Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxtewahedo
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 47.96K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ።
‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ››
ት.ኢሳ 58÷3
https://youtu.be/csxxAMGtC4I
ለመቀላቀል
http://t.me/ortodoxtewahedo

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-06-09 14:01:16
ይህንን ያውቁ ኑሯል

የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል የተተከለው በ1905 ዓ.ም በልጅ ኢያሱ ዘመነ መንግሥት ነው። የመጀመሪያውን መቃኞ ያሰሩት ፊት አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ሲሆኑ ጽላቱም በጎንደር ክፍለ ሀገር የነበረና ከዚያ መጥቶም በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተቀመጠ ነበር።

ታድያ ፊት አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ያሰሩት የመጀመርያው መቃኞ ለአገልግሎት ምቹ ስላልነበር ሁለተኛ መቃኞ ድጋሚ ተሰርቶ ታቦቱ እንዲገባ ተደርጓል።

ንግስት ዘውዲቱ በግንቦት 28 በ 1914 ዓ.ም የዐማኑኤልን በዓል ተገኝተው ሲያስቀድሱ ምርጊቱ ተደርምሶ ሲወድቅ በማየታቸው ሦስተኛ መቃኞ እንዲሰራ አዘዙ። የደብሩ አስተዳዳሪ በጊዜው የተክለ ሃይማኖትን ቤተ ክርስትያንም አንድ ላይ ያስተዳድሩ የነበረ በመሆኑ ንግስቲቷ የቤተ መንግስታቸውን አጣኝ የመጀመርያው አስተዳዳሪ ሆነው ደብሩን እንዲጠብቁ አደረጉ። አለቃው ሦስተኛ መቃኞ አሰርተው ታቦቱ ወደ ተዘጋጀለት መቃኞ ገባ።

በ1920 ህዝቡ እየበዛ በመምጣቱ አገልግሎቱ እንዲሰፋ ስላስፈለገ በንግስት ዘውዲቱ አማካኝነት አዲስ ሕንጻ ቤተ መቅደስ ግንባታ ተጀመረ። በ1931 ታህሳስ 28 ቀን ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ታቦቱ ወደ መንበሩ ገብቷል። ንግስት ዘውዲቱ ፍጻሜውን ሳያዩ ያረፉ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ደግሞ ክብ ቅርጽ ነበረው።

አሁን ያለው ቤተ ክርስቲያን በጥር 28 ቀን 1969 ዓ.ም በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ግንባታው የተጀመረ ሲሆን የወቅቱ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ በነበሩት በሊቀ ሊቃውንት ንቡረ ዕድ አባ ተፈራ መልሴ አስተባባሪነት በምእመናን ርብርብና በቅዱስ ዐማኑኤል አከናዋኝነት ግንቦት 28 ቀን 1978 ዓ.ም ተጠናቆ ታቦተ ህጉ ወደ ህንጻ ቤተ ክርስቲያን ገብቷል።

@ortodoxtewahedo
2.6K viewsedited  11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 08:11:18 የንጉሥ ሥልጣን በሥጋ ላይ ነው፤ የካህን ሥልጣን ግን በነፍስ ላይ ነው፡፡  ንጉሥ ይቅር ቢል የገንዘብን ዕዳ ነው፤ ካህን ይቅር ሲል ግን የበደል የኃጢአት ዕዳን ነው፡፡

ንጉሥ ያዝዛል፤ ካህን ግን ያስተምራል ይዘክራል፡፡ ንጉሥ ያስገድዳል፤ ካህን ግን ነጻ ፈቃድን ያያል፡፡

ንጉሥ ቁሳዊ የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፤ ካህን ግን ረቂቅ (መንፈሳዊ) የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፡፡ ንጉሥ የጦር ዕቃ መሣሪያውን ቢሰብቅ አንገዛም ብለው ባመፁት (እንዲሁም ከወራሪዎች ሥጋውያን ደማውያን) ላይ ነው፤ ካህን ግን ውጊያው ከጨለማ አበጋዞች ከአጋንንት ጋር ነው፡፡

ስለዚህ ሥልጣነ ክህነት ከሥልጣነ መንግሥት ይበልጣል፡፡ እንዲህም በመኾኑ ንጉሥ አንገቱን ለካህናት እጅ ያጎነብሳል፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ትንቢተ ኢሳይያስ፣ ድርሳን ፬ በተረጎመበት ድርሳኑ)

@ortodoxtewahedo
4.1K viewsedited  05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 21:39:11
በደብረ ኤልያስ በአብይ የሚመራው መንግስት የደረሰ ጭፍጨፋ ።

@ortodoxtewahedo
4.2K viewsedited  18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 20:07:26
++ እንኳን ወደ ጉባኤ ቤትዎ በሰላም ተመለሱ ++
---------------------------

መምህር የኔታ ኃይለ ማርያም ዘውዱ ከ27 የእስር ቀናት በኋላ ዛሬ ተለቀዋል ፡፡ የኔታ እንኳን ወደ ጉባኤ ቤትዎ በሰላም ተመለሱ! እግዚአብሔር የተገፉትን ይሰማል እግዚአብሔር የእናቶችን የሲቃ ጩኸት እንደ ራሔል ፈጥኖ ያደምጣል ፡፡ በእንባ በጸሎት ያሰባችኋቸው በሙሉ የአበው በረከት ይጠብቃችሁ፡፡

@ortodoxtewahedo
3.7K views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 20:07:05
የህንድ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ
"ማለቂያ የሌለው ሀዘን" ሲሉ ገልፀውታል

ትናንት በህንድ ከፍተኛ የባቡር አደጋ የደረሰ ሲሆን ከ260 በላይ ንፁሀን የሞቱ ሲሆን ከ1000 በላይ በሚሆኑት ደግሞ ከባድና ቀላል አደጋ ደርሶባቸዋል።

ይህንን አደጋ በማስመልከት ፓትርያርኩ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በደረሰው አደጋ ከልብ ማዘናቸውን በመግለጽ ለሞቱት ነፍሳቸውን ይማር ለተጎዱት ደግሞ ፈጣሪ ምህርት እንዲያደርግላቸው እንፀልያለን ብለዋል።

ፓትርያርኩ "ማለቂያ የሌለው ሀዘን" በሚል በገለፁበት መልዕክታቸው ህንዳውያንና መላው ዓለም በዚህ አደጋ ለሞቱትና ለተጎዱት ሁሉ በፀሎት እንዲያስቧቸው በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ለሞቱት ነፍስ ይማር ለተጎዱት ምህረት ያውርድላቸው

@ortodoxtewahedo
3.1K views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 22:29:38
ጥቂት ባለ ስርዓቶች እልፍ ስርዓት አልበኞችን ይረታሉ።
***

ሰዶም 5 ጻድቃን ቢገኝባት የሰማይ መስኮት ተከፍቶባት ባልጠፋች ነበር።

ዕብራውያን ከግብጽ በወጡበት ዘመን በመቅሰፍት ያላለቁት ሙሴን የመሰለ ቅን እረኛ ስለያዙ ነው።

ህዝበ እስራኤል ቡሩክ ይባሉ ዘንድ የአብርሃም ከካራን መውጣት እንጅ የእነርሱ ጽድቅ መስፈርት አልነበረም።

ዛሬም ቅድስት ቤተክርስቲያን በጥቂት ደጋግ አባቶች የመንፈስ ቅዱስ ማደርያነት ይህን ወጀብ ታልፍ ዘንድ እንደሚያስችላት አምላኳ የታመነ ነው።

በጩኸት መቅደሷን ለመክፈል ፣ ስርዓት ለመጣስ ከሚሯሯጡባት እልፍ ሰዎች ይልቅ በዝምታ ታምር የሚሰሩ ጥቂት የአብ ተክሎች በቤታችን እንደሚኖሩ እናምናለን !!!

በቅድስና የቆሙ፣ከስርዓተ ቤተክርስቲያን ወግነው የጸኑ ጥቂቶች ድንበር ለማፍለስ ስርዓት ለመጣስ ከሚዝቱ ብዙኃን ይልቅ ለእግዚአብሔር የቀረቡ ናቸው ።

እንደ ጊያዝ የጠላቶቻችንን ጉልበት ብቻ አይተን እንዳንፈራ ኃይልህን እንድንመለከት የመንፈስ አይናችንን ግለጥ!!!

እግዚአብሔር ይመስገን !!!

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

@ortodoxtewahedo
1.1K viewsedited  19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 17:58:12
1.9K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 17:58:03 ጥያቄ ብቻ ነው።

በዚህ የምትቀየሙ ሁሉ፣ ሳላውቅ የበደልኳቸሁ ካላችሁም ይቅር በሉኝ፣ እንድትድን ለምን ትጠይቃለህ ግን አትበሉኝ። እንድድን በወልደ እግዚአብሔር ሞት ተጠርቻለሁና።

@ortodoxtewahedo
1.8K viewsedited  14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 17:58:03 ቅዱስ ሲኖዶስ ሠራኤ ሕግ ወፈጻሜ ሕግ የሆነውን ጌታቸውን የተከተሉ፣ ሙጽአ ሕግ የሆነችውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተልእኮ በሕገ እግዚአብሔር በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የሚያስፈጽሙ አባቶች ስብስብ እንደሆነ አምናለሁ፣ አውቃለሁም።

ለዚህም ነው በዘወትር ጸሎታችን ያለውን እንደ ሁሉም ክርስቲያኖች ሁሉ ዕለት ዕለት “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት” ብለው ያስተማሩኝን የማምነው፣ የምመሰክረው፣ የምጸልየውም።

ቤተ ክርስቲያን ከጉባኤያት ፣ ከምክር ቤቶች፣ ከስብሰባዎች ሁሉ በላይ የሆነችውም በተፈጥሮዋም፣ በአሠራሯም፣ በሂደቷም ከሁሉም በላይ በሆነው በጌታዋ በቤዛዋ በመድኃኒቷ እንዲህ ጸንታ የምትኖር ስለሆነች እና መሆንም ስላለባት እንደሆነ አውቃለሁ፣ አምናለሁም።

አንዳንድ ሰዎች ዘመን ሰጠን፣ ጉልበት አገኘን ብለው ይህን አስትተው እንደ ጎሣ ምክር ቤት፣ እንደ ፌዴሪሽን ምክር ቤት፣ እንደ ወንድማማቾች እድር፣ እንደ ተወላጆች ማኅበር፣ እንደ መሳሰሉት ቅርጽ እና መልክ ይዛ እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ መሆኗ ቀርቶ እንተ ታህ
ሕተ ኩሉ መንግሥታት፣ ፓርቲያት ፣ ብሔር ወጎሣ ወመማክርት እንድትሆን የሚፈልጉትን ሁሉ ነፍሴ አጥብቃ ትጸየፋለች፣ በሚቻለኝም ሁሉ እንደ አባቶቼ ይህን እቃወመዋለሁ። እንዲህ እንዲሆን የሚመኝ የሚሠራ ካለም ክርስቶስን ረዳቴ እና ጌታየ አድርጌ ቅዱስ ጴጥሮስ ሲሞንን እንደረገመው እረግመዋለሁ፣ ከኅብረቱ እንደለየውም ቢያንስ ራሴን ከእንዲህ ያለው እለያለሁ።

የእኔ ጥያቄ ለሲኖዶስ፦

እኔ ቅዱስ ሲኖዶስን የምጠይቀው የመብት ጥያቄ የለኝም። ቅዱስ ሲኖዶስ የታዛዦች የአገልጋዮች ጉባኤ እንጂ የባላ ሥልጣናት ምክር ቤት አይደለምና።
እኔ ቅዱስ ሲኖዶስን የምጠይቀው የአካባቢ፣ የጎሳ፣ የቋንቋ፣ ... የመሳሰሉት የውክልና ጥያቄም የለኝም። የሰማያውያን የመላእክት ወንድሞች የሆኑ ይህን ዐለም የካዱ አባቶች ጉባኤ ነውና። ቅዱስ ሲኖዶስን የምጠይቀው የእገሌ ይሾም የእገሌ አይሾም ጥያቄም የለኝም። ጥያቂዬ የሕግ እና የሥርዓት እንጂ የመብት እና የፖለቲካ አይደለምና።

ቅዱስ ሲኖዶስ አማኞች እንደ ፓርቲ ያቋቋሙት በፈለጉ ጊዜ ሕጉን ቀይረው ዘመን የወለደውን ንጉሥ የወደደውን አስመስለው የሚሠሩት ተራ ተቋም እንዳልሆነ ስማር ኖሪያለሁ፣ በዐለም ባሉት ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያን ሁሉም እንዲህ እንዳልሆነ አውቃለሁ፣ አያለሁምና ምንም ዐይነት የመብት ጥያቄ የለኝም። የመብት ጥያቄ ያለው ክርስቲያን ሆኖ ሊኖር የሚችልም የለምና።

የእኔ ጥያቄ መዳኑ በቤተ ክርስቲያን ሊፈጸምለት እንደሚሻ አንድ ኃጢአተኛ እና ደካማ ሲኖዶሴ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኔም ቤተ ክርስቲያን ሆና ማየት ብቻ ነው። ቤተ ክርስቲያንን መገለጫዋን ቅዱስ ሲኖዶስን በሌላው እንዳደረጉት ኢትዮጵያን ይምሰል በሚል ሽፋን ምክር ቤት ይምስል፣ የጎሳ ውክልና ምጥጥን ስሌት ይጠቀም የሚሉትን የምቃወመው ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን እንድትሆን የልጅነት ድምፄን፣ ክርስቲያናዊ ግዴታዬን ለመወጣት ብቻ ነው።

መብት በሚል አደገኛ የፖለቲካ ቃል በር አስከፍቶ ሲኖዶስን የጎሳ ምክር ቤት፣ ቤተ ክርስቲያንም የድኅነት ቤት የፍጥረት ሁሉ መጠጊያ ሐመረ ኖኅ መሆኗን አስጥሎ ጥቅመ ሰናዖር፣ ሐይመተ ፈርዖን ሆና እንድትቆጠር እና ራሷ ከሆነው ከጌታ ከክርስቶስ ከብልቶቿ ከንጹሐን ምእመናን ለመለየት የሚደረገውን ጥረት የምቃወመው ሊቀርብ የሚገባው ጥያቄ የሕግ እና የሥርዓት እንጂ የመብት እና የፖለቲካ አይደለም ብዬ ስለማምን ነው።

ባለፈው ጊዜ በሻሸመኔ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተገደሉ፣ አካላቸው የጎደለ፣ የታሠሩ የተገርፉ እና አሁንም የሚታሠሩ፣ ቤተ ክርስቲያናቸው እስካሁን የተዘጋባቸው፣ በአዲስ አበባ እንኳ ከሥራቸው ተፈናቅለው በደስታ የተቀበሉት ጥያቄያቸው የድኅነት የሕግ የሥርዓት ይከበር ጥያቄ ስለሆነ እንጂ የመብትማ ቢሆን እንዲህ አይሆንም ነበር። እነዚህ ሁሉ ጥያቄያቸው ቤተ ክርስቲያናቸውን ከወንበዴዎች፣ በጎቹንም ከተኩላ ጠብቃችሁ አድኑን የሚል ትሑት እና የመጨረሻ አነሥተኛ ጥያቄ ነው። የእኔም ጥያቄ ድኅነት ፈለገው የመጡ ምእመናን የጌታን ደም በቁርባን ሰጥተው በማዳን ፈንታ የምእመናን ደም ላፈሰሱ፣ በልተው ላልጠገቡ ለተራቡ ተኩላዎች ሰጥታችሁ አታስበሉን፣ ይልቁንም ድኅነታቸውን ሽተው ለሚያድኑን እረኞች አብቁን የሚል ብቻ ነው።

ይህ ካልሆነ ሲኖዶሱ ሲኖዶስ አይደለም ያሰኝና ብዙዎችን ሊያስወጣ፣ ምእመናን ሊከፋፍል፣ ... ሌላም ሌላም ችግር ሊያስከትል ስለሚችል የእነዚያ ሰዎች የድኅነት ጥያቄ የእኔም ልባዊ ጥያቄ ነው።

አባቶቼ የምታመልኩት የምታገለግሉት፣ እኔም ኃጢአተኛው እና ደካማው የማመልከው ላገለግለውም የምመኘው ሕያው እግዚአብሔር በሚያውቀው ጥያቄዬ አንድ እና አንድ ብቻ ነው።

ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትም ሆነ ማንኛውም ነገር በሕግ እና በሥርዓት ፣ ቀኖናውን መሠረት ባደረገ ለማንም በማያዘነብል፣ ለምእመናን ድኅነት እና ለቤተ ክርስቲያን እድገት እንጂ ለፓርቲዎችና እና ለፖለቲከኞች መሣሪያ ባልሆነ ግልጽ እና ሁሉም ሊያውቀው በሚችል በሲኖዶስ በጸደቀ የምርጫ መመሪያ እና ባለማድላት በተመሰከረላቸው አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሲፈጸም ሕግ ሥርዓት ሲተገበር የማየት የልጅነት ጥያቄ ብቻ ነው።

በእኛ ዘመን ለምን ሕግ ይወጣል? ቀኖናስ ለምን ይጠበቃል የሚል ድምጽ ለሚሰሙት እንዴት ይረብሻል በእውነት። ይህ ድምፅ ይሰማል የሚል እምነት ባይኖረኝም መረበሹን አለመናገር ግን ድምፃቸውን እንደ አማራጭ ማስቆጠር መስሎ ስለተሰማኝ ከፊል የተስማማሁ ስለመሰለኝ ነው ያነሣሁት እንጂ ይደረጋል ብዬ አላስብም።

ጥያቄዬ ቅዱስ ሲኖዶስ በዓላማው በክብሩ ጸንቶ እንዲኖር ቅዱስ ጳውሎስ የሚያውኳችሁ ይቆረጡ እንዳለው ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለመጣል እና ቤተ ክርስቲያንን ለማወክ ያሰፈሰፉ ሁሉ በሕግ ተቆርጠው እንዲወድቁ ብቻ ነው።

ጥያቄዬ ቤተ ክርስቲያንን ተሳታፊዎች የሚዘውሯት ተራ ምድራዊ ተቋም ሳትሆን ሰማያዊ መልኳን ይዛ እንድትጸና ሕግ ሥርዓቷ ይከበር የሚል ብቻ ነው።

ጥያቄዬ አሳሳቾች በሚፈጽሙት ችግር ምእመናን እንዳይረበሹ ለድኅነታቸውም መሰናክል እንዳይበዛ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይከበር የሚል የልጅነት ጥያቄ ብቻ ነው።

ይህን መጠየቅ ካልቻልኩማ ምኑን ልጇ ሆንኩት፣ ስማረው የኖሩክትስ ምን ይጠቅመኛል። ለድኅነት ካልሆነስ ምን ይረዳኛል። ቤተ ክርስቲያኔ ቤተ ክርስቲያን ካልሆነችስ ምን ይጠቅመኛል። ፓርቲማ መች ቸገረኝ፣ ሕግ ጥሰት እና ድፈረትማ በዓለም ሁሉ ሞልቶ የለ። ከዚህ ሁሉ የጥፋት ባሕር ቀዝፋ የምታሽግር መርከቤን ሽንቁረው ውኃውን አስገብትው አብረን እናስጥምህ ሲሉኝ ዝም ካልኩኝማ ምኑን ሰው ሆንኩ? የተርሴስ ተጓዦች የተጨነቁትን ያህል ካልተጨነቅሁ ምን እጠቅማለሁ? እነሱ እንዳደረጉት ለመርከቢቱ የከበደውን ነገር ባላውቀው እንኳ ሸክም ካልቀነስኩ ምን ረባሁ? የተኛውን ካልቀሰቀስኩ ወደ አምላክህ ጩህ ካላልኩ ከእነዚያ ተጓዦች የማንስ እጅግ ምስኪን አልሆንምን? ስለዚህ የእኔ ጥያቄ የድኅነት እንጂ የመብት ጥያቄ አይደለም። የመብት ጠያቂዎችንም መስማት አልፈልግም። እርሱ ለፖለቲካ ፣ ለድርጅት፣ ለዚህ ዓለም ሰው ሰራሽ ተቋም እንጂ እግዚአብሔር ለመሠረታት፣ ፍጽምት እና አለነውር እንድትሆን ላደረጋት ቤተ ክርስቲያን የመብት ጥያቄ የለኝም፣ ሊኖረኝም አይችልም። የእኔ ጥያቄ እንተ ላዕኩሉን እንተ ታሕተ ኩሉ ሊያደርጉ የመጡትን በሕግ በሥርዓት ቆርጣችሁ፣ መርከባችን ከሚያናውጥ ማዕበል ቀዝፋችሁ አድኑን የሚል የድኅነት የሕግ የሥርዓት
1.6K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 17:58:02 የእኔ ጥያቄ የድኅነት እንጂ የመብት ጥያቄ አይደለም ፤ ከሲኖዶስ የምጠብቀው እና የምጠይቀው
(መ/ር ብርሃኑ አድማስ እንደጻፉት)

አቤቱ ጌታዬ እና መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሳላውቅ በድፍረት አውቄ በትዕቢት ከመናገር እንድትጠብቀኝ እለምንሃለሁ። ጌታዬ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አንተ በደምህ ከመሠርትሃት በኪድንህም ካቆምካት አካልህ ከሆነች ብልት አድርጋ ከምትሰበስበን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ኅብረት ከሚያወጣ ድፍረት ፣ ምን አገባኝም ከሚል ፍርሃት እንድትጠብቀኝ እኔ ከሁሉ የማንሰው ኃጢአተኛ ልጅህ እለምንሃለሁ።

ጌታዬ ሆይ ከእንግዲህስ ወዳጆቼ እንጂ ባሪያዎቼ አልላችሁም ብለህ ባከበርሃቸው፣ ምሥጢራትህንም ሁሉ በገለጽህላቸው ፍጹማን ወዳጆችህ፣ አንተ ታማኝ መልካም ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ብለህ በምታከብራቸው ትጉኃን አገልጋዮችህ፣ ለባሕርይህ ለማይስማማ ሞት ራስህን አሳልፈህ በሰጠህላቸው ንጹሐን ምእመናን በጎችህ ብለህ እንኳን የአባቶቼን የየትኛውንም ሰው ኅሊና ሊጎዳ ከሚችል ክፉ ሐሳብም ሆነ ንግግር ትጠበቀኝ ዘንድ እለምንሃለሁ። ጌታ ሆይ ከግብዝነት፣ ከአድርባይነት እና ከሚታወቅም ከማይታወቅም ጥፋት እንድትጠብቀን በጎውን እና እውነተኛውን ነገር ብቻም ለመናገር ከአንተ ውጭ እንኳን እኛ የበቁትም ቢሆኑ አይቻላቸውምና ስለቅዱሳንህ ሁሉ ይልቁንም የባሕርያችን መመኪያ የድኅንነታችን ዘውድ ስለምትሆን ንጽሕት እናትህ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ብለህ በመልካሙ መንገድ ብቻ ምራን፣ እኔንም ከዚህ መንገድ አታውጣኝ አሜን። ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ፤ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሜን።

አንዳንድ ሰዎች ስለሲኖዶስ በጻፍናቸው ተነሥተው ጉዳዩን ለመጠምዘዝ ከተቻለም መለያየት እና ጸብ በመፍጠር የሚፈልጉትን ለማሳካት እንደሚጥሩ ስለተሰማኝ፣ በቅንነት ሆነው ጥያቄያችንም የመብት ጥያቄ የመሰላቸው እና እራሳቸውንም የሆነ አካባቢ ተወካይ አድርገው የመብት ጥያቄ ጠያቂ እና አስተባባሪ ሆነው ስላየሁ የእኔ እና እኔንም የሚመስሉ ወንድሞቼ ጥያቄ ምን ዓይነት ጥያቄ እንደሆነ ስለቅዱስ ሲኖዶስ ያለኝን እምነት በማስቀደም በመግለጽ ጥያቄዬን በድጋሜ አቀርባለሁ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፦

ቅዱስ ሲኖዶስ የእግዚአብሔር መንግሥት አስፋፊዎች የመላእክት ወንድሞች የሰማያዊ ዜጎች አንድነት እንጂ የከርስቲያኖች የየአካባቢው ተወካዮች የሚሰበስቡበት ምክር ቤት እንዳለሆነ በደንብ አውቃለሁ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ከብዙ ቋንቋ ተናጋሪዎች የመጡ አባቶች ቢገኙበትም የየቋንቋቸው ወኪሎች ስብስብ እንዳልሆኑም በደንብ አውቃለሁ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ከየአካባቢው ተወልደው አድገው በመጡ አባቶች የተመላ ቢሆንም የየተገኙበትና የየመጡበት አካባቢ ተወካዮች እና የወንበር ምድብ ቆጣሪዎች ስብስብ እንዳልሆነና ሊሆንም እንደማይችል፣ እንደማይገባውም በደንብ አውቃለሁ።

ቅዱስ ሲኖዶስ በሰማይ ያለች የእግዚአብሔርን መንግሥት በምድር ሆነው ያገለግሉ ዘንድ የሚላኩ የእግዚአብሔር አምባሳደሮች ስብስብ እና ለላካቸው ለእግዚአብሔር መንግሥት ፍላጎት ብቻ የሚሠሩ በተፈጥሮ ከሰው ወገን ቢሆኑም በክህነት ምክንያት ከመላእክት ወገን የሆኑ እና እንደ መላእክትም ለሁሉም እኩል ቅርብ የሆኑ ሊሆኑም የሚገባቸው አባቶች ስብስብ እንደሆነ አምናለሁ። ከዚህም የተነሣ ከመካከላቸው ከላከው ከእግዚአብሔር እና ከሾመችው ከአካሉ ከቤተ ክርስቲያን ፈቃድ ወጥቶ የራሱን ፈቃድ የሚከተል፣ የምድራዊ መንግሥታትን ፈቃድ ለመፈጸም እና ለማስፈጸም የሚሠራ አካል ቢገኝ ከማኅበረ መላእክት ወገን ሳለ የራሱን ሌላ መንግሥት ማቋቋም ከፈለገ ከዲያብሎስ እና እርሱን እሺ በጄ ካሉት ከሠራዊቱ የሚመደብ እንደሆነ አምናለሁ፤ አውቃለሁም።

በሐዋርያት መዓርግ ተሹሞና እና ተሰይሞ በጉባኤያቸውም ተገኝቶ እውጭ ላሉት ምሥጢር የሚሰጥ፣ ከእነርሱም ጋር የጥቅም ውል ያለው ቢኖር አልደነቅም። እንዲህ ያለው ከሐዋርያት ሲኖዶስ እያለ ከአይሁድ ጋር የጥቅም ውል የተዋዋለ እና ከጉባኤያቸውም የተሰናበተውን ይሁዳን እንደሚመስል እና በእርሱ ምክንያትም ሌሎች እንደማይተቹ በደንብ ተምሬያለሁና። ረቂቅ ባሕርይ በነበረው በሳጥናኤል ምትክ ከመሬት አፈር የተፈጥረው አዳም እንደተተካ፤ በይሁዳም ምትክ ማትያስ በሐዋርያት እጩነት ቀርቦ በዕጣ እንደገባ ከአባቶቼ ተምሬያለሁ፣ አውቃለሁምና የሚወጣ ቢኖር አልደነግጥም አልረበሽምም። እንዲህ ባላው ሰው ምክንያት ቤተ ክርስቲያን ስሟ እንደማይጎድፍ ክብሯ እንደማይቀንስ ሁሉን የሚያውቅ ጌታ አስቀድሞ አለማስገባት እየተቻለው ለይሁዳ እድሉን በመስጠት አስተምሮናልና።

ቅዱስ ሲኖዶስ ለእጃችሁ በትር አትያዙ የተባሉ ሐዋርያት ወራሽ እንጂ ሰይፍ፣ ጎራዴና እና ዱላ ይዘው ክርስቶስን ለመያዝ የመጡ፣ ዳዊት በመዝሙሩ አገቱኒ ከለባት ያላቸው ለምድራዊ ገዥዎች ፍላጎት የሚጮሁ የዚያ ዘመን አይሁድ ወራሽ እንዳልሆነ አውቃለሁ፣ አምናለሁም።

ቅዱስ ሲኖዶስ በዐመጻው ምክንያት መልአከ እግዚአብሔር በሰይፍ እጁን የቀጣውን ታውፋንያን ንስሐውን ተቀብሎ በተአምራት እጁን መልሶ ዐመጸኛውንም ወደ ትሕትና እና መታዘዝ የሚመልሱ የቅዱስ ጴጥሮስ ልጆች ስብስብ እንጂ እንደ አውሳብዮስ እና ጓደኞቹ የመንግሥታትን ጉልበት ተጠቅሞ ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍሉ ሰዎች ስብስብ እንዳለሆነ አውቃለሁ፣ እንዲህ ሆኖ እንዲኖርም እጠብቃለሁ።

ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት እንደ ጠቢቡ ሰሎሞን ረቂቅ ፍርድ ፈርዶ ሕዝቡን የእግዚአብሔርን መጋቢነት የሲኖዶስን መንፈስንቅዱሳዊነት ሊያሳይ እንደሚተጋ እንጂ እንደ ኢሳይያስ የንጉሥ ድምፅ ፈርቶ እኔ ምን አገባኝ ብሎ ቤተ ክርስቲያንን ለዖዝያን ፍላጎት አሳልፎ በመስጠት ለምጻም የሆኑ ሰዎች ስብስብ እንዳልሆነ ፣ እንደማይሆን፣ ሊሆንም እንደማይገባው አምናለሁ፤ እጠብቃለሁም።

ቅዱስ ሲኖዶስ የእግዚአብሔር መንግሥት ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ተጨንቆና ተጠብቦ እንደ ጳውሎስ እስከ ዕልዋሪቆን እንደ በርተሎሜዎስም በላእተንሰብእ ያሉበት ድረስ ሔዶ ለመስተማር የሚያስቡ አባቶች ስብስብ እንጂ እንደ አካባቢ የልማት ድርጅቶች በየአካባቢው ሕንፃ ለመሥራት ግንብ ለማቆም የሚሯሯጡ ውሉደ ባቤል ደቂቀ ናምሩድ ስብስብ እንዳልሆነ አምናለሁ፣ ተስፋም አደርጋለሁ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ቄሣር ግቢ ቢገባ እዚያ ያሉትን ለውጦ እንደ ጳውሎስ ከቄሳር ቤት የሆኑት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል የሚሉ ጥቡዓን ስብስብ እንጂ እንደ ዴማስ በከተማ ውበት በቤተ መንግሥት ግርማ ተሰልቦ አላማውን ለውጦ የሚኖር ከተሜዎች ስብስብ እንዳለሆነ እረዳለሁ።

ቅዱስ ሲኖዶስ እንደ ዲዮስቆሮስ ጥርሱ እስኪረግፍ ቢደበደብ እንደ አትናቴዎስ አምስት ጊዜ ቢሰደድ በትዕግሥት መከራውን ተቀብለው ቤተ ክርስቲያንን የሚያሻግሩ ፣ ዐለም ትቷችኋል ቢባሉ ልክ እንደ አትናቴዎስ እኔም ዐለምን አልፈልገውም የሚሉ ልበ ሙሉዎች ስብስብ እንጂ በቤተ መንግሥት ማዕድ እና ሽንገላ ልባቸው የሚማልል አባቶች ስብስብ እንዳልሆነ አውቃለሁ፣ እጠብቃለሁም።

ቅዱስ ሲኖዶስ እንደ ሲሞን ገንዘባቸውን ይዘው እናንተ የያዛችሁትን መዓርግ ልያዝ፣ ጓደኞቼ ከደረሱበት ልድረስ ብለው በእኔ ጊዜ ነው ወይ መመሪያ የሚወጣው እያሉ ዘመድ አዝማድ ስጦታ አስይዘው በመላክ፣ ውለታ ቆጥረው በማስታወስ የሚወተውቱ ሲሞናዊያንን ገንዘብህ ይጥፋ፣ ሀሳብህም አይፈጸም እያለ እነርሱን ትቶ ማትያስን በይሁዳ ፈንታ በተካበት መንገድ ለመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሚሆኑትን የሚሾም ወራሴ ጰጥሮስ ወሐዋርያት እንደሆነ አውቃለሁ አምናለሁም።
1.3K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ