ፡፡”

የኅሙስ ውዳሴ ማርያም

ወኢያረትዕ ቅድሜየ ዘይነብብ ዐመፃ
አመጻን የሚናገር በፊቴ አይጸናም

     መዝ 100:1

በትቢት እና በአመጽ የተሞላችሁ የዱድያኖስ ግብራ አበሮች ወደ ልባችሁ ተመለሱ እንቢ ካላችሁ ግን ብርቱዎችን ደካማ የሚያደርገው የእግዚአብሔርን ክንድ አትችሉትም።


ምዕመናን መረጃ ይደርሳቸውና ይነቁ ዘንድ ይሄን ሊንክ ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ አድርሱ ቀላል የሚመስል ግን ብዙ ጥቅም አለው አድርጉት።

በዚ ግዜ ለዚያልሆንን መቼ ልንታዘዝ ነው። 

#share #share #share 

http://t.me/ortodoxtewahedo
1.4K views12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 15:54:15
መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናል።”

— 2ኛ ቆሮ 5፥10

ምዕመናን መረጃ ይደርሳቸውና ይነቁ ዘንድ ይሄን ሊንክ ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ አድርሱ ቀላል የሚመስል ግን ብዙ ጥቅም አለው አድርጉት።

በዚ ግዜ ለዚያልሆንን መቼ ልንታዘዝ ነው። 

#share #share #share 

http://t.me/ortodoxtewahedo
1.2K views12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 15:50:12
ከጴጥሮሳውያን የማኅበራት ኅብረት
የተሰጠ መግለጫ ::

@ortodoxtewahedo
1.3K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 15:45:06
1.3K views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 15:26:27
#ብፁዓን አባቶች ጅጅጋ ገቡ።

ዛሬ በጅጅጋ ከተማ በገራድ ዊልዋል አየር መንገድ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው በቅዱስ ሲኖዶስ አዲስ የተሾሙት ብፁዓን ኤጲስ ቆጶሳት እና ብፁዓን አባቶች ብፁዕ አቡነ መቃሪዮስ
የሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ
የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ
ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ
የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ
ብፁዕ አቡነ ገሪማ
የጌዴኦ አማሮ ና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ
በምስራቀ ፀሀይ ቅድስ ኪዳነምሕረት እና ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ሲገቡ የቤተክርስቲያን ሊቃውት ካህናት አባቶች የአብያተ ቤተክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች የሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ ሀላፊዎች እና ሰንበት ትምህርት ቤቶች እና ማኀበራት እና ምእመናን በመገኘት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

መረጃ ምንጭ :አማኑኤል የጅጅጋ ወጣቶች መንፈሳዊ ማኀበር

@ortodoxtewahedo
1.3K views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 15:26:23
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ተጉዘዋል።

ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አአባ)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን የሐምሌ 2015 ዓ.ም የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግሥ ለማክበር ዛሬ ድሬዳዋ ከተማ ገብተዋል ።

ዛሬ ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ,ም ቅዱስነታቸው ድሬዳዋ ከተማ ሲገቡ በአውሮፕላን ማረፊያ እና በመንበረ ጵጵስናው ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የድሬዳዋ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና የድሬዳዋ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ካህናትና ምእመናን ደማቅ አቀባበል አድርውላቸዋል።

ቅዱስነታቸው በአቀባበሉ ላይ ለተገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል ።

@ortodoxtewahedo
1.2K views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 07:36:13 በዘመነ ክረምት አዝርዕቱ በስብሰው ከበቀሉ፣ ካበቡና ካፈሩ በኋላ የሚጠቅሙት በሪቅ፣ በጎተራ እንደሚሰበሰቡ፣ እንክርዳዶቹ ደግሞ በእሳት እንደሚቃጠሉ ሁሉ እኛም ተወልደን፣ ተጠምቀን፤አድገን፣ ዘራችንን ተክተን እንደምንኖር፣ ዕድሜያችን ሲያበቃም እንደምንሞት፣ ሞተንም እንደምንነሣና መልካም ሥራ ከሠራን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንደምንገባ፣ በኀጢአት ከኖርን ደግሞ በገሃነመ እሳት እንደምንጣል የምንማርበት ወቅት ነው፡፡ በመሆኑም ሰይጣን በሚያዘንበው የኀጢአት ማዕበል እንዳንወሰድና በኋላም በጥልቁ የእሳት ባሕር እንዳንጣል ዅላችንም ቅዱሳት መጻሕፍትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያዘጋጁልንን የቃለ እግዚአብሔር ዘር በእርሻ ልቡናችን በመዝራት (በመጻፍ) እንደየዓቅማችን አብበን፣ ያማረ ፍሬ አፍርተን መንግሥቱን ለመውረስ መዘጋጀት ይኖርብናል፡፡
2.3K views04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 07:35:45 በአተ ክረምት (ዘርዕ፣ ደመና)

ከሰኔ ፳፮ እስከ ሐምሌ ፲፰ ቀን ድረስ ያለው የመጀመሪያው የክረምት ክፍለ ጊዜ ‹በአተ ክረምት› ወይም ‹ዘርዕ፣ ደመና› ይባላል፡፡ ‹በአተ ክረምት› ማለት ‹የክረምት መግቢያ፣ መጀመሪያ› ማለት ነው፡፡ በዚህ ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን ስለ ክረምት መግባት፣ ስለ ዘርዕ፣ ስለ ደመና እና ስለ ዝናም የሚያዘክሩ መዝሙራትና ምንባባት ይዘመራሉ፣ ይነበባሉ፡፡ ይህ ወቅት ደመና ሰማዩን የሚሸፍንበት፣ የዝናም መጠን የሚያይልበትና መሬት በዝናም ረክታ ዘር የምታበቅልበት ጊዜ ነውና፡፡

                    ዘርዕ

ምድር ከሰማይ ዝናምን፣ ከምድርም ዘርን በምታገኝበት ወቅት ዘሩን አብቅላ ለፍሬ እንዲበቃ ታደርጋለች፡፡ በምድር የምንመሰል የሰው ልጆችም ከእግዚአብሔር ባገኘነው ጸጋ ተጠቅመን፣ ከቅዱሳት መጻሕፍት እና ከመምህራነ ቤተ ክርስቲያን የምናገኘውን ቃለ እግዚአብሔር በተግባር ላይ ማዋል እንደሚገባን ከምድር እንማራለን፡፡ ይህን ካደረግን ዋጋችን እጅግ የበዛ ይኾናል፣ ከዚህም አልፎ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ እንበቃለን፡፡ የተዘራብንን ዘር ለማብቀል ማለትም ቃሉን በተግባር ለማዋል ካልተጋን ግን በምድርም በሰማይም ይፈረድብናል፡፡ ‹‹ምድርም በእርስዋ የሚወርደውን ዝናብ ከጠጣች፣ ያን ጊዜ ስለ እርሱ ያረሱላትን መልካም ቡቃያ ታበቅላለች፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድም በረከትን ታገኛለች፡፡ እሾኽንና ኵርንችትን ብታወጣ ግን የተጣለች ናት፡፡ ለመርገምም የቀረበች ናት ፍጻሜዋም ለመቃጠል ይኾናል፣›› በማለት ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ገለጸው (ዕብ. ፮፥፯-፰)፡፡

በቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ፲፫፥፩-፳፫ እንደ ተገለጸው ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የክርስትና ሕይወትን ከዘርና ፍሬ ጋር በማመሳሰል አስተምሯል፡፡ ይኸውም አንድ ገበሬ ዘር ሲዘራ በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር ከመብቀሉ በፊት በወፎች እንደ ተበላ፣ በጭንጫ ላይ የተጣለውም ወዲያውኑ ቢበቅልም ነገር ግን ሥር መስድድ አልቻለምና፡፡ በፀሐይ ብርሃን እንደ ጠወለገ፤ በእሾኽ መካከል የወደቀው ደግሞ ሲበቅል በእሾኽ እንደ ታነቀ፣ ከሁሉም በተለየ መልኩ በመልካም መሬት ላይ የተጣለው ዘር ግን አድጎ መቶ፣ ስድሳ፣ ሠላሳ ፍሬ እንደ ሰጠ የሚያስረዳ ነው፡፡

ይህም ምሳሌ አለው፡፡ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ተረጐመው በመንገድ ዳር የተዘራው ዘር የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ የማያስተውል (ልብ የማይል) ክርስቲያን ምሳሌ ነው፣ እንደዚህ ዓይነቱ ምእመን ሙሉ እምነት ስለማይኖረው በመከራው ጊዜ አጋንንት ድል ያደርጉታል፡፡ በጭንጫ ላይ የተዘራው ደግሞ ቃሉን ሰምቶ ወዲያው በደስታ የሚቀበል፣ ነገር ግን ተግባራዊ የማያደርግ (የማይተገብር) የክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡ ይህ ምእመንም በጠንካራ እምነት ላይ የጸና አይደለምና በሃይማኖቱ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በደረሰበት ጊዜ ፈጥኖ ይክዳል፡፡ በእሾኽ መካከል የተዘራውም ቃሉን የሚሰማ ቢሰማም ግን በዚህ ዓለም ዐሳብና ባለ ጠግነት ተታሎ ቃሉን የማይተገብር ክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡

በመልካም መሬት የተዘራው ደግሞ ቃሉን ሰምቶ ተግባር ላይ የሚያውል ክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ምእመን በተማረው ትምህርት ጸንቶ ይኖራል፣ መልካም ሥራም ይሠራል፡፡ በመልካም መሬት የተዘራው ዘር ስለ አንዱ ፋንታ መቶ፣ ስድሳ፣ ሠላሳ እንደሚያፈራ ሁሉ በክርስቲያናዊ ግብር ጸንቶ የሚኖር ምእመንም ሥራውን በሦስት መንገድ ማለትም በወጣትነት፣ በማእከላዊነትና በፍጹምነት ደረጃ እንደሚፈጽም፣ ዋጋውንም በሥራው መጠን እንደሚያገኝ የሚያስረዳ ነው፡፡ በሌላ በኩል ባለ መቶ ፍሬ የሰማዕታት፣ ባለ ስድሳ የመነኮሳት፣ ባለ ሠላሳ በሕግ ተወስነው በዓለም የሚኖሩ ምእመናን ምሳሌ ነው፡፡ በተመሳሳይ ምሥጢር ሁሉም የፍሬ መጠን በሁሉም ጾታ ምእመናን ሕይወት ውስጥ እንደሚገኝ የትርጓሜ ሊቃውንት ያስተምራሉ፡፡ ስለዚህም በሰማዕትነትም፣ በምንኵስናም፣ በዓለማዊ ሕይወትም ውስጥ የሚኖሩ ምእመናን መልካም ግብራቸው እጅግ የበዛ ከሆነ በባለ መቶ ፍሬ፣ መካከለኛ ከሆነ በባለ ስድሳ፣ ከዚህ ዝቅ ያለ ከሆነ ደግሞ በባለ ሠላሳ ፍሬ ይመሰላል፡፡ (ትርጓሜ ወንጌለ ማቴዎስ፣ ማቴ. ፲፫፥፩-፳፫)፡፡

                ደመና

እግዚአብሔር አምላካችን የውቅያኖስ እና የሐኖስ ድንበር ይሆን ዘንድ በውኃ መካከል ጠፈርን ፈጥሮ ከጠፈር በታች (በዚህ ዓለም) ያለው ውኃ በአንድ ቦታ እንዲወሰን አድርጎታል፡፡ ከዚያም ከምድር እስከ ብሩህ ሰማይ ድረስ የነበረውን ውኃ ከሦስት ከፍሎ ሢሶውን አርግቶ ጠፈር ብሎ ሰይሞታል፡፡ ከጠፈር በላይ ያለውን ሢሶውን የውኃ ክፍል ሐኖስ ብሎታል፡፡ ሢሶውንም ይህንን ዓለም ከሰባት ከፍሎ ሰባተኛውን ዕጣ አጐድጕዶ በዚያ ወስኖ ስሙን ውቅያኖስ ብሎ ጠርቶታል፡፡ የብሱን ክፍል ደግሞ ምድር ብሎ ሰይሞታል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ከደረቅ ምድር ደረቅ ጢስን፣ ከርጥብ ባሕር ርጥብ ጢስን አስወጥቶ እንደ ጉበት በለመለመች ምድር ላይ ደመናን አስገኝቷል (ትርጓሜ መዝሙረ ዳዊት፣ መዝ. ፻፴፬፥፯)፡፡

ደመና፣ ዝናምን የሚሸከም የማይጨበጥ፣ የማይዳሰስ ጢስ መሰል ፍጥረት ነው፡፡ በትነት አማካይነት፣ በደመና ተሸካሚነት ከውቅያኖሶች እና ከወንዞች እየተቀዳ ወደ ሰማይ ተወስዶ እንደ ገና ተመልሶ ወደ ምድር የሚጥለው ውኃ ዝናም ይባላል፡፡ ይኸውም በእግዚአብሔር ጥበብ በደመና ወንፊትነት ተጣርቶ ለፍጡራን በሚመችና በሚጠቅም መጠን በሥርዓት ይወርዳል፡፡ ‹‹ያጸንዖ በፍኖተ በድው ከመ ይዝንም ብሔረ ኀበ አልቦ ሰብእ ወኢይነብሮ ዕጓለ እመሕያ፣ ዝናሙን ሰው በሌለበት በምድረ በዳ ያዘንመዋል፤›› እንዳለ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በቅዳሴው፡፡ ይህ ኃይለ ቃል እግዚአብሔር በረዶውን በምድረ በዳ አፍስሶ የጠራውን ውኃ ሰው ወዳለበት እንዲዘንም ማድረጉን የሚያስረዳ መልእክት የያዘ ሲሆን፣ ምሥጢሩም ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንበለ ዘርዐ ብእሲ (ያለ ወንድ ዘር) በልዩ ጥበቡ ተፀንሶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱንና በተዋሐደው ሥጋ በምድር ተመላልሶ ወንጌልን ማስተማሩን፣እንደዚሁም ‹‹ሑሩ ወመሀሩ፤ ሒዱና አስተምሩ›› ብሎ ቅዱሳን ሐዋርያትን በመላው ዓለም ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት ማሰማራቱን ያመለክታል (ትርጓሜ ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ፣ ፪፥፭-፮)፡፡

ዘመነ ክረምት ስለ ሥነ ፍጥረት ዘርዘር ባለ መልኩ የሚነገርበት፤ ፍጡርን ከፈጣሪ መናን (ምግብን) ከተመጋቢ ለይቶ የሚያሳይ እና የሚያሳውቅ ዘመን ነው፡፡ በዚህ ወቅት የውኃ ባሕርይ ይሠለጥናል፣ ውኃ አፈርን ያጥባል፣ እሳትን ያጠፋል፡፡ ሆኖም ግን ውኃ በብሩህነቱ ከእሳት፣ በቀዝቃዛነቱ ከነፋስ፣ በእርጥብነቱ ከመሬት ጋር ተስማምቶ ከሦስቱ ባሕርያት ጋር ይኖራል፡፡ ይህን ምሥጢር ከሕይወታችን ጋር አያይዘን ስንመለከተው ዘመነ ክረምት የክርስትና ምሳሌ ነው፡፡ በክረምት ወቅት ገበሬው ብርዱንና ዝናሙን ሳይሳቀቅ ለሥራ ይሰማራል፣ በበጋው የእጁን ፍሬ ያገኝ ዘንድ የክረምቱን መከራ ይታገሣል፡፡ ይህም ምእመናን በሰማያዊው ዓለም የምናገኘውን ተድላና ደስታ በማሰብ በምድር ቆይታችን ወቅት የሚደርስብንን ልዩ ልዩ መከራ በትዕግሥት ማሳለፍ እንደሚገባን ያስገነዝባል፡፡

@ortodoxtewahedo
2.2K viewsedited  04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 07:33:33 "አእምሮ የክርስቲያን ሕይወት ዓላማን የማይረዳ ከኾነ በጎ ምግባራት መሥራቱ ብቻውን ጥቅም የለውም ትርፍም አያስገኝም።"

          ቀሌሜንጦስ ዘሮም

@ortodoxtewahedo
1.7K viewsedited  04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ