Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxtewahedo
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 47.96K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ።
‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ››
ት.ኢሳ 58÷3
https://youtu.be/csxxAMGtC4I
ለመቀላቀል
http://t.me/ortodoxtewahedo

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-05-15 21:15:39
"እስልምናን ተቀበሉ የተባሉት ግለሰብ በሀገረ ስብከታችን በየትኛውም አጥቢያ ፈጽሞ የማይታወቁ ናቸው" የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት

ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ሰሞኑን በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በወራቤ ከተማ እስልምናን ተቀበሉ እየተባለ ሲነገርላቸው የነበሩትን ግለሰብ አስመልክቶ የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ ግለሰቡ በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሌሉ እና ፈጽሞ የማይታወቁ መሆኑን አስታውቋል።

በመሠረቱ ማንኛውም ሰው የፈለገውን ማመን መከተል እንደሚችል በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ሕግ የተፈቀደ ነው ያለው ሀገረ ስብከቱ ይሁን እንጂ እስልምናን ተቀበሉ የተባሉት ግለሰብ በሀገረ ስብከታችን በየትኛውም አጥቢያ የማይታወቁ እና "ቄስ" ናቸው መባሉ ፈጽሞ ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን እየገለጽን መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ከእንደዚህ ዓይነት ሀሰተኛ መረጃ ራሳቸውን እንዲጠብቁና የታነጹበትን መሠረት ክርስትናቸውን እንዲያጸኑ ሲል በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አሳስቧል፡


@orthodoxtewahedo
2.4K viewsedited  18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 17:44:37 አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመክራሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይናገራሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይፈፅማሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይሠራሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስማማሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያከናውናሉ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይልካሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያሰለጥናሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ምስክር ይሆናሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሰውን ይስባሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያለምዳሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመክራሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያነጻሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸራሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያከብራሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸናሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስጨክናሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስተምራሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይጋርዳሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያለብሳሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ባለምዋል ያደርጋሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይቀመጣሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይፈርዳሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመረምራሉ ።
እንዲህ እናምናለን እንዲህም እንታመናለን አንድነትን ሳንለይ የተለየ እንዳይሆን ። የተቀላቀለ እንዳይሆን እንለይ።

እንደ አብርሃምና እንደ ይስሐቅ እንደ ያዕቆብም ሦስት የምንል አይደለም በገጽ ሦስት ሲሆን አንድ ነው እንጂ ።
ከፍጥረት ሁሉ እንደሚቀድም እንደ አዳም አንድ የምንል አይደለም በባሕርዪው አንድ ሲሆን ሦስት ነው እንላለን እንጂ ።

ክፉዎች አይሁድ ባለማወቃቸው የእግዚአብሔርን ገጽና አካል አንድ ነው የሚሉ በደለኞችን የይስማኤል ወገኖችንም እነሆ እንሰማቸዋለን ልቦናቸውን ያሳወሩ ናቸው ።

አምላኮቻቸውም ብዙ አጋንንቶቻቸው ብዙ የሆኑ በጣዖት የሚያመልኩ አረማውያንን እነሆ እናያቸዋለን ። እኛ ግን በጎ ጐዳና የሚያስተምሩትን እንከተላለን ። ሐዋርያት እንዲህ እያሉ እንዳስተማሩን ።

አብ ፀሐይ ነው ወልድ ፀሐይ ነው መንፈስ ቅዱስም ፀሐይ ነው ። ከሁሉ በላይ የሚሆን አንድ የእውነት ፀሐይ ነው ።

አብ እሳት ነው ወልድ እሳት ነው መንፈስ ቅዱስም እሳት ነው ። በልዕልና ያለ አንድ የሕይወት እሳት ነው ።
አብ ጎሕ ነው ወልድ ጎሕ ነው መንፈስ ቅዱስም ጎሕ ነው ። በብርሃኑ ፀዳል ጨለማ የራቀበት አንድ የጧት ጎሕ ነው ።

አብ ጒንደ ወይን ነው ወልድ ጒንደ ወይን ነው መንፈስ ቅዱስም ጒንደ ወይን ነው ። ዓለሙ ሁሉ የጣፈጠበት አንድ የሕይወት ወይን ነው ።

አብ ሐሊብ ነው ወልድ ሐሊብ ነው መንፈስ ቅዱስም ሐሊብ ነው ። ጭማሪ የሌለበት አንድ ሐሊብ እርሱ ነው ።

እንዲህም እናምናለን እንዲህም እንታመናለን ።
ምንጭ: – ቅዳሴ ማርያም

@orthodoxtewahedo
2.6K viewsedited  14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 17:36:16

"ወመለኮትሰ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ ፩ አምላክ አሐቲ መንግስት ወአሐቲ ስልጣን ወአሐቲ ምኲናን

መለኮት ግን አብ ወልድ መንፈስቅዱስም ነው። አንድ አምላክ አንዲት መንግስት አንዲት ሥልጣን አንዲት አገዛዝ ናቸው። "
አኰቴተ ቁርባን ዘእግዝእትነ ማርያም


@orthodoxtewahedo
2.0K viewsedited  14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 17:35:39
እንዲ እናምናለን አንታመናለን አብ ወልድ መንፋስ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር ብለን።

" አንዱ አብ ቅዱስ ነው። አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው። አንዱ መንፈስ ቅዱስም ቅዱስ ነው።

ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ

#እንኲን ለአብርሀሙ ሥላሴ በዓል አደረሳቹ አደረሰን ።

"+ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን::

+ (ቆሮ. 13:14)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedo


We believe that we do not believe that the Father, the Son, the Spirit, the Holy Spirit are one God.

"One is the Holy Father. One is the Holy Son. One is the Holy Spirit.

Liku Yohannes Afework

#Enquin delivered us the message for the Trinity of Abraham festival.

"+ May the grace of the Lord Jesus Christ, the love of God, and the unity of the Holy Spirit be with you all. Amen.

+ (Cor. 13:14)



#have a nice day

#Bal-e-Matebeun to here
Invite a group

To join
@orthodoxtewahedo
1.8K views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 17:32:46
http://t.me/ortodoxtewahedo
1.5K viewsedited  14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 17:32:30 የምናከብራችሁ አባቶቻቸን ሆይ ያስተማሯችሁ መምህራን ተዋክበውና ታስረው ከእናንተ ደጅ የማይደርስ ይመስላችኋልን?

የእናንተን ባናውቅም እኛ ግን እነሱን ባሰብን ጊዜ ሂደንም ባየን ጊዜ ልባችን ይደማል!

የኔታ ብላችሁ ቀለም ቀስማችሁ የእግዚአብሔርን ቃል የተማራችሁባቸው ጉባኤ ቤቶች ተዘግተዋል።

እነዛ ተቀምጣችሁ የቤተ ክርስቲያንን ጣእም የቀመሳችሁባቸው ወንበሮች ታጥፈዋል።

እነዚህ ጎጆዎች ያልፈረሱት በእነሱ የእግዚአብሔር አገልግሎት ቀናኢነት ነው።

አብነት መምህራኑ ግን የድርሻችንን እንወጣ አሉ እንጂ ወደ እናንተ አልቀሰሩም። በጉባኤ በር እንኳ ሳያልፉ ነገር ግን በከተማ በቅንጡ ቤት በሚኖሩት እና ዘመናዊ መኪና ከያዙ አገልጋዮች ራሳቸውን አነጻጽረው አልታገዝንም እና እንበተን አላሉም።

 ዛሬም የተራበና የተጠማ የተማሪ ፊት እያዩ በሰቀቀን ያስተምራሉ።

 እየራባቸው እየቸገራቸው ጉባኤ ዘርግተው በእግዚአብሔር ቃል ይበረታሉ።

ይህን ሁሉ ዋጋ የሚከፍሉት የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ እንዳይቋረጥ ነው።

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲቀጥል ከተፈለገ አብነት ትምህርት ቤት መምህራንን መጠበቅ መብት ሳይሆን ግዴታ ነው።

ቤተ ክርስቲያን ለጉባኤ ቤት መምህራን ጥበቃና ከለላ ማደረግ ያለባት ለማንም ብላ ሳይሆን ለሕልውናዋ ስትል ነው።

ምእመናን አባቶቹን እንደዐይኑ መጠበቅ ያለበት ደስ ስለሚለው አይደለም እግዚአብሔር የሚያይባቸው ዐይኖቹ የሆኑ ካህናትን የሚያፈሩ ስለሆኑ ነው።

እናም የመምህር ኃይለማርያም ዘውዱ ጉዳይ ሊገዳችሁ ይገባል። አንድ የጉባኤ ሊቅ እንዴት ባለቤት አይኖረውም?

እንደእናንት "በእንተ ስማ ለማርያም" ብለው ከውሻ ተጋፍተው ተምረዋል።

ገጠር ከተማ ሳይሉ ጉባኤ ዘርግተው ሊቃውንትን ሰጥተውናል።

በዚህ 2 ቀናት እንኳ ስንት ጉባኤ ታጠፈ? እሳቸውን የሚጠብቁ ስንት ምእመናን አንገት ደፉ?

ቢያንስ ምን ማድረግ ባትችሉ ያሉበትን ሁኔታ ከሚመለከታቸው ጠይቃችሁ ካለጥፋት ከሆነ በሕግ አምላክ በሉልን! ያልተረዳነው ካለም ለምእመናን አስረዱን!

ዛሬ በዝምታ ያለፋችሁት እውነት ነገ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን አለማንኳኳት አይችልም! ለመምህሩ የመጣ ለተማሪው አለመድረስ አይችልምና!

ሌላው ቢቀር ለምእመናን ስነ ልቦና ስትሉ ዋኖቻችንን ጠብቁልን!

ቤተ ክርስቲያን ችግር ባጋጠማት ጊዜ በልጅነታችሁ ከጎኗ የነበራችሁ የሕግ ባለሙያች ከእግዚአብሔር ጋር ከእናንተ ብዙ እንጠብቃለን! ከሊቁ ጎን ቁሙልን!

መስከረም ጌታቸው

http://t.me/ortodoxtewahedo
1.8K viewsedited  14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 13:35:37
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ብንረሳሽ ቀኛችን ትርሳን ባናስብሽ ምላሳችን በጉሮሮዋችን ይጣበቅ።

http://t.me/ortodoxtewahedo
2.1K viewsedited  10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 13:29:57
የተጠመቅነው ክህደትን ልንቃወም እንጂ ልንቀበል አይደለም።

ዲዮቅልጥያኖስ ነግሶ አርዮስ ጰጵሶ ሞት እና እስራት ብርቅ አይሆንም ትልቁ ተስፋቺን ከንጹህ ወርቅ ይልቅ የነጻው የሰማእታቱ ደም እንደ ሊቁ እና የቤተክርስቲያን መከራ መከራቸው ለሆነላቸው መምህር ኃይለማርያም ዘውዱ የቀኖቱ እትራት ምስክር ሆኖ እናት ቤተክርስቲያንን እና ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን አምላከ ቅዱሳን ነጻ እንደሚያወጣቸው አንጠራጠርም
#እርፍ_ይዞ_ወደኀላ_የለም

እውነተኛ መምህሮቻችን በረከታችሁ ይደርብን

http://t.me/ortodoxtewahedo
2.2K viewsedited  10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 06:10:44
ካህን ታፍኖ ታሥሮ ዝም የሚል ሲኖዶስን መንፈስ ቅዱስ ይመራዋል ብለን አናስብም፤ አንጠብቅምም።
አባቶቻችን እውነት በመምህሩ መታሠር እጃችሁ ከሌለበት የታሠሩት የጉባኤ መምህር ናቸውና ዝምታችሁን አስወግዱ። ካልሆነ ግን እናንተን የሚተቹትን እየመረጣችሁ የምታሣሥሩ እናንተ ናችሁ።
በርግጥ የተወሰኑ አባቶች በጨለማው ሲኖዶስ ውስጥ ሆነው የሚሠሩትን ሥራ እያየን ነው። ጊዜ እንጠብቅ ብለን እንጂ ሀሉንም እንገልጠዋለን።
መንፈስ ቅዱስ የሚመራችሁ ከሆነ ኪህናችሁን አስፈቱ፤ ካህኑን የሚያሣሥር መንፈስ ቅዱስ የሚመራው አካል የለምና ዝምታችሁን ስበሩ።
ትናንት በምእመን የተጀመረው እሥራት ዛሬ ካህን ላይ ደርሷል። ቀጣዩ ተራ የእናንተው ነው። የሚያዋጣው ከምትመሩት ምእመን ጋር መሆን ነው።
የምእመናን ጅረት አይቋረጥም፤ ፖለቲካ ግን ነገ ይጠፋል።

ድምፀ ተዋሕዶ

http://t.me/ortodoxtewahedo
2.5K viewsedited  03:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 07:31:38
607 views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ