2023-05-16 08:58:13
ትናንትም የነበረው፣ ዛሬም ያለው፣ ነገም ሆነ ለዘላለም የሚኖረው ለወገነኖቹ በመጽሐፍ እንዲህ ብሎ የተናገረውና እኛ ዛሬ የምናመልከው፣ አባት ብለን የምንጠራው እግዚአብሔር መሆኑን አንዘንጋ! በቤቱ አንቀልድ:-
መቃባያን ቀዳማዊ 13፣ 30-41
ክፉ ሥራ ሁሉ ቅሚያና ትዕቢት፥ ስስትም በአሳባቸው የተዘጋጀ ነው። ስለዚህም እግዚአብሔር ቸል አላቸው፣
ከተሞቻቸውንም ገለበጣቸው፤ እስከ መሠረታቸው ድረስ በእሳት ያቃጠላቸውም አሉ እስከ ዘለዓለም ድረስ ፈጽመው ጠፉ ከእነርሱ አንድ ስንኳ አልቀረም" 0ኀጢአት ታስረዋልና የዘለዓለም ፍርድ እስከሚሰ ጥባት እስክ ታላቋ የፍርድ ቀን ድረስ ይቈያሉ፤ በክፉ ሥራቸውም አሳዝነውኛልና አልምራቸውምº ይቅርም አልላቸውም" እኔም ቸል አልኋቸው፤ እንደዚሁም የኢየሩሳሌም ልጅ: በፍርድ ቀን አንቺ ጐስቋላ የኢየሩሳሌም ልጅ እንደእነርሱ ትታሰሪያለሽ፤ ሥራሽ ሁሉ ቅሚያና ኀጢአት፥ ዝሙትና ስስት፥ ሐሰት መናገርም፥
እኔም የማልወደው የስሕተትና የድጥ መንገድ ስለ ሆነ ተቈጥቼ በያዝሁሽ ጊዜ ምክንያት አታገኝምና። እኔ ለክብር አድርጌሽ ነበር፤ አንቺ ግን ራስሽን ለውርደት አደረግሽ፤ እኔ ለእኔ ብዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ለሌላ ሆንሽ። እኔ ለቅድስና አጭችሽ ነበር፤ አንቺ ግን ለዲያብሎስ ሆንሽ፤ እኔም እንደ ሥራሽ ክፋት እበቀልሻለሁ። ቃሌን ሁሉ ስላልሰማሽ፥ በወደድሁሽም ጊዜ ያዘዝሁሽን ትእዛዝ ስላልጠበቅሽ
የፈጠርሁሽ እግዚአብሔር እኔ ነኝና ክፉ በቀልን አበዛብሻለሁ፤ እንደ አንቺ ባሉ በኃጥኣንም ሁሉ ላይ እቈጣለሁ፤ እንደ ክፋታቸውም በፍርድ ቀን እከፍላቸዋለሁ።
ቃሌንም አልጠበቅሽምና፥ ፍርዴንም ቸል ብለሻልና አንቺንም ከእነርሱ ጋር እቀጣሻለሁ።
በልቡናችሁ እግዚአብሔርን መፍራት የሌላችሁ፥ ሰዶምና ገሞራ፥ ወዮላችሁ። በእሳተ ገሃነም ካንቺ ጋራ በአንድነት የሚፈረድባት እኅትሽ የኢየሩሳሌም ልጅ እንደዚሁ ወዮላት! ለዘለዓለሙ መውጫ ወደሌለበት ወደ ተዘጋጀው ወደ ገሃነም በአንድነት ትወርዳላችሁና ያንቺን ሥራ የሠሩ ሁሉ ወዮላቸው። ቃሌንና ትእዛዜን አልጠበቃችሁምና ቃሌንና ትእዛዜን ያልጠበቃችሁ አንቺና እርሷ, በፍርድ ቀን በአንድ
ነት ወደ ሲዖል ትወርዳላችሁ"
1.7K views05:58